የትግራይ ህዝብ ጥቅምና መፃኢ ዕድል የሚረጋገጠው በመገንባት ላይ ባለችው ኢትዮጵያ ላይ ነው – ሜ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ (ዶ/ር)

ሜ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ (ዶ/ር) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመዳኤ ወይም ኢንሳ በመባል የሚታወቀው ተቋም) ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ሜ/ጄነራል ተክለብርሃን ነባር ታጋይ ሲሆኑ፤ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈው እዚህ የደረሱ ሲሆን፤ በትምህርታቸው ደግሞ የሶስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) ይዘዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ማይክሮሊንክ ኮሌጅ በኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ ተምረዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸው ደግሞ በለንደን ከተማ በሚገኘው ለንደን ዩኒቨርስቲ በሴኩሪቲ ኢንጅነሪንግ ተምረዋል፡፡ በአሜሪካ አገር በሚገኘው ዋልደን ዩኒቨርስቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ማኔጅመንት የሶስተኛ ዲግሪያቸው (ዶክትሬት) ይዘዋል፡፡ ሜ/ጄነራል ተክለብርሃን ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ናቸው፡፡ ሜ/ጄነራል ተክለብርሃን ከውራይና መፅሄት ባለቤትና ማ/ዳሬክተር ጋር ያደረጉትን ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ ለአንባቢዎቻችን እየጋበዝን፤ ለዚህ ቃለ-መጠይቅ ፈቃደኛ ስለሆኑ ለሜ/ጀነራል እያመሰገንን፤ ለአንባቢያን መልካም ንባብ እንመኛለን፡፡

ውራይና፡- በአሁኑ ወቅት በሃገራችን አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች እያየን ነው፡፡ የተለያዩ ሰዎችን ባልተደራጀ መንገድም ቢሆን ስለጉዳዩ እያወሩና እየተከታተሉትም ይገኛሉ፡፡ ከዚህ አንፃር በምንናሳቸው አከባቢያዊ፣ ክልላዊና ሃገራዊ ውይይቶችና ትንታኔዎች (discussion and analysis) ልንመለከታቸው የሚገቡን አለም- አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ዝንባሌዎች (global trends and circumstances) ምንድ ናቸው ትላለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- አለምአቀፋዊ ሁኔታውን በተለያየ መንገድ ማየት ይቻላል፡፡ እኔ ግን ይህ ጉዳይ በፖለቲካዊና ቴክኖሎጂካዊ መነፀር ማየት እፈልሃለሁ፡፡ ቴክኖሎጂ በፖለቲካ ሂደቱ ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ የዚህ መገለጫ ደግሞ ዓለምን ወደ አንድ መንደር እየቀየረ ያለው ግሎባላይዜሽን ብለን የምንጠራው ሂደት ነው፡፡ ግሎባላይዜሽን የምንለው አስተሳሰብ ከመጣ ደግሞ 20 ዓመታትን ያስቆጠረ ክስተት ነው፡፡ የዚህ አስተሳሰብ መሰረቶች ደግሞ አንደኛው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕድገት ያመጣው በኢንፎርሜሽን የመቀራረብና የመተሳሰር ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ደግሞ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ የወለደው መስተጋብር ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ዕድገቶች ቴክኖሎጂ የወለዳችው መተሳሰሮች ናቸው፡፡

ሁለተኛው ጉዳይ ግዙፍ ኩባንያዎች የዓለም ገበያ በመቆጣጠራቸው ምክንያት የተፈጠረ መስተሳሰር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሚፈጠረው መተሳሰር (መስተጋብር) ኩባንያዎቹ የሚሰጡት የምርትና የአገልግሎት አለማቀፋዊነት አማካኝነት የሚፈጠር ነው፡፡

ሶስተኛው መሰረታዊ ጉዳይ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ልውውጦችን እንዲቆጣጠሩና ፍትህ እንዲነግስ ለማድረግ ታልሞ የተቋቋሙት ተቋማት ናቸው፡፡ እነዚህ ተቋማት በማን ፍላጎት እንደተቋቋሙ ሌላ ጉዳይ ሆኖ እንደ አለም-አቀፍ ፍርድ- ቤት፣ የዓለም ባንክ፣ አይኤምኤፍ፣ የተለያዩ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ወዘተ ያካተቱ ናቸው፡፡ በመሆኑም በነዚህ ተቋማት አማካኝነት ላለፉት 20 ዓመታ እየተጠናከረ የመጣ አለም-አቀፍ መስተሳሰር (ግሎባላይዜሽን) አለ፡፡ በዚህ ምክንያትም በተለየም አሜሪካ ልዕልናዋን እያረጋገጠችና የዓለም ፖሊስ ሆኖ እንድትንቀሳቀስ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በተለይ ደግሞ ቀዝቃዛው አለም ጦርነት ካበቃ በኋላ የተፈጠረው ሁኔታ ይህ ነው የሚመስለው፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ይህ ሁኔታ እየተቀየረ መጥቷል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ አንደኛው የዓለማችንን ሁኔታ መወሰን የሚችሉ አዳዲስ ሃይሎች መፈጠራቸው ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በኤስያ በከፍተኛ ደረጃ የኢኮኖሚ ዕድገት እያመጡና በዚህም አማካኝነት አለም-አቀፍ ጫና መፍጠር የቻሉ እንደ ህንድና ቻይና የመሳሰሉ ሃገራት ግንባር ቀደም ተጠቃሶች ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ብሪክስ (BRICs) እየተባለ በሚታወቀው አዲስ የሃገራት የማህበር ባንክ የሚገለፅ አዲስ ለውጥና አስተላለፍ ነው፡፡ ስለዚህ የአለማችን ቀጣይ ሁኔታ የሚወስነው በነዚህ ሃይሎችና አሰላለፎች ፍትጊያ/ውድድር ነው ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ ቻይና የወሰድን እንደሆነ ከአሜሪካ ብቻ ሊመነጭ የነበረው አለም-አቀፋዊ ትስስር ለመቀማትና የመተካት እየሰራች ነው፡፡ ይህ የአሜሪካ የኢንተርኔት የበላይነት (hegemony) በመቀማት ሊሳካ የሚችል ነው፡፡ የፈጠረችው የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻውን የራሷን አለም-አቀፍ መተሳሰር እንዲኖራት ስለሚያስገድዳት በራሷ መንገድ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ ህንድም ተመሳሳይ መንገድ ጥረት እያደረገች ነው፡፡ ቻይና፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ብራዚልና ደቡብ አፍሪካ እየፈጠሩት ያለ ህብረትም ቢሆን በአሜሪካ የበላይ አዛዥነት የሚንቀሳቀሱትን እንደ የአለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ ለመተካት አልያም በራሳቸው ተቋም ለመጠቀም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም የነበረው የግሎባላይዜሽን እንቅስቃሴና ሁኔታ በሌሎች አዳዲስ ሃይሎች እየተፈተነ ነው ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በራሳቸው ውስጥ በ2008 እ.ኤ.አ. የተከሰተው የገንዘብ ቀውስ ምክንያት የተፈጠረው መንገራገጭ እየፈተነው ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በተለይም በነፃ-ገበያ እሳቤ (ኒዮሊበራሊዝም) ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ እንደነ ፍራንሲስ ፍኩያማ የሚባሉ ኒዮሊበራሊዝም የሚቀናቀነው ሃይል የለም እያሉ ”the end of history” መጽሐፍ ላይ የፃፉት አስተሳሰብ ተመልሰው ሃሳባቸውን እንዲከልሱ ያደረገ ክስተት ነው፡፡ ካፒታሊዝም የነበረው ሊቀጥል አይችልም የሚል ስጋት የወለዳቸው የተለያዩ አማራጭ ምሁራዊ ትንታኔዎች ፅንሰ-ሃሳቦች ብቅ እያሉ ነው፡፡ በመሆኑም አዳዲስ አማራጭ መንገዶችን የማፈላለግ ዝንባሌዎች እየታዩ ነው፡፡

ከዚህ በመነጨ ምክንያት ደግሞ ዲሞክራሲ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡ ምርጫ ባላደጉት አገሮች ይቅርና እንደ አውሮፓና አሜሪካ ባሉ ያደጉ አገሮች ጭምር ፈተና እየገጠመው መጥቷል፡፡ ይህ ጉዳይ በተለይም ከሳይበር ጦርነት ጋር ተያይዞ በግልፅ የሚታይ እውነታ ሆኗል፡፡ በተለይም ከትራምፕ መመረጥ ጋር ተያይዞ በሩስያና አሜሪካ መካከል የተፈጠረው ጭቅጭቅ፤ በጀርመን የተካሄደው ምርጫ፣ በፈረንሳይ በተደረገው ምርጫ ወዘተ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭቅጭቆች አሉ፡፡ አሁን ደግሞ በቀጣይ በሩስያ የሚደረገው ምርጫ አሜሪካ በሳይበር ውግያ በምርጫው ውጤት ልታዛባው ትችላለች የሚሉ ስጋት አለ፡፡ ስለዚህ የሳይበር ጦርነት የሚባለው በኢንፎርሜሽን አማካኝነት የሰውን አስተሳሰብ ለመቀየር የሚደረግ፤ በዚህ የስነ-ልቦና ጦርነት አማካኝነት ደግሞ በአስተዳደራዊ ሌሎች ጉዳዮች የሚፈጥረው ተፅዕኖ፣ ስጋትና ችግር አለ፡፡ በዚህ ምክንያት ምርጫ ሆነ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ተአማኒነታቸው ጥያቄ ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታ በኬንያ በተደረገው ምርጫም ታይቷል፡፡

ስለዚህ ህዝቦች በተቋማት የነበራቸው መተማመን እየጠፋ ይገኛል፡፡ ሌላው በአለማችን እየታየ ያለው አዲስ ዝንባሌ የቀኝ-ዘመም አክራሪ ሃይሎች የበላይነት ለማረጋገጥ እያደረጉት ያለ እንቅስቃሴ ነው፡፡ እነዚህ ቀኝ-ዘመም የምንላቸው በህዝበኝነት (populist) የሚታወቁ ናቸው፡፡ እነዚህ በአሜሪካም በአውሮፓም የታዩ ናቸው፡፡ አለም በቀውስ ውስጥ የምትሆንበት ለምሳሌ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጋር በተያያዘ የነበረ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከጊዜው ጋ በነበረው አለማ-አቀፍ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እንደተፈጠሩት የፋሺሊዝም፣ ናዚዝም ወዘተ አስተሳሰቦች እንዳደጉበት ነው፡፡ ያም ሆኖ ይህ እነዚህ አስተሳሰቦች ነባሩን መዋቅር (establishment) እየተፈታተኑት ያሉት ናቸው፡፡ በመሆኑም በመርህ የሚመራ ሳይሆን በስሜትና የግል ፍላጎት የሚዘወር እየሆነ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አደጋ ውስጥ እየከተቱት ናቸው፡፡ የተሟላ ዲሞክራሲ ገንብተዋል በምንላቸው እንደ ስዊድን የመሳሰሉ አገሮች በፀረ-ስደረኞች የሚገለፀው እንቅስቃሴ የዚሁ አስተሳሰብ አንድ አካል ነው፡፡ ይህ ማለት ራስን በማጠር የራሴ የምትለው ህዝብ ብቻ በመንከባከብና በመጠበቅ፤ ለሌሎች ሰዎች (ወይም መጤ ለምትላቸው) የማጥቃትና የመጉዳት እንቅስቃሴ እየተፈጠረ ነው ማለት ነው፡፡

በሌላ አነጋገር በእንግሊዘኛው ዜኖፎብያ (xenophobia) የምንለው አስተሳሰብና ተግባር እያቆጠቆጠ ነው ማለት ነው፡፡ ዜኖፎብያ ማለት ከውጭ በመጡ ሰዎች (መጤዎች) ላይ የሚደረግ ጥልቅ የጥላቻ ስሜት ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በአገር ውስጥ የሚፈጠረው ቀውስ በስደተኞች አማካኝነት ነው ብሎ የማመንና መፍትሄው ደግሞ ስደተኞችን እንዲወጡ የማድረግ ሁኔታ ነው፡፡ የውስጥ ችግር አይቶ የችግሩን ምክንያት በደንብ ምርምሮ መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ በስሜት ዜጎችን በሌሎች ሰዎች ላይ እንዲነሳሱ ከማድረግና የቀውሱ ሁሉ ምንጭ እነሱ አድርጎ የመቁጠር አዝማሚያ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ህዝበኝነት የሚያጠቃቸው ሃይሎች ይህን ሁኔታ ይጠቀሙበታል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ወደ ሰልጣን የሚመጡበት ምቹ ሁኔታ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አለም አቀፍ ሽብርተኝነት አለ፡፡ ይህ ሽብርተኝነት የሚፈጥረው ተፅዕኖ አለ፡፡ በተለይ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየው የሽብርተኝነት ተግባር ከሁሉም የባሰ ያለ ነው፡፡ ይህን ለመመከት ተብሎ የሚደረጉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች አሉ፤ በዚህም መንግስት አልባ ሃገራት እየበዙ የመጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ደግሞ በቀለም አብዮት (color revolution) አማካኝነት መንግስት አልባ የሆኑ እንደነ ሊብያ፣ የመን የመሳሰሉ ሃገራት አሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በአገራችን ይሁን በአለም ደረጃ የሚፈጥረው ተፅዕኖ አለ፡፡

ውራይና፡- መጨረሻ ላይ ያነሱት የቀለም አብዮት ጋር ተያይዞ የቴክኖሎጂ ሚና ትልቅ ነበር፤ ከማህበራዊ ሚድያ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ብዙ ነገሮች አሉ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን ፡- አዎ በተለይም ሊበራል ሃይል የሚመራ ስለነበር በተለይም በቴክኖሎጂ ለምሳሌ በፌስቡክ አማካኝነት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በማባባስ ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡

ስለዚህ አለም አቀፋዊ ሁኔታ በአጠቃላይ ሲታይ መልካም አይደለም፤ ያለው ዝንባሌ አሉታዊ ገፅታው እያደገ የመጣ ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ቻይና፣ ህንድ የመሳሰሉ በማደግ ላይ ያሉ የኤስያ ሃገሮች እየፈጠሩት ያለ ዕድገት ተስፋ የሚሰጥ ነው፤ በተለይም እንደኛ ላሉ ሃገራት፡፡ የነዚህ ሃገራት መምጣት በራስህ መንገድ ማደግ እንደሚቻል አርአያ ከመሆን ባሻገር የሚፈጥሩት የኢንቨስትመንት ዕድል ደግሞ ሌላ ጠቃሚ ጉዳይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን በፖለቲካ መነፀር ስታየው የአክራሪነትና ፅንፈኝነት አስተሳሰብ እያቆጠቆጠ መጥቷል፡፡ ነባሩን መዋቅር (establishment) ደግሞ እንዲናጋ እያደረጉት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሉአላዊነት (globalization) ፈተና እያጋጠመው ችግር ውስጥ ነው ያለው፡፡ የራስህ ትናንሽ ግዛቶች ፈጥረህ የመንቀሳቀስ ሁኔታ ይታያል፡፡ አዝማሚያው የሚያሳየው ይህ ነው፡፡ ምንምኳ ሉአላዊነት ጠቅልሎ ወድቋል ባንልም እየታየ ያለው ዝንባሌ ግን ወደ መበታተን (balkanization) የሚያመራ ነው፡፡ በገበያ፣ በኢኮኖሚያዊና የንግድ እንቅስቃሴ አይን ብናየውም ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው፡፡ የመከላከል (protectionist) ባህሪ እያሳዩ በመምጣታቸው ለነበረው ትስስር ትልቅ ስጋት ሆኖበታል፡፡

Photo - General Teklebrhan Woldearegay, Director General of INSA
Photo – General Teklebrhan Woldearegay, Director General of INSA

ውራይና፡- ከንግድ ጋር በተያያዘ መገለጫዎቹ ምንድናቸው? በምሳሌነት ምን ማንሳት እንችላለን?
ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ለምሳሌ ትራንፕ ከኤስያ ጋር የነበረው የንግድ ግንኙነት ማለትም trans-Atlantic partnership (tpp) ሰርዞታል፡፡ ከአፍሪካ ጋር የነበረው AGOA (African growth opportunity act) የሚባለው በተለይም ለአፍሪካ የሚጠቅመውን ስምምነት አሁን ትራንፕ የያዘውን አካሄድ ግምት ወይም ስናስገባ ዕጣ ፈንታው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ በመሆኑም የንግድ ትስስሩና እንቅስቃሴው ፈተና ላይ ወድቋል፡፡ ይህ እንደ ምሳሌ በመውሰድ አሁን ያለው ውድድር ቻይና የምትመራው የኤስያ እና የአሜሪካ መካከል በመሆን በትስስሩ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ አለ፡፡ አንደኛው ይህ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በሽብርተኝነትና በቀለም አብዮት አማካኝነት እየተፈጠረ ያለው የመንግስት አልባ አገሮች መብዛት ያልነው በሌላ መልኩ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡

ይህ አለም አቀፋዊ ሁኔታ በአገራችን የሚፈጥረው ተፅዕኖ መታየት አለበት፡፡ ቀደም ብዬ ለመግለፅ እነንደመኮርኩት ተስፋ የሚሰጡ (ተስፋ የምናደርግባቸው) ዓለም አቀፍ ዕድገቶችም አሉ ብዬ ነው የማስበው፡፡

ውራይና፡- ይህ ወደ ሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ስናመጣው (አንዳንዶቹ ለመነካካት ሞክረሃል) ለአከባቢያዊ፣ ሃገራዊና ክልላዊ ጉዳዮቻችን የምናይበት ርዕዬት ማለትም  ልንጠቀምበት የሚገባን መለኪያዎችና መነፅሮች (frame work and perspective) ምን መሆን አለባቸው ትላለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ጥሩ፡፡ ብዙ ዓይነት ነው ሊሆኑ የሚችሉት፡፡ ፖለቲካዊ መነፅር፣ ጅኦ-ፖለቲካዊ መነፅር፣ ኢኮኖሚያዊ መነፅር እንዲሁም ቴክኖሎጂካዊ መነፅር (frame work and perspective) አሉ፡፡ እነዚህ በመሰሉ የሚታወቁ መነፅሮች ማየት ትችላለህ፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በነዚህ መነፅሮች ብቻ ማየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ውስብስብና እርስ በረሳቸው የተያያዙ ናቸው፡፡ በርግጥ ድሮም ውስብስብ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ያለንበት አለም በፍጥነት የሚያድግ እና ብዙ ለውሶች የሚታዩበት ከመሆኑ አንፃር የአሁኑ ሁኔታ በጣም የተወሳሰበ ነው፡፡

ስለዚህ ከተለመደው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ወይ ሌላ ብቻ የሚል መተንተኛ ወይም መለኪያ ወጣ ብለን መሰብሰብ ፅንሰ-ሃሳብ (complex theory) በሚባል መነፅር ወይም መተንተኛ ማየት አለብን የሚል አስተሳሰብ ነው ያለኝ፡፡

በውስብስብ ፅንስ-ሃሳብ (complex theory) አተያይ (perspective) ደግሞ ስታየው ቋሚ የሚባል ነገር የለም፡፡ ምክንያቶቹ ብዙ ናቸው፡፡ መስተጋብሩና አጠቃላይ ሂደቱ በንቃት መከታተል እንጂ ካለፈው እየተነሳህ የወደፊቱ በመተንበይ መንቀሳቀስ አይቻልም፡፡ ይህ ሳለ ግን መዋቅራዊ (structure) የሆኑ ነገሮች የለም ማለቴ አይደለም፡፡

ለምሳሌ ቴክኖሎጂ የወለደው መተሳሰር መዋቅራዊ ለውጥ አምትቷል፡፡ ፖለቲካዊ ሁኑታው ይለወጥ አይለወጥ በአሁኑ ጊዜ አለም በአንድ ገመድ የታሳሰረበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ ማንም አገር ከዚህ ትስስር ውጭ ልትሆን አትችልም፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉትን በፖለቲካ ኢኮኖሚ አማካኝነት የተፈጠሩት ትስስሮች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡ ሃገሮች በሚያደርጉት የፖሊሲ ለውጥ ሊለዋወጥ ይችላሉ፡፡ ሃገሮች በሚያደርጉት የፖሊሲ ለውጥ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ በጣም ፈጣን ለውጥ የሚታይበት ነው፡፡ ይህች ግን አንዲት መዋቅራዊ ለውጥ ብቻ ናት፡፡

ሁለተኛው መዋቅራዊ ለውጥ የቻይና መምጣትና ከኤሜሪካ ጋር የምታደርገው ፍኩክር የፈጠረው መዋቅራዊ ለውጥ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ዘርፉ ብዙ አለም አቀፋዊ የመዋቅር ለውጥ ነው ያመጣው፡፡ ይህ ሁኔታ የአንድ አገር የበላይነት ሳይሆን የብዙ ሃይሎች ሚዛን የሚንፀባረቅበት ሁኔታ ነው፡፡ ከቴክኖሎጂ በተያያዘ ነዳጅ የነበረው ሚና በቴክኖሎጂ እየተተካ በመምጣት የተፈጠረ ለውጥ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የልሂቃን በዝባዥነት በሚታወቅባቸው ሃገራት የሚፈጥረው ለውጥ አለ፡፡ ስለዚህ ከነዳጅ አቅርቦት ጋር የነበረ ጉዳይ በአዲስ ቴክኖሎጂ እየተመታ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የሃይል አማራጮች የነዳጅን ሚናና ቦታ እየተኩ ሲመጡ የሚፈጠር መዋቅራዊ ለውጥ አለ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የሚፈጥሩት ትስስር በውስብስብ ፅንስ ሃሳብ (complex theory) የማየት ጉዳይ ነው እንግዲህ የመነፅር (perspective) ጉዳይ የምንለው፡፡

ውራይና፡- ስለዚህ በሃገራችን የመጣው ማህበረሰባዊ ለውጥ መሰል መዋቅራዊ ለውጥ አምጥቷል ማለት ይቻላል?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡–  የእኛ ለውጥ ሳው በአንድ በኩል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረት ያደረገ ህይወት የሚመራ በውጭ የተፈጠረ ሃይል አለ፡፡ ማለት በኤስያ፣ አውሮፓና አሜሪካ ማለቴ ነው፡፡ ማህበረሰባዊ መረጃ የሚባል ኢንፎርሜሽን መሰረት ያደረገ የኢኮኖሚ ማህበራዊ መስተጋብር ወዘተ ያለው፤ ኢንፎርሜሽን ሞተር የሆነበት ማህበረሰብ አለ፡፡ ኢንፎርሜሽን ብቻ ሳይሆን ሳይበር ብለን የምንጠራው መተሳሰር (መስተጋብር) ነው፡፡ ይህ በአንዳንዶቹ አባባል ሶስት አብዮቶች ተካሂዶበት የተደረሰበት ደረጃ ነው፡፡ አንደኛው መሬት (እርሻ) መሰረት ካደረገ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ የተደረገ ሽግግር ነው፡፡ ይህ አራት የሚሆኑ ደረጃዎች አሉት፤ መጀመሪያ ማሽን መሰረት ያደረገ የማምረት ሂደት አለ፤ ቀጥሎ ኤሎክትሮኒክስ መሰረት ያደረገ ነው፤ ሶስተኛው ደግሞ ኮምፒተር መሰረት ያደረገ አምራችነትና ትስስር ነው፤ አራተኛው ደግሞ ልክ ኢነርጂ እንዳልነው ከነዳጅ ወደ አዳዲስ አማራጮች የተሸጋገረ ሶስት ነገሮች በማስተሳሰር አምራችነት መሰረት ያደረገ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዲጂታላይዜሽን (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የሚባለው ሰውን የሚተካ የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው፤ በመቀጠል የባዬ ቴክኖሎጂ ብለው የሚገልፁት ነው፡፡ ስለዚህ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ደረጃዎች አልፈዋል ማለት ነው፡፡

እኛ ያለንበት ደግሞ የመጀመሪያ የሽግግር ደረጃ የሚባለው ገና እንጭው ላይ ነው፡፡ መሬት (እርሻ) መሰረት ያደረገ ማህበራዊ ህይወት ነው ያለን፡፡ ስለዚህ መሬት መሰረት ካደረገ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር ጥረት እያደረግን ነው ያለነው፡፡ ምንምኳ ጥረት እያደረግን ቢሆንም ሽግግሩ ግን እስከ አሁን አልተሳካም፡፡ ስለዚህ በኛ እና በቀሪው አለም ያለው ልዩነት በጣም የተራራቀ ነው፡፡ በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ነው ትስስሩ የተፈጠረው፡፡ ከዚህ ደግሞ ማምለጥ አንችልም፡፡

ስለዚህ ባህላዊና እሴታዊ ተፅእኖዎች በኛ ላይ ሊደርስ ግድ ሆኗል፡፡ አለማዊ ተፅዕኖውም ሊያጠፉን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ነጻነታችን፣ ባህላችን፣ ትውፊታችንና አስተሳሰባችን ሊያስጥለን ስለሚችል፡፡ ይሁን እንጂ ትስስሩ ወደ ራሳችን ጥቅም ልንቀይረውም እንችላለን፡፡ ይህ በራሳችን አቅም ነው የሚወስነው፡፡ የኢንፎርሜሽን አቅም ማለት በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ ማለት ነው፡፡ እኛ የሚያስፈልገን ከእርሻ ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር ብቻ ሳይሆን አሁን ያለውን በዕቅቀት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ ማለት ነው፡፡ እኛ የሚያስፈልገን ከእርሻ ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር ብቻ ሳይሆን አሁን ያለውን በዕውቀት የተመሰረተ ሂወት የሚመራው የህብረተሰብ ክፍልም ልናስብለት ይገባል፡፡

ስለዚህ ሌሎቹን በሂደት ረዥም ርቀት ተጉዘን ዕድገታችን ማረጋገጥ አንችልም፡፡ ምክንቱም አለማዊ ሁኔታው ተቀይሯል፡፡ ልዩ ሃብታችን በመለየት ይህን መሰረት አድርገን ነው ማደግ ያለብን፡፡ ለማደግ ደግሞ አሁን የተፈጠረው የቴክኖሎጂ ዕድል ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ ደግሞ መሰረታዊ ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) እየመጣ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ ቅርፅ አልተቀየረም፡፡ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ ደግሞ መሰረታችን ማድረግ የሚገባው ኢንፎርሜሽን ወይም ኢንዱስትሪ ነው፡፡

ውራይና፡- እዚህ ጋ በአንድ በኩል ቴክኖሎጂ መኖሩ ህዝቡ ነፃ እንዲሆን አድርጎታል ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በመንግስት እንዳይጨቆን አልያም አለም እንዳይ አድርጎታል   ማለት ይቻላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ አለማዊ ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ስለማይታየው የተቀነጨ (የተወሰነው) ጉዳይ ብቻ ወስዶ ለቀውስ ወይም እሴቶቻችን እንዲሸረሸሩ ብቻ ነው የሚጠቀምበት የሚባል አስተሳሰብ አለ፡፡ እዚህ ላይ በብዙዎች መደናበር አለ፡፡ እንዴት ነው የሚታየው?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- አዎ ይህ ያየነው አለማዊ ሁኔታ አወንታዊም አሉታዊም ጎኖች አሉት፡፡ ለምሳሌ ቴክኖሎጂ የፈጠራቸው ዕድሎች አሉ፡፡ ቀደም ብለው ሞኖፖሊ የፈጠራቸው ክልከላዎች እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ምንጮች ዕድሎች እየተሰጠን ነው፡፡ መረጃ ለማግኘትና መረጃውን በፍጥነት ፕሮሰስ ለማድረግና ዓለም እንድናውቃት ብቃት ሰጥቶናል፡፡ ይህ መስተጋብር (ትስስር) ታሪካዊ አመጣጥ አለው፡፡ በሳይበር ትስስር የተፈጠረው ከና ቁጥጥር ውጭ በሆነ ሃይል በተለይም በአሜሪካ ነው፡፡ እዚህ ላይ አሜሪካ የምትፈልጋቸው እሴቶች አሉ፡፡ እነዚህ የአሜሪካ እሴቶች ደግሞ የግለሰብ ነፃነትና ጥቅም (liberty and interest)፣ ነፃ- ገበያ፣ ክፍት- ገበያ (deregulated market)፣ ዝቅተኛ ወይም ዜሮ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶች አሜሪካ የደረሰችበት ዕድገት የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡

በቴክኖሎጂ ይሁን በሚጠቀሙበት ቋንቋ እየሸጡት ያሉት እነዚህ የአሜሪካ (የምዕራባውያን) እሴቶች ናቸው፡፡ በምንጠቀምበት ቋንቋ ይሁን ቴክኖሎጂ የነሱ በመሆኑ የነሱ እሴቶች እየወሰድን የራሳችን እሴቶች እየተውን ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በአለም ያለው አጠቃላይ ሁኔታ በራሳችን ፍላጎት ነው እየቀረፁት ያለው፡፡ ይህ ደግሞ በዋነኛነት ገበያ ስለሚፈልጉ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአለም-አቀፍ የንግድ ተቋማትና የሲቪል ሶሳይቲ ማህበራት ተጠቅመው የአለም ሁኔታ ለመቅረፅ በተለይም ባላደጉት ሃገራት (እንደ ደቡብ ኤስያ፣ ደቡብ አሜሪካና አፍሪካ) ሙከራ (experiment) ያደርጋሉ፡፡ እነሱን በሚጠቅም መንገድ እንዲቀርፅ ደግሞ እንደ አላማ ይዘው ይሰሩበታል፡፡ በነሱ እይታ ይህ ስህተት አይደለም፤ አቅማቸው የፈቀደላቸው ሁሉ እነሱን የሚጠቅም ሁሉ ይሰራሉ፡፡

በአንፃሩ ደግሞ ያላደጉ ሃገራት ይህን ጉዳይ በንቃት የሚከለከሉበት አቅም ማሳደግ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ጥቅማቸው የሚረጋገጠው በመከላከል ስለሆነ፡፡ ሁለተኛ ዝም ብለው በራቸው መዝጋት ብቻ ሳይሆን የመጠቀም አቅማቸው ማሳደግ አለባቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ስታየው የሳይበር አጠቃቀም ላይ አንድ ብዙ ተጠቃሚ የለም፡፡ ለምሳሌ የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያ ሳየው ከ100ሚ. የኢ/ያ ህዝብ 15ሚ. ብቻ ነው ተጠቃሚው፡፡ ይህ ማለት 15% አከባቢ ብቻ ነው ተጠቃሚው፡፡ በተነፃፃሪ ደግሞ በኬንያ ካየን ከ48ሚ. ህዝብ 43ሚ. ተጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ማለት 90% የኬንያ ህዝብ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ 4.5 ሚልየን ፌስቡክ የሚጠቀም ሲሆን፤ ለኬንያ ደግሞ 6 ሚልዮን የፌስቡክ ተጠቃሚ አለ፡፡ አሁን ያለው ትስስር (መስተጋብር) ያላደገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዕድገቱ ፈጣን ስለሆነ ትስስር ማደግ ይቀጥላል፡፡ ለምሳሌ በ2000 ዓ.ም አከባቢ 10,000 የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ነበሩ፤ አሁን ግን 16 ሚልዬን የሚጠጋ ህዝብ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ግን ሳይበር ለኢኮኖሚያዊ አቅም፣ አዳዲስ ሃሳቦች ለማምጣት የሚጠቀሙና ቢዝነስ የጀመሩ አሉ፡፡ በኢንድስትሪ ደረጃ ግን ገና ነው፡፡ ስለዚህ ሳይበር መሰረት ያደረገ ኢንዱስትሪላይዜሽን ሊመጣ ይገባል፡፡ ይህ ማለት ዕውቀት መሰረት ያደረገ ገበያ ማለት ነው፡፡ ዕውቀት ነው የሚሸጠው፤ ለምሳሌ ጎጉል ዕውቀት ነው፡፡ ጎጉልና ፌስቡክ በቢልዮን የሚገመት ዋጋ እንዲያወጡ ያደረጋቸው ዕውቀት እንጂ እንደ ነዳጅና ማዕድን የመሳሰሉ የድሮ ማተሪያል ካፒታል አይደለም፡፡ በቢልዮን እየተሸጠ ያለው ሃሳብ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ስታርች አፕ እየተባለ በቢልዬን ነው እየተሸጡ ያሉት፡፡ ስለዚህ በአገራችን ያለው ኢንዱስትሪ በዚህ መነፅ ስታየው ገና ያላደገና በውጭ የአለም- አቀፍ ተቋማት ጥገና ወይም ተላላኪና የሆነ ወይም ደግሞ በየቦታው የተበታተነና ያልተሳሰረ ነው፡፡

ስለዚህ እዚህ ላይ ለውጥ ካልመጣ ቅድም ያልከው በፌስቡክ ላይ የሚታየው መንጫጫት ሊቀየር ያስቸግራል፡፡ ለፖለቲካ የሚወሰነው ኢኮኖሚ ነው፡፡ ኢኮኖሚው ላይ ለውጥ ካልመጣ ፖለቲካው ላይ ለውጥ ማምጣት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስራ የሌለው ብዙ የተማረ ወጣት ነው ያለው፡፡ ስለዚህ አሁን ኢንተርኔት ሲያገኝ ለጭቅጭቅ ሊጠቀምበት ግድ ነው፡፡ ስለዚህ ፌስቡክ ላይ የሚታየው ዘረ መሰረት ያደረገ የተሳሳተ አካሄድ ወይም መጥፎ አጠቃቀምና ጭቅጭቅ የኢኮኖሚው ነባራዊ ሁኔታ ነፀብራቅ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የኛ ሳይበር በውጭ ጥገኝነትና ተፅዕኖ ስር ያለ ነው፡፡ በመሆኑም በራሳችን ዕድገትና ሃሳብ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ቋንቋችን የኢንተርኔት ቋንቋ አይደለም፡፡ ቋንቋችን፣ ትውፊቶቻችንና ባህላችን ኢንተርኔት ላይ ምንም ቦታ የለውም፡፡ ስለዚህ መለወጥ አለበት ማለት ነው፡፡

ውራይና፡- ሳይበር ምንድነው? የሳይበር ምህዳርስ ስንል ማለታችን ነው ? ተቋማችሁ ምንድን ነው የሚሰራው? የሳይበር ትስስር ምን ማለት ነው? ሳይበር ለቢዝነስና ስራ ፈጠራ    እንዴት ልናውለው እንችላለን? ከዚህ አንፃር የናንተ ፈንታ/ሚና ምን ሊሆን ይችላል?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ሳይበር የተለያየ ትርጉም ነው ያለው፡፡ ለኛ ሳይበር የምንለው ሶስት ነገሮች የሚያሟላ ነው፡፡ ማስተሳሰር፣ መስተጋብርና ግኑኝነት ነው፡፡ የሶስቱም ድምር ነው፡፡ መስተሳሰር ላይ የተመሰረተ ርክብ፤ ይግ ደግሞ የሚፈጥረው ግኑኝነት አለ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም መሰረተ ልማት ኮምፒዩተር ማዕከል ያደረገ ነው፡፡ ኮምፒዩተር ስንል ጠረጴዛ ላይ የምናስቀምጠው ዴስክቶፕ ብቻ ሳይሆን ቺፕስ ወይስ ዲጂታል ቴከረኖሎጂ ጭምር መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የማንኛውም መሰረተ ልማት ኢንነርጂ፣ ውሃ፣ ባቡር፣ ትራንስፖርትና ሚድያ ሁሉንም ኮምፒዩተር መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት አለም በፋይበር (ኢንተርኔት የምንለው) ተሳስሯል፡፡ ይህ ደግሞ የአሜሪካ ቢሆን ድርጅት ነው የተሰራው፡፡ ቻይናም ቢሆን one belt road (የአንድ መንገድ መቀነት) የሚባል ፕሮጀክት ነድፈው በራሳቸው መንገድ መሰረተ ልማቱ ለመዘርጋት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ መሰረተ ልማት አለ፡፡ ትላልቅ አለም አቀፍ የዳታ ማዕከላትም አሉ፡፡ ሳተላይት መሰረት ያደረጉ ትላቅ አለም አቀፍ ሚዲያዎች አሉ፡፡

ይህ በቀላሉ ልትገልፀው የማትችል የተወሳሰበ መሰረተ ልማት አለ፡፡ ይህን መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ሰፍትዌሮች፣ ህግ፣ ፕሮቶኮልና ስታንዳርድ አለ፡፡ ስለዚህ እነዚህም የመሰረተ ልማቱ አንድ አካል ናቸው፡፡ በእነዚህ ውስጥ ደግሞ መረጃ (ኢንፎርሜሽን አለ፡፡ መረጃ እንደ ደም ስር ነው የሚያገለግለው፡፡ ይህ ኢንፎርሜሽን የሚቀመጥ ወይም የሚከማች (stored) ነው፡፡ የሚቆጠሩ፣ የሚተነተኑና የሚያስተላልፉ ማጣሪያዎችና ቦታዎች አሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መስተጋብሩን የሚፈጥር ማህበረ-ሰብ አለ፡፡ የአገራችን አርሶ አደርና የአሜሪካ አርሶ አደር የሚፈጥሩት መስተጋብር አለ፡፡ የአገራችን አርሶ-አደር ከአሜሪካው አቻው እንዴት ይገናኛል ካልን ለምሳሌ የቡና ገበያ ከወሰድን በኒውዬርክ በሚገኝ የስቶክ ገበያ ነው የሚወሰነው፡፡ የአሜሪካ አርሶ አደር ሳይሆን አሜሪካ ናት የምትወስነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አርሶ አደሩ ለውጭ የሚልከው የስንዴ ምርት የሚወሰነው የምርት አይነት ጠይቆና ዋጋ አረጋግጦ ነው፡፡ አለም ይከታተላታል ማለት ነው፡፡ “በላዊ” መስተጋብር አለ፡፡ ስለዚህ ሳይበር የምንለው የትስስር፣ የመስተጋብር (interaction) እና የግንኙነት ድምር ነው፡፡

ውራይና ፡- ስለዚህ እንደ እኛ ባሉ ሃገራት ሉአላዊነት በቀላ ሊጣስ ይችላል?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ቀደም ሲል ሉአላዊነት ከዳር ድንበር ጋር ነበር የሚየያዘው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዳር ደንበሮች በሳይበር እየፈረሱ ነው ያሉት፡፡ ቢሆንም ሉአላዊነት የለም ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ህግ አውጥተህ አገር ማስተዳደር ራሱ ሉአላዊነት ነው፡፡ ውጣኔዎች የሚያሳልፍ የኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡ ህዝብም በምርጫ መንግስት ይመርጣል፡፡ ስለዚህ በድምሩ ሉአላዊነት ማለት የህዝብ መብት ማረጋገጥ ነው፡፡ የህዝብ መብትና ፍላጎት ማሟላት ነው፡፡ ቢሆንም ይህንን ሁኔታ የሚፈታተኑ ነገሮች ናቸው አሁን እየተፈጠሩ ያሉት፡፡ ለምሳሌ አንድ የውጭ አገር የሆነ ዜጋ አንድ ላፕቶፕና የኢንተርኔት ኮኔክሽን ተጠቅሞ አገር ውስጥ ያለውን ሃይል በተዛባ መረጃ ነውና ውስጥ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

ይህ ሳይበር የጥፋት መሳሪያ አድርጎ መጠቀምን ነው የምናሳየው፡፡ ይህ ሉአላዊነት መጋፋት ነው፡፡ አሁን በህዝብ የተመረጠ መንግስት ነው ያለው፤ በአንፃሩ ደግሞ ፀረ-ህዝብ የሆነ ሃይል ይህ በህዝብ የተመረጠ መንግስት በነውጥ ለመቀየር ሙከራ ያደርጋል፡፡ የሉአላዊነት ትርጉም ሰፊ ነው፡፡ አሁን ዳር-ድንበር የመቆጣጠር አቅም ነበረን፡፡ ሳይበር ከማስተዳደር አንፃር ድንበራችን እስከየት ድረስ ነው፤ ድንበራችንስ እንዴት እንከላከለው የሚሉት ጉዳዮች አስቸጋሪ ናቸው፡፡ ድንበር ላይ ወይም አውሮፕላን ማረፍያ ሆነህ የህዝብ ፍሰት እንቆጣጠረው ነበር፡፡ የዕቃዎች ፍሰት በተመለከተም በጉምሩክ አማካኝነት ልትቆጣጠረው ትችላለህ? መረጃ ቪዛ የለም፤ ወይም ደግሞ የጉምሩክ ሂደት የሚከተል አይደለም፡፡ የራሱ የሆነ ሂደት የሚከተል ነው፡፡

ስለዚህ ተቋማችን አገራችን የራሷ ሳይበር እንዲኖራት ነው የሚሰራው፡፡ ቅርፅ ያለው ሳይበር ልታስተዳድረው ትችላለህ፡፡ ከሌሎች ጋርማ ልትደራደር ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ከዓለም ጋር ለመተሳሰር የሚያስችል ሳይበር መገንባት ስለሚያስፈልግ፤ የሳይበር ህግና ፖሊሲ እንዲኖረንና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ በዩኒቨርስቲዎች ስርዓተ- ትምህርት እንዲካተት ይሰራል፡፡ በዚህም በስትራተጂ ደረጃ ትስስር እንዲኖረን ይሆናል፡፡ የመከላከል አቅማችን ለማሳደግ ደግሞ የተማረ የሰው ሃይል እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር ደግሞ የተነቃቃ ባለሀብት እንዲኖረን ይረዳል፡፡ የሳይበር ጥቃት ለመከላከልና የኢንዱስትሪ ትስስር ለመፍጠር በተለይም በሳይበር ጥቃቶች ላይ የሚያጠነጥኑ ጥናቶች በአገር ውስጥ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ የአገር ውስጥ ገበያም እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ስለዚህ እዚህ ጋር መሰራች ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ እየተፈጠረ ያለው የሳይበር ጥቃት መከላከል የሚችል የሰው ሃይል ማፍራት ተቋማችን ጥረት ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ተቋማችን ብቻውን የሚናደርገው ሳይሆን ሃገራዊ የሆነ ትስስር በመፍጠር ነው፡፡

ውራይና፡- አንተ እንዳልከው አንድ ሰው ውጭ አገር ሆኖ ማህበራዊ ሚድያ በመጠቀም ኢትዮጵያን የሚጎዳ ወይም ማህበራዊ ሚድያውን የሚበክል ነገር ሊፅፍ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ጎጂ ስለሆነው መረጃ አይደለም የምናወራስ፡፡ እሱ ጥሩ ነው፡፡ መጥፎ/አጥፊ ስለሆነው ፅሁፍ ነው የምናወራው፡፡ ምክንያት የተሳሳተ መረጃ ነው ሰው እያዛባ ያለው፡፡ በመሰረቱ የሃገር ጥቅም ግምት ውስጥ ያስገባ ሳይሆን በሌሎች ሃሎች የመንቀሳቀስ ዝንባሌዎች ናቸው እየታዩ ያሉት፡፡ ስለዚህ እዚች አገር ምን ሊደረግ ይችላል? ይህ ጉዳይ በጣም ከባድ ነው፡፡ የእናንተ ተቋም ትክክለኛ ያልሆነ መረጃዎችን የሚያጠራበት ወይም ደግሞ የሚከታተልበት ህጋዊ ማዕቀፍ አለ ወይ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- መልካም ይህ የሳይበር አማካኝነት እየተፈጠረ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ እንዴት እንከላከል የሚለው ነው፡፡ ይህ በዋናነት የማህበረሰቡ ንቃት ነው የሚወሰነው፡፡ የማህበረሰቡ ንቃት ካደገ ነው መከላከል የምንችለው፡፡ ንቃት ማለት ደግሞ ይህ የመረጃ መረብ ራሱ ማለት ነው፡፡ በሆነ አጋጣሚ ወደ ቢዝነስ ወይም አወንታዊ የማህበረሰብ ግኑኝነት መቀየር ይቻላል፡፡ በተለይ የተማረው ሃይል እንደ መልካም ዕድል ወስዶ ወደ ራሱ ጥቅም ሊቀይረው ይገባል፡፡ አሁን ግን ማለፍ የሚገባን ነገር አለ፡፡ ማህበራዊ ሚድያ አዲስ ክስተት ነው፡፡ ህብረተሰባችን ደግሞ ለዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ሊለምደው ይገባል፡፡ ሊለማመደው ከሆነ ደግሞ ክፍት መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ደግሞ መንግስት በቴሌኮሙኒኬሽን ዝርጋታ በንቃት እየሰራ ከሚገኘው፡፡

ለጊዜው ግን ችግሮች ሊኖሩ ግድ ነው፡፡ ዋናው ችግር ማህበራዊ ሚዲያ ሳይሆን ሌላ አካል ነው፡፡ስለዚህ ዋና ችግር በሆነው ላይ ነው መስራት ያለብህ፡፡ ኢንተርኔት ላይ እየታየ ያለው ችግር የማህበራዊ ሚድያ ችግር አይደለም፡፡ አንዱ የማህበረሰባችን የአጠቃቀም ንቃት ችግር ነው፡፡ ሌላው ደግሞ መንግስት በተቋማቱ አማካኝነት የሚወስዳቸው እርምጃዎች አሉ፡፡ የኮምፒዩተር አዋጅ አለ፡፡ የኮምፒዩተር አጠቃቀም እንደፈለገኸው አይደለም፡፡ ከአግባብ ውጭ መጠቀም እንደሚያስቀጣ የሳይበር ህጉ አስቀምጧል፡፡ የተለያዩ አካላትም የራሳቸው ሚና አላቸው፤ ለምሳሌ እንደ ፌደራል ፖሊስ፣ ዓቃቢ-ህግ ወዘተ የመሳሰሉትን፡፡

ውራይና፡-  የሳይበር /ኮምፒዩተር ህግ ስንል ምን ማለት ነው?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- የኮምፒዩተር /ሳይበር አዋጅ ከወጣ ሁለት አመት ሆኖታል፡፡ ኮምፒዩተር መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የሰዎች ማንነት መስረቅ፣ በሚስጢር የሚጠበቅ መረጃ መስረቅ፣ የሰዎች መልካም ስም መስረቅ፣ ዘር መሰረት ያደረገ የማባስና የማጥቃት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዬች እንደ ወንጀል ተካተዋል፡፡ ኮምፒዩተር እንዳሻህ የምትጠቀምበት ሳይሆን፤ ተጠያቂነትም እንዳለውና በህግ እንደምትጠየቅበት በመሆኑም ማህበረሰቡ ህጉ ማወቅ አለበት፡፡ ችግር በሚገጥመው ጊዜ ወደ ሚመለከተው አካል አቤቱታውን ማቅረብ አለበት፡፡

ስለዚህ አንደኛው ህጉ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ይህን ህግ የማስፈፀም አቅም ነው፡፡ ፖሊስ የመመርመር ብቃት ሊኖረው ይገባል፡፡ የዲጂታል ምርመራ ለመገንባ ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡ መንግስትም በጀት መድቦ እየሰራበት የሚገኝ ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አገራዊ ደህነት አደጋ ውስጥ የሚከቱ አሉ፡፡ ቅድም እንዳልከው ዕቅድ አቅደው ከውጭ ፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር ተባብረውን የስነ ልቦና ጦርነት የከፈቱብን አሉ፡፡ ይህ ለመከላከል በመሰረታዊነት የነቃ ህ/ሰብ መፍጠር፤ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ችግሮች የሚከላከልበት የመንግስት አቅም መገንባት ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ሰአት እንደነ ኢንሳ የመሳሰሉ ተቋማት ድርሻቸው መጫወት አለባቸው፤ እየተጫወቱም ነው፡፡

ውራይና፡- በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ቀውሶች፣ አመፆችና ቅሬታዎች አሉ፡፡ በተለይ ከ 2008 ዓ.ም ጀምሮ አንዱን ስታክመው፤ በሌላ በኩል የማገርሸት ሁኔታዎች ይታያሉ፡፡ የወጣቶች እንቅስቀሴዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የህዝቡ ጥያቄዎች ናቸው ልትል ትችላለህ፡፡ ቢሆንም ሰዎች የሚረብሹ ሁኔታዎች ናቸው ያሉት፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ታውጆ ነበር፡፡ እውነተኛ የችግሮቹ መነሻ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የነዚህ ችግሮች መዋቅራዊ መንስኤዎች ምንድ ናቸው ትላለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- አንድ ምንጭ አይደለም ያለው፡፡ በውስብስብ ፅንሰ-ሃሳብ (complex theory) ነው መታየት ያለበት፡፡ አንድ መንስኤ መርጠህ ለማውጣት መሞከር ከንቱ ነው፡፡ ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ፣ ቴክኖሎጂካዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ትስስር ነው ሊታይ የሚገባው እጅግ የተወሳሰበና ብዙ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ ተደርጎም ሊታሰብ አይገባም፡፡ ሌላው ኢትዮጵያ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለችው የሚለውን ጉዳይም መታየት አለበት፡፡ ኢትዮጵያ በሽግግር ላይ ያለች ሃገር ነች፡፡

የትኛውም በሽግግር ውስጥ ያለ አገር የሚያጋጥመው ችግሮችና ፈተናዎች አሉ፡፡ መሰረታዊ የስርዓት ለውጥ ነው የተካሄደው፡፡ ካለፈው ስርዓት እጅግ የተለየ ስርዓት ነው በኢትዮጵያ የተተከለው፡፡ ይህ በእኩልነት የተመሰረተ አዲስ የፌደራሊዝም ስርዓት ነው፤ ይህ ደግሞ ገና መሰረት መያዝ ያስፈልገዋል፡፡ ቀደም ሲል አገር በሚመነጭ ስልጣን ነው አገሪቱ የምትትዳደረው፡፡ ስልጣን ከገዥው መደብ ነበር የሚመነጨው፡፡ አሁን ግን ስልጣን ከህዝብ ነው የሚመነጨው፡፡ ለብዙ ዘመናት ስልጣን ከንጉሱ ወይም ከማዕከላዊ መንግስት በሚመነጭ ስልጣን የምትመራ ሃገር ነው የነበረችው፡፡ በሁለቱም መካከል ደግሞ ግጭት አለ፡፡ ስለዚህ የስርዓት ግጭት አለ የሚል አመለካከት ነው ያለን፡፡

በአንድ በኩል አዲሱ ስርዓት ስር ሊሰድ/መሰረት ሊይዝ ይፈልጋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ አሮጌው ስርዓት አዲሱ ስርዓት እንደማይሰራለማረጋገጥ እንቅፋት መፍጠር አለበት፡፡ የድሮ ስርዓት ጠቅልሎእንዲጠፋ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ጊዜው የአዲሱ ስርዓት መሰረተ-ልማት /መዋቅሮች የሚፈትኑበት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ደረጃ ነው ማየት ያለብን፡፡ በሶስተኛ ደረጃ መታየት ያለበት ደግሞ እየተፈጠረ ያለው አዳዲስ ፍላጎቶች ናቸው፡፡ በርግጥ የድሮውን ስርዓት ለማስቀጠል ሲሆን ይችላል፡፡ ወይም በሌላ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ በኒዮሊበራል አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለው መንገድ አዋጪ አይደለም የሚል አቋም የያዘ ይህን ለመግጠም የተዘጋጀ ሃይል ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከውስጣቸው የሚመነጭ ሌሎች ፍላጎቶች አሉ፤ የብዙ የማህበረሰብ አካላት ፍላጎቶች መስተጋብር ስለሆነ፡፡

ሽግግር  በተለያዩ መስኮች ማለትም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማንነታዊ፣ ቴክኖሎጂካዊ፣ ታሪክ እና ወዘተ አለ፡፡ ለምሳሌ ማህበራዊ ሽግግር የወሰድክ እንደሆንክ የት/ት መስፋፋት የፈጠረው ብዙ የተማረ የሰው ሃይል አለ፡፡ የስራ ፈጠራ አቅም ማደግ አለበት፡፡ የስራ ፈጠራ አቅም ስለሌለ ደግሞ አብዛኛው ጠባቂ ነው፡፡ አሁን ከድሮው መዋቅር ጋር እንዴት እንደሚጋጭ እንየው፡፡ የነበረው አካሄድ በመንግስት ተቀጥሮ መስራት፤ ግን ደግሞ የተማረው የሰው ሃይል በቁጥር እጅግ አነስተኛ ነበር፡፡ ኢኮኖሚውም ቢሆን መሃል አገር ነበር የሚገኘው፡፡ ያየቆየው ስነ ልቦና አሁንም አልተቀየረም፡፡ መንግስት ስራ እንዲቀጥረው ነው የሚጠብቀው፡፡ በሌላ በኩል አዲሱ ስርዓት የሰራው ነገር የሰውን አቅም ማሳደግ ነው፡፡

አዲሱ ስርዓት ራሱን የቻለ፣ ነፃ ሆኖ ሃብት የሚፈጥርለት ወጣት ነው የሚጠብቀው፡፡ በመሆኑም እዚህ ላይ ግጭት አለ፡፡  በርግፅ ወጣቱ ራሱ እንዲችልና አቅም እንዲፈጥር ከተፈለገ መንግስት በፖሊሲ የጠደገፈ ፕሮግራም ማውጣትን ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ይገበዋል፡፡ ስለዚህ እዚህ ላይ የጨነቀው (suffocated) ሃይል እየፈጠረ ነው፡፡ መሬት አግኝቶ መሬት መሰረት ያደረገ ምርት ማምረት የሚችል አይደለም፤ አልያም ኢንዱስትሪ መግባት አልቻለም፡፡ ወይም ደግሞ እንደ ሌሎች የበለፀጉ ማ/ሰብ የራሱን ስራ ፈጥሮ ከመንግስት ሳይጠብቅ መስራት አልቻለም፡፡ ስለዚህ በት/ት ያለፈ በቂ የሰው ሃይል በተመሳሳይ ሁኔታ አለ፡፡ አሁን ይህ ሃይል ወደ ተጨባጭ አቅም የመለወጥ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጥፋት ብቻ ሳይሆን ዕድልም ጭምር ነው፡፡ እንደ ዕድል መጠቀም የሚችል የመንግስት መዋቅር ሊኖር ይገባል፡፡ የሚመራ ማለቴ ነው፡፡ ይህ የመላው ኢትዮጵያ ችግር ነው፡፡ ብሄር ይሁን ዘር መሰረት አያደርግም፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳችን የሆነ ቦታ ሄደን እንንጫጫለን፡፡

ማህበራዊ ለውጦች እየታዩ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል መሬት ላይ ተተክሎ የሚሰራ አምራች አርሶ አደር ነበር፡፡ ከተማ ውስጥም ነጋዴ የሚባል የከተማ ኗሪ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከገጠር የመጣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአርሶ አደር የተማረ ልጅ አለ፡፡ ይህ ሁሉ  ለውጥ ባለው መዋቅር የሚሄድ አይደለም፡፡ ግንኙነቶችም እየተቀየሩ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ኢኮኖሚው ከግብር የወጣ አይደለም፤ ግብርናውም ዘመናዊ አልሆነም፡፡ መሬቷ ደግሞ በነበሩ አርሶ አደር ተይዟል፡፡ መሬት የተቆጣጠረው አርሶ አደሩ ነው፡፡ አዲስ እየተፈጠረ የሰው ሃይል ደግሞ አለ፡፡ መሬቱ ደግሞ ሁሉንም ማስተናገድ አይቻልም፡፡ ስለዚ ይህ እየተሰደተ ያለው መጣት መሸከም የሚችል እንደ ኢንዱስትሪ የመሰሉ የኢኮኖሚ መሰረተ-ልማቶች የለም፡፡ ወይም ደግሞ ከመሬቱ ሳይነቀል እዛ እያሉ ወደ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገርበት ሁኔታ መፍጠር አስቸጋሪ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ታሪክና ማንነት አለ፡፡ አንዱ ትልቁ ችግር የኢ/ያ ታሪክ በትክክል አልተፃፈም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚመለከት ታሪክ አልተፃፈም፡፡ ታሪክ አትቀይረውም፤ አትጨምርለትም፤ ታሪክ እውነት ነው፡፡ ስለዚ እውነት ላይ መሰረት ያደረገ ታሪክ የለም፡፡ የተለያዩ ሃሳብ ነው ያለው፡፡ ታሪክ እንደገና ለመፃፍ እንቅስቃሴዎች አሉ፡፡ ታሪክ ለመፃፍ ፍላጎት የሚያሳያዩ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች አሉ፡፡ የፖለቲካ ፍላጎቶች ታሪክ በማዛባት ማሟላት የሚፈልጉ አሉ፡፡ እዚህ ጋ የተለያዩ ግችቶች (ልዩነቶች) አሉ፡፡ የቀውስ አይነት ዝንባሌዎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ የሚመጣ ተፅዕኖ አለ፡፡

ውራይና፡- ታሪክ ላይ ያነሳኸው ጉዳይ፤ በእኔ እይታ የተፃፈ ታሪክ አለ፡፡ የተፃፈው ታሪክ የተዛባ መሆኑ አንዱ ችግር ሆኖ፤ ይህ ግን ሃቁ እንዲታወቅ በማድረግ እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ የመገንባት ሂደት መሰረት ያደረገ ታሪክ ብታይ በእውነት የህዝቦች አስተዋፅኦ ይለያያል፡፡ በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ተመሳሳይ አስተዋፅኦ አልነበረም፡፡ ቀደም ሲል ያነሳኸው የስርዓት ለውጥ፤ አሁንም ይወክለኛል የሚል የሕ/ሰብ ክፍል አለ፤ ሌላው ግን እንደማይመለከተው ነው የሚታስበው፡፡ አሁን ግን በአገር ግንባታ ላይ ሁሉም እኩል አስተዋፅኦ አለው፡፡ ታሪክ እየተነሳ ግን አሁንም ኢትዮጵያ እኩል እንድናያት ያደርጋል፡፡ ኢኮኖሚ ያነሳኸው ላይ መሬት የማይለወጥ ቢሆንም እሴት (value) የሚጨምር ነው፡፡ ይህ ግን አልተደረገም፡፡ አርሶ በሚበላ አርሶ አደርና የመንግስት ስልጣን በያዘው አካል መካከልም የጥቅም ግጭቶች አሉ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች እንዴት ማስተካከል ይቻላል?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡-  ያለፈው ታሪክ የኢ/ያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ግኑኝነት የሚያዛባ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን በተለያዩ አተያዮች እንድትታይ ያደረገ ነው፡፡ ይህ የታሪካችን አካል ነው፡፡ አሁን ያለው ህገ መንግስት የመጣው ይህን የተዛባ ግንኙነት ለማስተካከል ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ተቀባይነት ሊያገኝ ከሆነ ሂደቶች ያስፈልጉታል፡፡ በተግባር ሊፈተን ይገባል፡፡ የአዲሱ ግንኙነት ተቀባይነት በተግባር እየተፈተነ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ቀደም ብዬ እንዳልኩት በስርዓቶች መካከል ያለ ትግል ነው፡፡ በኢኮኖሚ ዘርፍም ቢሆን በተመሳሳይ ሁኔታ እየተፈተነ ነው፡፡ ይህ የሰው -ሃብት ነው የፈጠረው፡፡ ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሃብት እንዲያፈሩና ያላቸውም ሃብት እንዲጠቀሙ የሚፈቅድ ስርዓት ነው፡፡ ግን እሴት ሊጨምሩ ይገባል፡፡ ይህ መሬትን መሰረት ያደረገ የኢኮኖሚ ስርዓት ሳይሆን ወደ ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ሊሸጋገሩ ይገባል፡፡ አሁን ያለው አዙሪት ግን ከመሬት የሚያወጣ አይደለም፡፡ መሬቱም ቢሆን እሴት ሳትጨምር የምታመርት ከሆነ የስርዓት ሽግግር አልተደረገም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሃይሎች በስልጣን ካለ አካል ጋር በመመሳጠር የሚያደርጉት ግንኙነት የኪራይ ሰብሳቢነት ግኑኝነት ነው፡፡ እሴት ሳይጨመር መሬት በመሸጥና በመለወጥ ሃብት የሰበሰበ ሃይል አሉ፡፡

አሁን ባለው ኢኮኖሚ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እሴት የሚፈጠርበት ዕድገት ካልተፈጠረ ወይም ደግሞ ወደ ሌላ ኢኮኖሚ የሚሸጋገርበት ሁኔታ ካልተፈጠረና በነበረችው ኢኮኖሚ ወይም ተፈጥሮ በሰጠችህ ሃብ መሰረት ያደረገ ሂወት ካለህ ጉዳዩ ማን ሰፊ፣ የለማ ዌም ማዕድን ያለው መሬት አለው ወደሚል ነው የምንሄደው፡፡ ይህ ደግሞ አላስፈላጊ ውድድር (whataboutism) ነው የሚመጣው ይህ ደግሞ የእኔነትን ያመጣል፡፡ የሃብት እጥረትና የእጥረት ባለበት ሁኔታ ውድድር ያለነው፡፡ ይህ ተከትሎ ደግሞ ሌላውን በመጤነት የመፈረጅ፣ እነሱና እኛ የሚል ነገር ያመጣል፤ ግጭት ማንሳቱም ግድ ነው፡፡ ይህ የዕድገቱ ውጤት ነው የሚሆነው፡፡ ዘሮ ዘሮ ኢኮኖሚውን የሚመለከት ነው የሚመስለኝ፡፡

ፖለቲካውን በሚመለከት ቅድም እንዳልኩህ ህገ-መንግስቱ አዲስ የህዝብ ግንኝነቶች ፈጥሯል፡፡ ይህ በተግባር ሲውል መውደቅና መነሳት ይኖራል፡፡ ይህ ጠንካራ አመራር ያስፈልገዋል፡፡ በአመራር የሚፈጠር ችግርም አለ፡፡ ስለዚህ ችግሩ ውስብስባን የብዙ ምክንያቶች ውጤት ነው፡፡ ወደ አመራር ስንመጣ፤ አሁን ያለው ችግር የህገ-መንግስት የፖሊሲና ስትራቴጂ ችግር አይደለም፡፡ በዋናነት ለዚህ ችግር በባለቤትነት የሚወሰድ አመራር ሊኖር ይገባል፡፡ ይህ አመራር ደግሞ ለህዝብ ጥቅም የወገነ ሊሆን ይገባል፡፡ ሁልጊዜ በመንስትና በፓርቲ ያለ አመራር የራሱ ፍላጎቶችና ጥቅሞች ያሉት ናቸው፡፡

ስለዚህ ልክ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንዳለው በአገራችንም አለ፡፡ ይህ ንኡስ የምሁር ከበርቴ የኢኮኖሚ መሰረቱ እርሻም ኢንዱስትሪም አይደለም፡፡ አሊት (elite) ስለሆነ ገዢ የመሆንና ሃብት ተቆጣጥሮ የመያዝ ፍላጎት ነው ያለው፡፡ ይህ ፍላጎት ሁልጊዜ ያለና የሚኖር ነው፡፡ ስለዚ አመራር ስንል ይህን ፍላጎት የሚቆጣጠር፣ ለህዝብ የወገነ፣ ለህዝብ ጥቅም የማይክድ፣ የሚክድ ሃይል ሲኖር ደግሞ ይህንን የሚታገል፣ ፖሊስዎች ለማስፈፀም የሚሰዋ አመራር ማለታችን ነው፡፡ ቢሮክራሲውም አዲስ አይደለም፡፡ በድሮው ቢሮክራሲ ውስጥ ነው የምትሰራው፡፡ ከፀጥታ ውጭ ያለው የመንግስት መዋቅርና ቢሮክራሲ እንዳለ ነው የቀጠለው፡፡ በአዳዲሶቹ ክልሎች ሳይቀር የፈጠሩት ቢሮክራሲ ከቀድሞው ማዕከላዊ መንግስት ቢሮክራሲ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለዚህ በሂደት የሚገነባ አዲስ ቢሮክራሲ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ አሁን እያስቸገረ ያለው የተለያየ ፍላጎት ያለው ነው፡፡ ቀደም ብለን ያስቀመጥናቸው ችግሮችና ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው፡፡ አሁን ካለንበት ሁኔታ ነቅለን ወደ ሌላ ለመሸጋገር ደግሞ አመራር ያስፈልገዋል፡፡ አመራሩ ደግሞ አንዳንድ እየተፈጠሩ ያሉት ለውጦች የሚያሳዩት ነው፡፡ ስለዚህ የውድድር ፍላጎት ማደጉ ባህሪያዊ ነው፡፡ የተፈጥሮ ሃብት መጠቀም ወይም ኪራይ ሰብሳቢነት ባህሪያዊ ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች እንደሚገጥሙን ተለይተውም ነበር፡፡ ስለዚህ ፈተናው ይህ ለህዝብ የወገነ ሃይል በመደራጀት ማሸነፍ አለበት፤ እነዚህ ችግሮችም መቅረፍ ይኖርበታል፡፡ ልዕልናው ማረጋገጥ አለበት፡፡ በአስተሳሰብና በተግባር ልዕልና ሊኖረው ይገባል፡፡ ልዕልና ስለነበረው ነው ለውጦች ሲመዘገቡ የመጡት፡፡

አሁን እየፈተነን ያለው ጥያቄ ልዕልናው እንዴት ይቀጥል የሚለው ነው፡፡ በስልጣን ያለው አካል እኮ ብዙ የሚያጎመጁት ነገሮች አሉ፡፡ እኔ በሰራሁት ሌሎች ሃብታም እየሆኑ ስለሆነ እኔም ሼር ልግባ የሚሉ አሉ፡፡ እየተፈጠረ ባለው አዲስ የካፒታሊዝም ስርዓት ተቋዳሽ እንዲሆን ግን ቦታው አይፈቅድለትም፡፡ መሰረት አለበት፡፡ ይህንን የካደ ስልጣን ለግል ጥቅሙ የሚያውል ነው፡፡ በሌላ በኩል የተፈጠረ ሃብት አለ፡፡ ይህ ሃብት በማኒፋክቸሪንግ ወይም በአግሮ ኢንዱስትሪ የመጣ አይደለም፡፡ በርግጥ ሰርቶ ሃብታም የሆነ አለ፡፡ ብዙ ሃብት ደግሞ ቀደም ብለን እንዳልነው ከመሬት ጋር በተያያዘ ወይም ጤናማ የንግድ ስርዓት ባለመኖሩ ምክንያት በአቋራጭ የተፈጠረ ነው፡፡ እዚህ ላይ ፍትሃዊ የሃብት ተጠቃሚነት ጥያቄ አለ፡፡ በዚህ ጥያቄ ምክንያት የተፈጠረ ቀውስ አለ፡፡ ጋደኛህ ሳይሰራ በአጭር ጊዜ ሃብታም ሆኖ ስታይም ምንድ ነው አእምሮህ የሚመጣብህ? ስለዚ ስልጣን የያዘው በህገወጥ መንገድ ሃብት የሚያፈራው ውስጥ እጁ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ ይህ ዓይነት መተሳሰር (network) የሚፈጥረው ዕንቅፋት አለ፡፡ ስለዚህ አሁን እየተፈጠረ ያለው ችግር የብዙ ምክንያቶች ድምር ውጤት ነው የሚል ሃሳብ ነው ያለኝ፡፡

ውራይና፡- ቅድም ስላነሳኸው የቢሮክራሲ ጉዳይ እመለስበታለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን ማሳያችን ለራሳችን ልናየው የሚገባው ዕውቀት መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚ በመሬት ላይ ወይም በሌላ ሊሰራ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የተማረ የሰው ሃይል ትኩረት የሚያደርግ ነው፡፡ ቁሳዊ ለውጥ ብቻ ሳይሆን የሰው አእምሮ ላይ መስራት የሚገባው ስራ ነበር፡፡ መጀመሪያ የሰው ሃይል ማልማት ላይ ያለህ አቋም፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ደግሞ አሁን እየተሄደበት እና መኬድ ያለበት መንገድ ላይ ያለህ ሃሳብህስ ምን ይመስላል?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡-  ዕውቀት መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚ ስንል እሴት ጨምረህ ሃብት ማካበት ወይም ባለሃብት መሆን ማለት ነው፡፡ ከአሁን በፊት ትልቅ የሚባለው ሃብት ካፒታል ነበር፡፡ ከዛ ጉልበት አለ፡፡ ሌላው ደግሞ እንደ መሬትና ማዕድን ያሉ ጥሬ ዕቃዎች /ሃብቶች ናቸው፡፡ አሁን ግን በአለም ላይ እነዚህ ብቻቸውን ወሳኝ አይደለም፡፡ ለምሳሌ የነዳጅ ቦታ በኤሌክትሪክ እየተተካ ነው፡፡ በነዳጅ የሚሰራ መኪና ወይም ባቡር በኤሌክትሪክ እየተተካ ነው፡፡ ኤሌክትሪክ ደግሞ ከውሃ፣ ፅሃይና ንፋስ እየመነጨ ነው፡፡ ስለዚህ ነዳጅ በነበረው ቦታና ዋጋ እየተተካ ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ አጠቃላይ ጅኦ-ፖለቲካውን የሚቀይር ነው፡፡ ነዳጅ የሚያመርቱ ሃገራት ሌላ አማራጭ ካላመጡ የሚፈጥሩት ቀውስ አለ፡፡

አጋጣሚ ሆኖ እኛ የገነባነው ኢኮኖሚ የተፈጥሮ ሃብ መሰረት ያደረገ አይደለም፡፡ ያረጋገጥነው ዕድገት መሬትና ጉልበት መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይህ አንድ ጥንካሬ ነው፡፡ ኢኮኖሚያችን ጠንካራ መሰረት እንዲኖረው የሚያደርግ ነው፡፡ መሰረቱ ተዘርግቷል ማለት ነው፡፡ ዋናው ነገር አሁን ዕውቀት ነው የሚያስፈልገው፡፡ ካፒታል የሚፈጥር ዕውቀት ነው፡፡ ዕውቀት ከሃሳብ ነው የሚጀምረው፡፡ በሃገራችን መፈታት ያለባቸው አያሌ ችግሮች አሉ፡፡ ችግራችን ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ብዙ የፈጠራ ስራዎች ሊመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ፈጠራዎች ማንቀሳቀስ የሚችል ስርዓት ግን ያስፈልጋል፡፡ ፈጠራዎች ወደ ገበያ ሊወጡ፣ ሊገዙ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ብሉውን በሚባል ፕሮጀክት የእርሻ የፈጠራ ስራ ሰምቻለሁ፡፡ ሃሳቡ ወደ ገበያ ቀርቦ፤ ሃሳብ ደግሞ ወደ ቢዝነስ፣ ወደ ማኒፋክቸሪንግ ይቀየራል ብለው የሚያስቡ ገንዘብ ያለችው ሰዎች ደግሞ ይገዙታል፡፡

ይህ በካፒታልና በሃሳብ መካከል ያለው መስተጋብር ነው የሚያሳየው፡፡ በዓላማችን ያሉት ቢልዮነሮች ካየን መጀመሪያ ተማሪዎች ናቸው የነበሩት፤ ቢልዮነሮች አልነበሩም፡፡ አሊበባ የሚባለው የኤሌክቶሪኒክስ ገበያም በተመሳሳይ፡፡ ስለዚ ገበያ የምትፈጥረው ሃሳብ ይዘህ እንጂ ካፒታል ይዘህ አይደለም፡፡ ስለዚህ ዕውቀት ስንል ሃሳብና ፈጠራ ማለታችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ውስጣሚ ነው፡፡ የአከባቢህ ችግር የመፍታት ክህሎት ነው፡፡ አከባቢህን መሰረት በማድረግ መመራመርና ችግሮችህ መፍታት ማለት ነው፡፡ ስትወስን ደግሞ መረጃን ጥሬ-ሃቁን መሰረት በማድረግ መወሰን፡፡ ይህም ቢሆን ልፋት አለው፡፡ ተምረህ ግን እሴት የማትጨምርበት ገበያ ወይም ሃገር በሚሆንበት ወቅት ሁለት ተፃራሪ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ በቀላ መሬት እየሸጠና እየለወጠ ወይም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተሰማርቶ ሃብት የሚያካብት ሰው እያየህ ከፍተኛ ጥረት ወደ ሚፈልገው የሃብት ፈጠራ ሂደት መግባት ያስቸግረዋል፡፡ ይህ ነው ፈተናው፡፡

ውራይና፡- ቀጥሎ ያለው ችግር ቢሮክራሲ የምንለው ነው፡፡ አሁን ያለው ቢሮክራሲ የቀድሞውን ስርዓት መዋቅር የሚጠቀም ነው፡፡ ይህ አዲሱ ቢሮክራሲ ወደ ኋላ የማየት ሸክም ያለው ነው፡፡ ሁለተኛ የአቅም ችግር ያለው ነው፡፡ ከመሬትና ሜሪቶክራሲ ጋር የተያያዙ ጉዳይ ነው፡፡ መቀየር ያለበት ጉዳይ አለ፡፡ የኔ ጥያቄ መሬት የሚባለው ምንድ ነው? ከመሬት ጋር በተያያዘ የኛ ጉዳይ ምንድ ነው? አሁን ያለው ሁኔታ መሬት የሚባል ነገር የለውም፤ የየራስህን ሰው የመሳብ ሁኔታ አለ፡፡ ግልፅ የሆነ የመሬት መለኪያ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ያለህ ሃሳብ ምን ይመስላል?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ትክክል ነው፡፡ መሬት ዝም ተብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡ መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ አንደኛው ሁኔታ ሜሪቶክራሲን መምራትና መስራት የሚችል ቆራጥ መንግስት ያስፈልጋል፡፡ ሌላው ደግሞ አሁን ላለው ማህበራዊ ቅርፅ የሚመች መሆን አለበት፡፡ ማህበራዊ ቅርፅ ሲባል ለምሳሌ በቋንቋ፣ በባህል፣ በታሪክና በትውፊት አንድ የሆነ ማህበረሰብ አለ፡፡ ቻይና ከወሰድክ ከ90% በላይ ህዝብ ሃን የሚባለው ነው፡፡ ኮርያ ከወሰድክ ደግሞ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህልና አንድ ታሪክ ያለው ህዝብ ነው፡፡ አሁን እነዚህ ጋር ሜሪቶክራሲ ስርዓት ለመገንባት ቀላል ነው፡፡ ብዙ ቋንቋና ባህል ባለው ማህበረሰብ ግን መሳሳብ ሊኖር ይችላል፡፡ ቢዝነስ ለማቋቋም ስታስብ እኳ ቤተሰብ ነው የምትቀጥረው፡፡ ማህበራዊ ሁኔታ አንድ ምክንያት ነው፡፡ በኢ/ያ ብዙ ቋንቋና ባህል አለ፡፡ ልንቀበለው የሚገባና መስተናገድ ያለበት፡፡ ብዝሃነት ዕድል ነው፡፡ ይሁን እንጂ የተዛባ የታሪክ ግንኙነት ስላለን የእኔ ብሄር ተበደለ የሚል አስተሳሰብ ሊኖር ይችላል፡፡

ሶስተኛው ሁኔታ ገበያ ነው፡፡ ገበያ ስንል ብሄርን መሰረት ያደረገ አይደለም፤ የብሄር አጥር የሚያፈርስ ነው፡፡ ምክንያቱም ገበያ ስንል በተከፋፈለው ማህበረሰብ መካከል ውህደት ተፈጥሯል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች እንደፈለጉት ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱበትና ባፈሩት ወይም ባበረከቱት ልክ እሴት የሚለዋወጡበት ማለት ነው፡፡ የቋንቋ፣ ባህልና ጂኦግራፊ አጥሮች ፈርሰዋል ማለት ነው፡፡ ገበያ በውድድር ነው የሚያምነው፡፡ ማን ምን አይነት እሴት አቀረበ ነው ጥያቄው፡፡ስለዚህ የዕውቀት ገበያ ጭምር ነው የሚኖረው፡፡ ወደ ቢሮክራሲ የሚገባው ከገበያ ነው የሚገኘው፡፡ ስለዚህ ቢሮክራሲ ዕውቀት ላይ መሰረት አድርጎ መ፣ን ለዚህ ስራ ይመቻል፤ ይመጥናል ብለህ ዘሩን መሰረት አድርገህ ሳይሆን ገበያ መሰረት አድርገህ በብቃቱ ነው የምትመርጠው፡፡ በሃገራችን ደግሞ ገበያ ገና አልተፈጠረም፡፡ ቅድም እንዳልከው መደበኛ ያልሆነ (informal) ነው፡፡ መደበኛ ያልሆነ ደግሞ የኢኮኖሚ መለኪያ ሊሆን አይችልም፡፡ መለኪያዎቹ ዘር ነው፡፡ እዚህ ላይ ቢሮክራሲውም ቢሆን በተመሳሳይ ነው የሚሄደው፡፡

ገበያ ካልተፈጠረ በስተቀር ሜሪቶክራሲ አይፈጠርም ማለት አይደለም፡፡ መንግስት እነዚህ ችግሮች ለይቶ መለኪያዎች፣ እንዲሁም ማስፈፀሚያ ስርዓትና ደንብ በማጠናከር ስርዓት የሚዘረጋበትና የሚሰራበት ሁኔታ መፍጠር አለበት፡፡ በአሁኑ ሰዓት እየተደረገ ያለው ግን የነባሩን ስርዓት የሚያጠናክር እንጂ መሰረታዊ ለውጥ ሊያወጣ ይችላል፡፡ የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችል መንግስት መቅረፅ አለበት፡፡ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ካለበት ደግሞ መጀመሪያ የሁኔታ ትንተና ማድረግ አለበት፡፡ ምቹ ሁኔታዎች፣ ፈተናዎች እንዴት ነው የምተነትናቸው? መንግስት ስንል ደግሞ ፌደራል መንግስት ብቻ ማለታችን አይደለም፡፡ የክልል መንግስት ቋንቋ መሰረት ላያደርግ ይችላል፡፡ አንድ አይነት ቋንቋ ተናጋሪዎች ስለሆኑ፡፡ በተለይ በፌደራል መንግስት በኩል ያለው የቋንቋ፣ በባህልና ብሄር ያለ አለመጣጣም መታየት አለበት፡፡ ዞሮ ዞሮ አሁን የያዝነው አካሄድ ዉሱን ለውጥ ማምጣት ካልሆነ በስተቀር፣ እንደ ቢፒአር፣ ቢኤስሲ የመሳሰሉ የለውጥ መሳሪያዎች መሰረታዊ የሜሪትቶክራሲ መርሆች ይዘው የተነሱ አይመስለኝም፡፡

ውራይና፡- ካነሳናቸው አብዛኛው ነገሮች መካከል የአመራር ሃይል ወሳኙ ነገር ነው፡፡ አመራርነት ላንተ ምንድ ነው? ፖለቲካዊ ይሁን ተቋማዊ አመራር በሽግግር ሁኔታ  ምንድ ነው? ከተሞክሮና ካነበብነው ተነስተህ የአመራ መለኪያዎች ምንድ ናቸው?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- በአሁኑ ስርዓት ስልጣን የተከፋፈለ ነው፡፡ ስልጣን ከህዝብ ነው የሚመነጨው፡፡ ከአንድ ማዕከል የሚመነጭ ስልጣን የለም ብለን ነው የምንነሳው፡፡ መንግስትም ቢሆንም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚለው፡፡ ህገ-መንግስትም እንዲህ ነው የሚለው፡፡ ወደ ፌደራል መንግስትም ብንመጣ እነዚህ እነዚህ ስራልኝ ብለው ክልሎች ነው ስልጣን የሚሰጡት፡፡ እንደ የአገር መከላከያ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን፣ ጉምሩክ፣ ገንዘብ፣ የውጭ ጉዳይ ወዘተ ክልሎች ናቸው የሚሰጡት የስልጣን ምንጭም በክልሎች ያሉ ህዝቦች ናቸው፡፡ ስለዚህ አመራር ስንል የተከፋፈለ ነው፡፡ ከአንድ መአከል የሚመነጭ አይደለም፡፡ የድሮው አስተሳሰብ ግን ንጉስ አይከሰስም፤ ሰማይ አይታረስም የሚል ነው፡፡ ለምሳሌ ጠ/ሚኒስተር የሁሉም ችግሮች ምንጭ፣ የሁሉም መፍትሄዎች ምንች አድርጎ ማሰብ አሁን ካለው ስርዓት ጋር አይጣጣምም፡፡ የጋራ አላማ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በጋራ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሰዎች ተመሳሳይ አላማ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አመራር ማለት ሲጀመር የጋራ አላማ መኖርን ነው የሚያመለክተው፡፡ የተለያየ አላማ ካለቸው ግን አመራር አለ ማለት አይቻልም፡፡ አመራርነት የህዝቦች ወግንና ፍላጎት መመለስ ነው፡፡ ስለዚ ውግንና አለ ወይ? ብለን መጠየቅ አለብን፡፡

አመራር ማለት የተለየ ዕውቀት የመኖር ጉዳይ አይደለም፡፡ አንደኛው የጋራ አላማና ውግንና መኖርን ነው፡፡ ይህ በትግሉ ግዜ ነበር፡፡ በሌላ በኩል የራስን አስተዋፅኦ የማድረግ ወይስ በአንድ አስተሳሰብ የመመራት ጉዳይ ነው የሚለው ነው፡፡ ለይስሙላ ኮሚቴ፣ ምክርቤት ወዘተ ሊባል ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው የግሉ አስተዋፅኦ የማያደርግ ከሆነ ዋጋ የለውም፡፡ በግለሰዎች የሚመራ ነው የሚሆነው፡፡ መጀመሪያ ህዝባዊ ውግንና ፍላጎት፣ በመቀጠል ውሳኔዎች ላይ የራስህ አስተዋፅኦ ልታበረክት የምትችልበት ብቃት ሊኖርህ ይገባል፡፡ ብቃትህ በሚትጫወተው የመሪነት ሚና ብቃት ሊኖርህ ይገባል፡፡ ብቃትህ በምትጫወተው የመሪነት ሚና ሊለያይ ይችላል፡፡ ከላይ ያለው አብዛኛው የፖለቲካ ብቃት ተብሎ ነው የሚታወቀው፡፡ የፖለቲካ ብቃት ካለህ ሁኔታዎች የመረዳት እንዲሁም ፖሊሲዎችን አጥብቀህ መያዝን ይኖራል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ፈተና የሆነው የወገናዊነት ጉዳይ ነው፡፡ ለአመራርነት ቀጥረኸው የራሱ ጥቅም ያስቀድማል፡፡ የግል ፍላጎት መጫን ይፈልጋል፡፡ ይህ ሁኔታ በብዛት ካለ የጋራ አላማ እየተሸረሸረ አመራርነት ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ በጋራ ከመስራት ይልቅ እርስ-በርሱ የሚናቆር ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ደግሞ አመራርነት ሊያረጋግጥ አይችልም፡፡ ቀደም ብለን ለማየት እንደሞከርን በሃገራችን የህዝኝነት ስጋቶች እያደገ የመጣበት ሁኔታ አለ፡፡

በአሁኑ ሰአት የራስን ፍላጎት ለማረጋገጥ አለ የምትለው ኋላቀርነት ሁሉ ትጠቀምበታለህ፡፡ አንደኛው ሽፋን ብሄርና ቋንቋ ነው፡፡ የወንዝህ ልጅ ነች ብለህ ህዝብ ለማነሳሳት ትሞክራለህ፡፡ ሁለተኛ የውስጥ የፍትህ፣ የኢኮኖሚ ሌሎች ችግሮች መንስኤያቸው ውጫዊ ነው ብለህ ስትል ነው፡፡ የሽግርህ ፈጣሪ ሌላ አካል ነው ስትል ማለት ነው፡፡ ይህ አባጅቦ ነው የፈጠረው ማለት ስትጀምር ማለት ነው፡፡ የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር አባጅቦ መጣብህ ትላለህ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አመራርነት ማለት እነዚህ የመሰሉ የስርዓቱ አደጋዎች ሲፈጠሩ የሚተነትንና የሚረዳ እና በፅናት የሚታገል ነው፡፡ አመራርነት በፅናት የሚታገልና መስዋእትነት የሚከፍል ነው፡፡ ስለዚህ ወሳኙ ጉዳይ የአስተሳሰብ ጥራትና ጥንካሬ ነው፡፡

ውራይና፡- መንግስት በፖለቲካና በኢኮኖሚው ውስት ከፍተኛ ሚና በሚኖርበት ጊዜ ቀደም ብለን ከገለፅናቸው አመራርነት በተጨማሪ ወጣ ያለ አመራር ማለትም የሚፈራ፣ ከሪዝማቲክ የሆነ፣ የሃሳብ የበላይነት ያለው መሪ ለምሳሌ እንደ መለስ አይነት መኖር አለበት ብለህ ታስባለህ? እንዲህ አይነት አመራር የግድ መኖር አለበት ትላለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- የህወሓት ስታይል የወል (collective) አመራር ነበር፡፡ የተዛባ አስተሳሰብ ስላለን ግን ግለሰን ነው የምንፈልገው፡፡ ባህላችንና አስተሳሰባችን አምባገነን መሪ ነው የምንፈልገው፡፡ ባህላችንና አስተሳሰባችን አምባገነን መሪ ነው የምንፈልገው፡፡ ይህ እያየን ነው ያደግነው፡፡ ህወሓት ወደ ድል ያደረሰው የጋራ አላማ ስለነበረ ነው፡፡ በመሆኑም ለዚህ አላማ መስዋእትነት ለመክፈል ግራ-ቀኝ የማያዩ አባል ነበረን፡፡ ለህዝብ ጥቅም የወገነ ነበር፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በጋራ ነበር ሁሉም ነገር የሚያየው፡፡ ሶስተኛ ክርክሮች ያደርጉ ነበር፡፡ ጥናትና ምርምር ይካሄድ ነበር፡፡ ለምሳሌ እኔ የመስታውሰው በ1972 አከባቢ እነ መለስ፣ አረጋሽ፣ አለምሰገድ ሌሎች የሚገኙበት 04 የሚባል የጥናትና ምርምር የሚካሄድበት ቡድን ተደራጅቶ ነበር፡፡ ከተለያዩ የአለም መፃህፍት የሚመጣ የጥናትና ምርምር ስራ እስከ 1975 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በኋላ ስራችንም እንደ መሰረት አገልግሏል፡፡ አራተኛ ነባራዊ የአገሩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ሁኔታ የሚያውቅ፤ የአለም ሁኔታ የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን ከአገራዊ ሁኔታ ጋር የማጣጣም (contextnalize) ሁኔታም ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ነበር የሚሰራው፡፡ ትኩረት ነበረው፤ ዕረፍት የሚባል ነገር አያውቅም፡፡ ከዚህ አልፎም በውስጣችን የሚታዩትን ኋላቀርነት በፅናት ይታገል ነበር፡፡ ውግንናው በሚመለከት የሚታዩትን አለመጥራቶች ያለምህረት ይታገላቸው ነበር፡፡ አሳታፊ፣ አሳምሮ የሚሰራና የሚያታግል ሃይል ነበር፡፡ ይህ በመሆኑም ህወሓት ወደ አሸናፊነት መጥቷል፡፡

ይህ የመለስ ውስን ሚና ወይም የሌላ ግለሰብ ሚና አይደለም፡፡ የወል (የጋራ) ሚና ነበር፡፡ እዚህ ጋር ግን የተሸለ አቅም ያላቸው ሰዎች አጠቃላይ ሃይሉን የማነቃቃት ሚና ነበራቸው፡፡ እንደ መለስ የመሳሰሉ ቅመሞች ነበሩ፡፡ ሁሉም ነገር ለመለስ መስጠት ግን ትክክል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለመለስ የፈጠረው የትግራይ ህዝብ ትግል ነው፡፡ መለስን የፈጠረው ትግል ነው፡፡ ስለዚህ መለስን የመለስ ግለሰብ መፈለግ ከንቱነት ነው፡፡ መለስ የተፈጠረበት ጊዜ፣ ሁኔታና ሂደት የለም፡፡ መተማመን ያለብን በራሳችንና እርሰ-በርሳችን ነው፡፡

ህዝባዊ ውስጣዊ ዲሞክራሲ አልነበረውም የሚሉ አሉ፡፡ በሀርግጥ ኋላቀርነቶች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በ1973 አከባቢ ኦሊቲዝም የሚባል ኋላቀር አስተሳሰብ ነበር፡፡ ኢሊቲዝም ማለት ራስህን ከምልከተ-ህዝቡ ነጥለህ ራስህን ልዩ አድርገህ የማሰብ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ኋላቀርነት ነበር፡፡ ይህ ግን ያለምንም ምህረት ታግለውታል፡፡ ሌላው እኔነትና ግለኝነት ናቸው የነበሩት፡፡ በየመድረኩ እየጠፈጠሩ የነበሩትን ችግሮች እየታገለ፤ ተማሪና ተራማጅ ድርጅት ስለነበር እንጂ በፀረ ዴሞክራሲያዊነት የማይታማ ከሆነማ ምኑ ድርጅት ሆነው፡፡ ድርጅቱ ማለት የአንድ ማህበረሰብ እንቅስቃሴ መገለጫ ነው፡፡ 

በህብረተሰባዊ እንቅስቃሴ ደግሞ ሁሉም አይነት ኋላቀርነት፣ ኋላቀር አስተሳሳቦችና ባህሎች የሚንፀባረቁበት ነው፡፡ ስለዚህ ዋናው ቁምነገር እነዚህ ችግሮች እንዴት ታግሎ ፊታቸው የሚለው ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ ንፁህ ከሆነ ግን ድርጅቱ ሊሆን አይችልም፡፡ አሁንም በኢትዮጵያ የምንጠብቀው ነገር ከወል አመራር አንፃር ነው ማየት ያለብን፡፡ አንድ ግለሰብ ከሌላ ግለሰብ ጋር አይደለም ማወዳደር ያለብን፡፡ የሆነ ሰው በላምባዲና መፈለግ አስፈላጊ አይደለም፡፡ የወል አመራር አለ ወይ ብለን መጠየቅ ነው ያለብን፡፡ የወል አመራር ከሌለና የግለሰብ ቆራጭ ፈላጭነት ከነገሰ ግን አደጋ ነው፡፡ ቆራጭ ፈላጭነት ከነገሰ ወይም ግለሰበኝነት ከነገሰ ፀረ ዲሞክራሲያዊ ነው፡፡ ይህን የሚታገል ሃይል ካለ ደግሞ በመልካም ሁኔታ ስርዓቱ ነው፡፡ ይህን የሚታገል ሃይል ካለ ደግሞ በመልካ ሁኔታ ስርዓቱ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ አመራሩ ከዚህ አንፃር ነው ማየት ያለብን፡፡

ውራይና፡- እንደ ታጋይነትህ በትግሉ ወቅት ሐቀኛ ህዝባዊ ዓላማ ነበር፡፡ አንተም የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ታየው ነበር፡፡ የተማርከው ነገርም አለ፡፡ በትግል ሂደትም የተማርከው ነገር አለ፡፡ አሁንም ሆነው ያ የነበረ ዓላማ ትክክል ነበር ብለህ ታስባለህ? በተጨማሪም ለትግራይና ለኢ/ያ እየታገልኩ ነው ትል ነበር፡፡ ልደቱ ሶስት መፅሃፍ ፅፎ ነበር፡፡ አንደኛው መፅሃፍ የህወሓት ታጋዮች ኢ/ያ ለመበታተን ነው የታገሉት ይላል፤ ቀጥሎ ደግሞ ይህ ትክክል አይደለም በተለይ ጥቂቶቹ ለፍትህ፣ለልማትና ለሰላም ነበር የታገሉት ይላል፡፡ ለመልካም አላማ ነበር የታገሉት ይላል፡፡ ከዚህ አንፃር አንተ በትግሉ ውስጥ ያደክ በመሆንህ የትግሉ አላማ ይህ ነበር ትላለህ? አሁንስ ምን መሆን አለበት ብለህ ታስባለህ? የታገልክለት ዓላማ እየተሳካ ነው ብለህ ታስባለህ? ምንስ መሆን አለበት ትላለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ወደ ትግል ስሄድ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ በወቅቱ በአከባቢያችን ይህ ሁኔታ ነበር፤ ከመፃህፍቶችን አነብ ነበር፡፡ የህወሓትና የኢህአፓ መፅሄቶች ነበሩ፡፡ በእኛ አከባቢ የሁለቱም ድርጅቶች እንቅስቃሴ ነበር፡፡ በወቅቱ ክርክሮች ይደረጉ ነበር፡፡ ተማሪዎች ስለነበር እየመጡ የወሩን ነበር፡፡ ከዛ በኋላ ወደ ህወሓት ተሳብኩ፡፡ አንደኛው መለኪያ ስነ-ምግባር ነበር፡፡ ለምሳሌ ህወሓት ምግብ ሲፈልጉ ርቧቸውም ቢሆን አያስገድዱም ነበር፡፡ ኢህአፓ ግን ሃይል ካላቸው ወደ ክርስትናና ተስካር ገብተውም ቢሆን አስገድደው ይበሉ ነበር፡፡ ሁለተኛ ኢህአፓዎች የማረኩት ስኳር ይሁን አንሶላ እየሰጡ ት/ቤት ውስጥ እየገቡ ተማሪዎች ይመለምሉ ነበር፡፡ በህወሓት በኩል ግል አሳምና ነበር የምትመለምለው፡፡ ሌላው ኢህአፓ የሚቃወማቸው ሰው ካለ ትቀጣ ነበር፡፡ ወደ ጭንጫ የሆኑ ቦታ እየወሰዱ ይገርፉ ነበር፡፡ በርግጥ አንዳንድ የህወሓት የህዝብ ግንኙነት አባላትም ተመሳሳይ ነገር ያደርጉ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ ግን ከነሱ ለሚለይ ሰው ምንም አያደርጉም ነበር፡፡ ኢህአፓዎች በሃይል መሬት ሲነጥቁ ታዝቢያለሁ፡፡ ስለፊውዳሊዝም መተንተን አይጠበቅብኝም፡፡ ጉዳዩ የፍትህ ጉዳይ ስለነበር፡፡

ደርግም ቢሆን ይገል ነበር፡፡ ጓደኞቻችን፣ ወንድሞቻችን ሞተዋል፡፡ ይህ አሁን ቁጭ ብለህ እንድታይ የሚያደርግ ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከአከባቢያችን ወጥተን ተማርን፡፡ ከዚህ በፊት ግን የመሬት ክፍፍል ነበር፡፡ እኔም ፊደል የቆጠርኩ ስለነበር መዝጋቢ ነበርኩ፡፡ ኮሚቴ ተዋቅሮ መሬት የሚያከፋፍሉ ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ጉቦ እንዳይበላ ጥንቃቄ እናደርግ ነበር፡፡ ለምሳሌ ጦላ ጠምቆና አርደው የተለየ ጥቅም የሚፈልጉ ነበሩ፡፡ ህወሓትም ቢሆን ይህንን ትቃወመው ነበር፡፡ ውስጥህ የሚኮረኩር ነገር ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ አላማ ማለት ይህ ነው፡፡ ጊዜው መጥፌ ነበር፡፡ ትምህርታችንም በሚገባ መከታተል አልቻልንም ነበር፡፡ መምህራንም ተበታትነው ነበር፡፡ ትምህርት ተዘግቶ ነበር፡፡ የሚያስተኛህ ነገር አልነበረም፡፡ ይህ ራሱ የቻለ አላማ ነበር፡፡ ሌላ አላማ አልነበረም፤ ወደ ድርጅቱ ገብተንም ታገልን፡፡

እነዚህ ሁሉ የፍትህ ጉዳይ ነው፡፡ በቋንቋችን አልተማርንም፡፡ በአማርኛ ነበር የተማርነው፤ ት/ቱ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ነበር የሚፈጅብን፡፡ መምህራኖቹ ከመሃል አገር የመጡ ስለነበር ከአማርኛ ውጭ በትግርኛ መናገር አትችልም፡፡ ሊገባህ አስቸጋሪ ነበር፡፡ እነዚህ ነገሮች ጠቅለል አድርገህ ስታያቸው የህወሓት አላማ ዲሞክራሲና ፍትህ ነበር፡፡ ለዚህ ነበር የታገልነው፡፡ ሁሉም ታጋይም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው ትግሉን የተቀላቀለው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ከበሮ ሰምቶ ነው ወደ ትግል የተቀላቀሉት ይላሉ፡፡ ከውጭ ሆነው ማለት ነው፡፡ መቸም በከበሮና በጭፈራ ወደ ትግል የተቀላቀለ ፈንጅ አይረግጥም፡፡ ራሱን መስዋእት አያደርግም፡፡ የጦርነት ነበልባል የማይገባቸው ናቸው እንዲህ የሚሉት፡፡ የህይወት መስዋእትነት በቀላል ትንታኔ የሚያልፉት ናቸው፡፡ ምንም ቢሆን በከበሮና በጭፈራ ህይወትህን አትሰጥም፡፡

ውራይና፡- ታድያ የከበሮውና የጭፈራው ሚና ምን ነበር? ብዙ ታጋይኮ እንደ ትልቅ ሚና ነው የሚቆጥረው?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ከበሮና ጭፈራ አለ ከተባለም ብሄራዊ ዘፎኖችን ነው፡፡ ከዚህ በፊት ትግርኛ አልነበረም፡፡ አማርኛ ነበር፤ ተነስ… ተራመድ የሚል ዘፈን ነበር፡፡ በትግሉ ጊዜ ትግርኛ መጣ፡፡ ህወሓት የትግርኛ ዜማና ግጥም እንዲሁም ባህል አወጣ፡፡ ይህ የፈጠረው ኩራት ነበር፡፡ ይህ ተራ ስሜት አይደለም፡፡ ኢህአፓም ይዘፍኑ ነበር፡፡ ቢሆንም የማንነት ጉዳይ ነው፡፡ ማንነት መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ ህወሓት ስርዓት የገነባው በትግሉ መገበድ አከባቢ አይደለም፡፡ ይልቁ በትግሉ ሂደት ውስጥ ነው የነበረው፡፡ የአፈር ጥበቃ፣ ምክር-ቤት፣ ራስህን በራስህ ማስተዳደር፣ የመሬት ክፍፍል፣ የፍትህ ስርዓት፣ ፍርድ ቤት በዛፍ ስር ነበር ድሮ የተጀመረው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ባህልና ቅርስ፣ የት/ት ስርዓት፣ ጠየናና እርሻ በሂደት እየጠገነቡ የመጡ ናቸው፡፡ አሁን በምናየው ልክ ላይሆን ይችላል፡፡ የኋላኋላ ግን ይህ ሁኔታ ስታየው ስርዓት እንደተቀየረ ትረዳለህ፡፡

ታሪክ ሰርቷል፡፡ አዲስ ህገ-መንግስት አምጥቷል፡፡ አሁን ወደ ኋላ በመመለስና ወደ ፊት በመሄድ መካከል ነው ትግል ያለው፡፡ በርግጥ ወደ ሌላ አቅጣጭ የመቀየር ጥረትና ሙከራም አለ፡፡ አሁን ወደድንም ጠላንም ስርዓት ተቀይሯል፡፡ ይህ ትልቅ ኩራት ነው፡፡ የመስዋእትነት ውጤት ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት በትግራይ ውስጥ እኔ በነበርኩበት አከባቢ ተመሳሳይ ችግሮች የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ የመበልፀግና የማደግ ጥያቄዎች ናቸው ያሉት፡፡ በርግጥ ስለ ፍትህ የሚያነሳቸውም ጥያቄዎች ቢሆን በልጆቹ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ድሮ ከመሃል አገር በሚላኩ የሚፈጠሩ የፍትህ ችግሮች ነበሩ፡፡ አሁንም እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሌላ ፈተና ነው፡፡ ድሮ የነበረው ችግር አይደለም አሁን ያለው፡፡ ሁሉጊዜ ደግሞ አዲስ ችግር ፈተና ይኖራል፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ያመጣው ችግር አለ፡፡ የመሰረተ ልማቶች ተዘርግተዋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የኢኮኖሚ ሽግግር ስላልተካሄደ ያየተተከለው አዲስ ስርዓት ወደ ኋላ እንዳይመለስ የሚል አሳሳቢ አደጋ አለ፡፡ በዚህ ምክንያት ደግሞ በየቀኑ የሚፈታተኑ ችግሮች አሉ፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ህዝብ ማዕከል ያደረጉ እና በየቀኑ የሚያገረሹ በሽታዎች የሚቀሰቅሱትና ወያነ የማጥራራት ዘመቻ ህዝብ የማነሳሳት ማዕከል የሚፈጥሩት ከላይ የተቀመጠው ችግር ሊፈጠር የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ይህ ድሮ በርሃ እያለን የለመድነው ጉዳይ ነው፡፡ ደርግም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ያደርግ ነበር፡፡ ከሃዲው ወያነ ይል ነበር፡፡ ይህ መፈክር አዲስ አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ነው እየመጣ ያለው፡፡ የእነሱ ስርዓት ነው የተቀየረው፡፡ የእነሱ ጥቅማጥቅም ስለሆነ የተመታው ቢጮሁ እውነታቸው ነው፡፡ ስለዚህ ይህ በቀጣይነት የሚወገድ እንጂ የትግል ውጤታችን ከንቱነት አይደለም፡፡

ውራይና፡- ቅድም እንዳልከው ዓላማው ትክክል ነው፡፡ ትክክለኛ አላማ ይዘህ ሁኔታዎች የመረዳት፣ የወል አመራር፣ ተማሪ ድርጅት መሆን፣ ቁርጠኝነት የሚባሉ መሰረታዊ የድርጅቱ እሴቶች አሉ፡፡ እነዚህ በማከናወን የስርዓት ለውጥ መጥቷል፡፡ ኢ/ያም እንደ ሃገር የሚያስቀጥላት ህገ-መንግስት ተተክሎለታል፤ ዕድገትም አምጥቶላታል ቢሆንም ዕድገቱ ሽግግር ያላሳየ ተወስኖ የቀረ ነው፡፡ በዚህ ድል ውስጥ ሆነህ ስታየው አሁን አጋጥሞ ያለው ችግር ለመቅረፍ አሁን ካለው የወጣቶችና የምሁራን ጉዳይ ጋር አያይዘህ ምን መደረግ አለበት ትላለህ? እነዛ የአመራር እሴቶች በተለይም ህዝባዊነትና ከልምድ የመማር ጉዳይ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ምን መስራት አለበት? በጥራታቸው የሚኖሩበት ስርዓት፣ እነዛን የአመራር እሴቶች መሰርቶ አድርጎ የሚሄድና ግለኝነትና ህዝበኝነት የሚታገል ሃይል በትግራይ እንዴት መፍጠር ይቻላል? ይህ ይሆናል የሚል ተስፋስ አለህ ወይ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- አሁን መንገዳገዶች አሉ፡፡ በአመራሩ ዘንድ ማለቴ ነው፡፡ በድርጅቱ ውስጥ በሂደት የግል ፍላጎት ያሳደገ ሃይል ተቀላቅሏል፡፡ የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በድርጅቱ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በዚህ መቀላቀል ውስጥም ስርዓቱ ወደፊት እንዲራመድ የሚፈልጉ ሃይሎችም አሉ፡፡ የራሱ ፍላጎት ብቻ የሚገዛው ሃይል ብቻ አይደለም ያለው፡፡ ሌላው በመንግስት ውስጥ የሜሪቶክራሲ አሰራር የመንግስት ጉዳይ ለማጠናከር ጠንካራ ፖሊሲና ስትራቴጂ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ሜሪቶክራሲ የሚወግን ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል፡፡

በተለይ በትግራይ ምቹ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ይህ ማለት እንደ ብረት የጠነከረ ተራራዎችን ማፍረስ የሚችል ህዝብ ነው ያለው፡፡  በነበልባል እሳት የተፈተነ ህዝብ ነው፡፡ ቀደም ብለን ያየናቸው እሴቶች በህዝቡ ዘንድም አሉ፡፡ ስለዚህ አመራርነት ማለት እነዚህን እሴቶች በመለየት ከሁኔታዎች ጋር አጣጥመህ የመተግባር ሁኔታ ነው፡፡ ሁለተኛ የትግራይ ህዝብ ብለህ ስለጠየቅየኝ፤ የትግራይ ህዝብ የራሱ እሴቶች አሉት፡፡ ለዚህ ዘመን በሚመጥን መንገድ እነዚህ ዕምቅ ሃብቶችና እሴቶች ሊወጣቸው ይቻላል፡፡ እነዚህ እሴቶች እንዲወጡ ግን በአንፃር ብልጫ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ አንፃራዊ ብልጫ (comparative advantage) ደግሞ የሰው አስተሳሰብ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይህ ማለት የሰው ሃይል መሰረት ያደረገ ነው፡፡ እነዚህ በህወሓት ትግል ጊዜ የተፈጠሩ እሴቶች እንደ አንፃራዊ ብልጫ ወስዶ የኢ/ያ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ላይ የራሱን አሻራ በሚያሳርፍበት ሁኔታ መንቀሳቀስ አለበት፡፡ በሌሎች ክልሎች የተሰሩትን በመድገም ሳይሆን የራሱን አንፃራዊ ብልጫ ወይም ተፈጥሮ መሰረት ያደረገ ፖሊስና ስትራተጂ መቅረፅ አለበት፡፡ ከፌደራል መንግስት በሚመጣ አንድ መድሃኒት ለሁሉም ቦታ ከሚል አስተሳሰብ መውጣት ይኖርበታል፡፡ መሰረታዊ የፌደራሊዝም ፖሊሲ ሊሳካ ከሆነ የራሱን ድርሻ መውሰድ አለበት፡፡ እንደ ተወዳዳሪ የራሱን ልዩ አቅም መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ ይገበዋል፡፡

የትግራይ አንፃራዊ ብልጫው ብዬ የማስበው ፅናት፣ ድስፒሊን፣ ለሰው ልጅ የሚሰጠው ክብር፣ በዕውቀት የተመሰረተ፣ በረዥም ታሪክ ያፈራናቸው ቅርሶች አሉን፡፡ እነዚህ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ልንቀይራቸው ይገባል፡፡ በፖሊሲ ደረጃ የለም ማለት አትችልም፡፡ ይሁን እንጂ እንደየ ሁኔታው ሊስተካከልና ሊቀየር ይገበዋል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ አይደለም፡፡ ህወሓትም ቢሆን እንደ ባህሪ በየመድረኩ እየተማረ የህዝብ ጥቅም ነበር ቅድሚያ የሚሰጠው፡፡ የከረመውን እያነከ የሚባል ከሆነ በታች ነው የሚሆነው፡፡ skilled incompetency የሚባል ነገር አለ፡፡ አንድ የምታውቀው ነገር በተደጋጋሚ የምትሰራው ከሆነ ተተክልሃል ማለት ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ በኢ/ያ ተፈላጊ መሆን ካለበት አሁንና ለወደፊቱ በምፈጥረው ሃብት ነው፡፡ ድሮ የነበረውን ተራ እየጎመራ የሚሄደው አሁንና በቀጣይም፡፡ በሚያፈራቸው አዳዲስ እሴቶችና ሃብት ነው፡፡ ስለአመራርነት ስናስብ ስለ ታጋይ አይደለም የምናስበው፡፡ ታጋይ እዚህ ደረጃ አድርሶናል፡፡ የትግራይ አመራርነት ተስፋ ወጣቱ ነው፡፡ ከድሉ ብኋላኳ የጠወለዱ 25 ዓመት ሆኖቸዋል፡፡ 70 ከመቶ የትግራይ ህዝብ ወጣት ነው፡፡ ይህ አመራር በትክክል ሊሰራ ከሆነ የግድ ሽግግር ሊኖር ይገባል፡፡ ሽግግር ባህሪያዊ ነው፡፡ በዚህ ቀን ይህን ያክል ወጣቶ ስልጣን እናወርስዋለን የሚል ሽግግር ይፈፀማል የሚል አስተሳሰብ የለኝም፡፡ ዕቅድ አጋዥ መሳሪያ ነው፡፡ ተፈጥሮአዊ ሂደቱ እንዳይኮላሽ ነው መከላከል ያለብን እንጂ ሽግግር በዕቅድ የምከናውነው ጉዳይ አይደለም፡፡ ሽግግሩ ሊያደናቅፉ የሚችል ዕንቅፋቶች ግን በዕቅድ ልታስወግዳቸው ትችላለህ፡፡ ድርጅቱ ወይም መንግስት ሚናው እየተጫወተ ነወይ የሚለውን ጥያቄ ነው መነሳት ያለበት፡፡ እንደ ታጋይ ስመለከተው መነሳት ያለበት ጉዳይ ሽግግሩን የሚያደነቅፉ ዕንቅፋቶች እያስወገደ ነው ወይ የሚለውን ጉዳይ ነው መታየት ያለበት፡፡ ታጋዮች ምቹ ሁኔታዎች ከመፍጠር በዘለለ በአመራርነት ባለቤት መሆን አይቻልም፤ ሊሆኑም አይችሉም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይሁን በቀጣይ መድረኮች ታጋዮች መለካት ያለባቸው የሽግግር ዕንቅፋት እየሆኑ ነው ወይስ ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ በሚለው መሆን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ራሳቸው መሪዎች መሆን አይችሉም፡፡ በመሆኑም ሽግግር ያስፈልጋል፡፡ ሽግግሩ በኢኮኖሚ ብቻ አይደለም፤ በአመራርነትም ሽግግር ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአመራር ቀውስ አለ፡፡ ቀውስ የፖሊሲ፣ ወይም የስትራተጂ አይደለም፡፡ መተካካት የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡ በእኔ አገላለፅ ወጣቱ እስከ አሁን ጠባቂና ተቹ ነው፡፡ መተቸት ጥሩ ነው፤ቢሆንም ሃላፊነት መውሰድ አለበት፡፡ የዚህ ዘመን ሃቀኛ አመራር ወደፊት እንዳይመጣ ዕንቅፋት የሆነው ይህ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ችግሮች ፈተና አሁን ያለው አመራር ራሳችን ማስቀጠል ጥሩ ነው፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ግን በአሁኑ ጊዜ ትችት ነው የሚበዛው፡፡ ይህ ከቀድሞው ስርዓት የወጣ ነው፡፡ ልዩነቱ የንጉስ ስም አጠፋችሁ ተብሎ ስለማይጠየቅ ነው፡፡ በመሆኑም እንደ ንጉስ በማየት ማተቸት ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ከልብ ሃላፊነት መውሰድ አለበት፡፡ ለሁሉም መተቸቴ ግን አይደለም፡፡ ቢሆንም ከልብ ሃላፊነት አልወሰደም፤ ምንምኳ ሃላፊነት እንዲወስድ የሚያስችል ዕድሎች ያልተቻቸለት ቢሆንም፡፡ ሁኔታዎች አልተመቻቸለትም ስንል ግን በተነፃፃሪ ነው፡፡ የሚያፍኑት ነገሮችም የለም፡፡ እያፈኑት ያሉት ከውስጥ ያለው አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ናት ቀውስ ያልናት ሁኔታ የሚፈልግ ነው ያለው፤ መራመድ የሚፈልገውም ይፈራል፡፡ እያስፈራው ያለው ደግሞ ለዘመናት ሊገነባ የመጣው ማህበራዊ ቅርፅ የፈጠረው ተፅዕኖ ነው፡፡

ግንባታ በሚመለከትም ችግር አለ፡፡ የትምህርት ጥራት ችግር አለ፡፡ እኔ ጥራት የምለው ኢንግሊዘኛ ማዕከል ያደረገ ት/ት አይደለም፡፡ በርግጥ የፊዚክስ፣ ሂሳብ ት/ቶች የት/ት ጥራት ዕምብርት ናቸው፡፡ ፊዚክስና ሂሳብ ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ጥቅም ላይ ሲውሉ እንጂ ለማስላ ብቻ ከሆነ ጥቅም የለውም፡፡ በሃገራችን ያለው ግን ዋጋ የለለውምን ኒውተን እንዲህ አለ፤ አንስታይን እንዲህ አለ የሚለውን ነው፡፡ ጥራት የምንለው ቀመሩ በዕለት ተዕለት ሂወታችን የሚሰጠው ትርጉም ነው፡፡ ጥራት ማለት ይህ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ጥራት የምንለው ግን ማህበራዊ ሃብቶቻችንና ፀጋዎቻችን ነው፡፡ ጥራት ያለው ት/ት የምንለው ማህበራዊ እሴቶቻችን ማለትም በታሪክ የወረስናቸው እሴቶቻችን፣ መልካም የማንነት መገለጫዎችን በመለየት የማንነት አካል ማድረግ፣ ኋላቀር የሆኑትን የሚያስወግድ፣ በዋናነት ደግሞ ክህሎቶቻችን የሚያሳድግ ትምህርት ሲሆን ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጋር ተያይዞ ፈተናዎች አሉ፡፡ ይህ ደግሞ ወጣቱ ፈጥኖ ሃላፊነት እንዳይወስድ እያደረገው ይገኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምዕራባዊ የሆነ ግለኝነት የሚያንፀባርቁ አሉ፡፡ እኔ እንዲህ ከሆንኩ፤ ማህበረሰቡ የራሱ ጉዳይ የሚሉ አሉ፡፡ ህብረተሰብ፣ አገር ለኔ ምኔ ናቸው የሚል ስንፍናና ቀውስ የጠጠናወታቸው አሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለኛ ማህበረሰብ አይሰራም፡፡ ወደ ውጭ ሄደ ሆነ ተሰደደ የፈለገው ማደረግ ይቻላል፡፡ ይህ የቀውስ መገለጫ ነው፡፡ አገርህ ልትቀይራት ከሆንክ ማንነትህን ሊኖርህ ይገባል፤ ማንነትህን ልትይዛት ይገባል፡፡ ከማንነትህ ውጭ ሆነህ አገርህ ልትቀይራት አትችልም፡፡ አሁን ካለው ወጣት መልካም አመራር ሊወጣ ይችላል፡፡ በደንብ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አደጋ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ እኔ የምለው ወጣቱ ሃላፊነት ሊወስድ ይገበዋል፡፡ ነባሩ ታጋይ ደግሞ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር አለበት፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ሞተር ሆኖ መቀጠል ስለማይችል ሊቀየር ይገባዋል፡፡ ሞተር አይደለሁም ብሎ ራሱን ማሳመንና መቀበል ይኖርበታል፡፡ ድርሻዬ ምቹ ሁኔታዎች ለወጣቱ ማመቻቸት ነው ብሎ መቀበል አለበት፡፡ ተፈጥሮአዊ ሂደቱ መቀጠል እንዲችል ነው ይህን ሃቅ መቀበል ያለበትና ሁኔታዎች ማመቻቸት ያለበት፡፡

ውራይና፡- አሁን ችግሮች አሉ፡፡ በዚህ ሀገራዊ ሁኔታዎች ተጋሩ በአሁኑ ወቅት በተለየ ዓላማ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ እየሆንን ነው ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ አስጊ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጋር ተሳስሮ ምን መደረግ አለበት? ምንጩስ ምንድ ነው? መፍትሔውስ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡-  አሁን በዚህ ጉዳይ በደምብ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ መጥፎና ያልጠሩ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወደ ወረደ አጀንዳ ነው የሚቀየሩት ይሄ በትግል ወቅትም ሲገጥመን የነበረ ነው፡፡ አብዛኛው ወደ ወረደ አጀንዳ ነበር የሚሄደው ወደ አውራጃ ወረዳ ጥያቄ ነበር የሚባሰው፡፡ የእከሌ ልጅ የእከሌ ነው ይሄ የጋራ ዓላማና ተልዕኮ ሳይኖር ሲቀር የሚመጣ ነው፡፡ ተልዕኮ አልባ ሀይል ሲፈጠር የሚመጣ ነገር ነው፡፡ ሌላ ደግሞ ዓላማ እና ተልዕኮ ሲጠፋ ወይም ሲታጣ ብቻ ሳይሆን የግል ፍላጎቶች ለማሟላት የሚፈጠር ነው፡፡ ይሄም የኪራይ ሰብሳቢዎች ባህሪ ነው፡፡ በደምን አስበው የሚፈጥሩት ጉዳይ አይደለም ከዚህ ባህሪ የሚመነጭ ነው፡፡ ወደ ስልጣን ለመምጣት ፍላጎት ካለ ሁሉም እንቅስቃሴህ በዛው ነው የሚቃኘው፡፡ ትዋሻለህ ውሸት ነውር አይደለም በእንደዚህ ዓይነት ፍላጎት እና ሁኔታዎች ብሔር ከብሔር ታጋጫለህ ይሄም ነውር አይደለም ባህሪያዊ ነው አቋም የሚባል ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ያ ሁኔታ የሚፈጥረው አጣብቂኝ ረብሻ አለ፡፡ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችም ለዚህ ነው የሚያመቻቹት ለምሳሌ አንዳንድ ማንነቶች ቋንቋን መሰረት ያደረገ ብሄራዊ የመንግስት ስርዓት ያዋጣል በሚል እንቅስቃሴ የሚመጣ ነው፡፡ የእነ ትራምፕ ሞዴልም እንደ ጥሩ ነገር ይወስዱታል፡፡ እገዛ የከሰሩ ነጮች ችግራችን በዛ ስርዓት ሳይሆን በስደተኞች ነው የተፈጠረው የሚል የሚመሳሰል ነገር አለ፡፡ ሃይማኖት መፍትሔ አድርጎ የሚመጣም አለ፡፡ ስለዚህ በአጣብቂኝና ረብሻ ወቅት ሁሉም በተለያየ ኋላቀርነት ናቸው የሚመጡት፡፡  ይሄ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ድል ካደረግን በኃላም እንኳን በ1985 ዓ.ም፣ 93 ዓ.ም፣ 97 ዓ.ም የጨለመና ቀውስ የተፈጠረበት ሁኔታ ነበረ፡፡ አሁንም እየታየ ነው፡፡ ቅድም እንዳስቀመጥኩት በሽግግር ወቅት ነው ያለነው፡፡ መጠየቅ የሚገባን ዋናው ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚደገም ከሆነ ነው፡፡ ስለዚህ በተደጋጋሚ ስትነሳ የምንሰማት ነገር እኔ ወደ ትግል ከገባው ጀምሮ ወያኔ ከዳተኛ የሚል ትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥያቄ ነው፡፡ ይሄ አዲስ አይደለም፡፡ አሁን ይሄ ለምን መጣ የሚል ነጥብ ማየት ጥሩ ነው፡፡ መነሻውስ ምንድ ነው? ባህሪውስ ምንድ ነው?

የስርዓትለውጥ የፈጠረው በመሐል የስርዓት ግጭት አለ፡፡ በስርዓት መሐል የሚደረግ ትግል ነው፡፡ የስርዓት ለውጥ ነው፡፡ በአዲሱ ስርዓት ስልጣኑ የተቀማ ወይም ስልጣኔን ይቀማኛል ብሎ ሲሰጋ የነበረ አሜን ብሎ አይቀበልህም፡፡ ይሄ የፈጠረው ችግር አለ፡፡ እነዚህ በአመለካከት ለተከታታይ 40 ዓመታት በልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውና ህብረተሰቡ ሰርተውበታል፣ ስለሚሰሩ ግን አይደለም፡፡ ይሄን የሚቀናቀን ከሆነ በተለይ ስርዓቱን ለመናድ ሙከራ የሚያደርግ ኃይል ሲፈጠር ለይተህ ስብእናን መግደል (character assassination) ማድረግና ጠላትና ወገን መፍጠርና ኃይል ልታደክም ግድ ይላል፡፡ በዋናነት ግን በአመለካከት የሚፈጠር ኃላቀርነት ነው፡፡ የገበያ ትስስር አልተፈጠረም፡፡ ህዝቡ እርስ በእርስ አይተዋወቅም፡፡ የህዝቦች መስተጋብር የለም፡፡ ይሄ ባልተፈጠረበት ሁኔታ የሆነ ከረጢት እየፈጠርክ የምታደርገው የተዛባ ፕሮግራም ለግዜው ጩኸት ልትፈጥር ትችላለህ፡፡ ይሄ እንጂ በሆነ አከባቢ ያለ ገበሬ ምንም ዓይነት ጥቅም ልዩነት የለም፡፡ ግን ማስመሰል አለብህ፡፡ አመለካከቶች አሉ፡፡ ይሄን የሚቀበል ኃላቀርነትም አለ፡፡ ውሸትና አሉባልታ ሊሰማ ይችላል፡፡ ውሸትና ወሬ በእውቀት አልተተኩም፡፡ ሌላ ቦታ ያለ ሰው ሊመስለው ይችላል፡፡ አንዳንድ ተጋሩም ማንነታቸው ተጠቅመው በመጥፎ መንገድ ይሄን የሚያባብሱ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

የሌላ አገር ተወላጅ ሲታዘባቸውም ከሚሰማው ጋር ሊያመሳስለው ይችላል፡፡ ከዚህ ተነስቶም ሊሰስት ይችላል፡፡ ስለዚህ ዋናው መንስኤ (ጠንቅ) አንድ ለ40 ዓመታት የስርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚታገል ያለው ሃይል ለስልጣን የሚፎካከር ሃይል ብሎ ስለሚወስድ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ይሄን የሚቋቋም ኃላቀርነት ስላለ ነው፡፡ ከዛ ግን የችግሩ መጠን ማየት ካለብን ሁልጊዜ በኢሊት ደረጃ ሊኖር ይችላል፡፡ አደጋው በህብረተሰቡ ደረጃ ከተፈጠረ ነው አደጋ የሚሆነው፡፡ ይሄ ችግር በየትኛው ደረጃ ነው የሚፈታው ካልን በእኩልነት አንድነት ነው፡፡ በስርዓት፡፡ ይሄ እንቅስቃሴ በይዘቱ ፀረ ህዝብ ነው፡፡ ፀረ ተጋሩ ብቻ አይደለም፡፡ የማንኛውም ህዝብ ፀር፣ ይሄን የሚያደርገው ጨምሮ ነው፡፡ ፀረ ተጋሩ ብቻ ነው ብለን መውሰድ የለብንም፡፡ በባህሪው የማንም ህዝብ ብላት ነው፡፡ የፈተና የኃላም ብቻም አይደለም እኩል የሚሄድ ነው፡፡ ሁሉም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው ነገር ካየን መጀመሪያ ከ አማራና ቅማንት ነበረ ቀጥሎ እዛ በሚኖር ተጋሩ ችግር ተፈጠረ፡፡ በመቀጠልም በሶማሌና ኦሮሞ ተፈጠረ ከዛም በገዳዩ መጤና ነበር የሚል ችግር ተፈጠረ፡፡ እንደዛ እያልክ ካየኸው ዓላማው ፀረ ህዝብ ነው፡፡ ፀረ ተጋሩ አይደለም፡፡ በዚህ የሚጠቀም ሃይል አለ፡፡ አቅጣጫ አስቀያሪ ነው፡፡ መንግስት በዚህ ጉዳይ የሚያተኩር ከሆነ ኪራይ ሰብሳቢው አቅሙን አሰባስቦ ለመተው ይቸገራል፡፡ ወደ ስልጣን የሚመጣ ከሆነም ኋላቀርነትን እያቃጠለ ሊጠቀምበት አለበት፡፡ ራሱን ለማዳንና ወደ ስልጣን ለመውጣት ነው የሚጠቀምበት፡፡ በህዝቡ ውስጥ ግን በመሰረቱ አንድ ህዝብ ሌላኛውን ህዝብ አነጣጥሮ የሚጠቃበት ትስስር የለም፡፡ እነዛ ፀረ ሰላም ሃይሎች የሚያደርጉት ካየህ ኢትዮጵያ ያበቃላት ፈርሳለች ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ትስስሩ ጥሩ ነው ህዝቡ ከኢሊቱ የበለጠ አስተሳሰብ አለው፡፡ ከዚህ ስርዓት ጋር ሊተሳሰር ይገባል፡፡ በእኩልነት የተመሰረተ አንድነት ያምናል፡፡ መጥፎ ሁኔታዎችም ድሮም ቢሆን መስመር አያልፉም ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ በተለያዩ ሐይሎች የሚፈጥሩ ፕሮፖጋንዳ መሰሎች የሚገነፍልበት ሁኔታዎች አሉ፡፡ ቢሆንም ግን ሳይቆይ ይሰክናል፡፡ ይሄ ጉዳይ የአመራር ጉዳይ ነው የሚሆነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መፍትሐየው ምንድ ነው የህዝብ ትግራይ የቀጣይ ጥቅሙና እድሉ አሁን እየተመሰረተች ባለችው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የትግራይ ህልውና ለይተን የሚባል ነገር ለይተን ማየት አንችልም፡፡ ቀጣይ አቅማችንና ህይወታችን እዛው ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ብቻችን የምናመጣው አይሆንም፡፡ ከሌሎች ህዝቦች ጥምረት ፈጥረን ነው ማምጣት የምንችለው፡፡ ጥቅምን መሰረት ያደረገ አንድነት ፈጥረን ስርዓቱ ስር እንዲሰድ ማድረግ ነው፡፡ ፀረ ድህነት ትግል ነው የሚፈጠረው፡፡ ሌላ አማራጭ ማየትም የውድቀት አማራጭ ነው፡፡

ውራይና፡– በትግራይ ውስጥ ያልተሟላ የልማት ጥያቄ አለ፣ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎችን አሉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ተወላጅ እየደረሱ ያሉ ችግሮች አሉ፡፡ ይሄን መሰረት በማድረግ የሚታዩ የአመለካከት ለውጦች በትግራይ ውስጥ አሉ፡፡ አንዱ ኢ/ያ የሚል ሃሳብ እንተወው የሚል ነው፣ አግአዝያን የሚል አዲስ ማንነት በትግርኛ ተናጋሪዎች አሉ፡፡ ሁለተኛ ከነዚህ ጋር እንዴት ብለን እንኖራለን የሚል አመለካከት አለ፡፡ ከ11ዓመታት በፊት አግአዝያን የሚል እንቅስቃሴ ሲመጣ ብዙም ትኩረት አልነበረውም፡፡ ከጎንደር ክስተት ቀጥሎ ግን አብዛኛው ወጣት የአግአዝያን አንልነት ቅፅ የሚሞሉ አሉ፡፡ ይሄ አሁን ያለውን ስጋት የፈጠረው ነው፡፡ ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ወዴትስ ይወስዳል? አንተስ እንዴት ታየዋለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡-  ቀደም ሲል ገልጨዋለሁ፡፡ በሽግግር ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ችግር የሚፈጠረው የመሪነት ቀውስ ሲኖር ነው፡፡ ስለዚህ በዋናነት አመራርነት ተስተካክሎ ለተፈጠረው ቀውስ ሊሻገረው ይገባል (አለበት)፡፡ ይሄም ነው ተስፋ መቁረጥ እያመጣ ያለው፡፡ በዋናነት ግን ህብረተሰቡን ወደኃላ መጎተት ነው፡፡ በማህበረሰብ አካሄድ እያደግን መጥተናል፡፡ ኢትዮጵያ የሚል ነገር እኮ ተመስርቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ዞናዊ ወይም አፍሪካዊ ውህደት ነው ሊኖር የሚችለው፡፡ ምክንያቱም ይሄ የዞን ውህደት የሚጠቅመን ለገበያ ነው፡፡ ሲፊ ገበያ የሌለው ደግሞ ሊኖር ወይም ማንነቱን ሊጠብቅ አይችልም፡፡ አሁን በብሔር የተመሰረቱ ገበያ የለም፡፡ ገበያ አለም አቀፋዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሚል እንተወውና ለሌለ የምንፍጨረጨርበት ጊዜ ነው፡፡ ለምሳሌ ቻይና ቻይና የሆነችበት የራስዋ የሆነ ትልቅ ገበያ ስላላት ነው፡፡ በእርግጥ ጥቂት ሆነው በታሪክ አጋጣሚ እድገት የፈጠሩ አሉ፡፡ እንደ ታዋን ሲንጋፖር የመሳሰሉ፡፡ በአውሮፓም እንደዚህ የነበረ ነው፡፡ አውሮፓም ወደ አንድ እየተሰባሰቡ ናቸው፡፡ አሁን ግን የእንግሊዝ መውጣት እየፈተነው ነው፡፡ ይሄም ቀደም ሲል ያቀረብኩት ነው፡፡ ይሄ ክልከላ (protectionism) የሚባል ወይም ባልከናይዜሽን የሚባል ማለት ነው፡፡

ሰዎች በዓለም ደረጃ ለመተሳሰር የሚጠቀሙበት ለምሳሌ በሳይበር አንድ ነው፡፡ አሁን የትግራይ የምትል ሳይበር ብቻ ገንብተህ ምን ታገኛለህ? ምን እውቀት ነው ያላት፣ የሆነ የትግራይ ማንሸራሸር ትችላለህ፡፡ ገበያ ግን አላት ወይ? ከዓለም ጋር የተሳሳረ መስተጋብር ሊኖር ይገባል፡፡ ሳይበር አለም ዓቀፍ መተሳስር ነው፡፡ ደስተኛም አትሆንም፡፡

ስለዚህ ይሄ ወደኃላ የምትመለስበት አይደለም፡፡ ወደኃላ መመለስ ማለት ወደ የብሔርህ ተጠግተህ፣ አጥር ፈጥረህ በቋንቋ ብቻ የሆነ ነገር ማድረግ አይደለም፡፡ በአህጉራዊና ሀገራዊ መተሳሰር ማንነትህ መጠበቅ አንድ ጉዳይ ነው፡፡ ኢ/ያ ከትግራይ ወይም ኦሮሞ ማንነት ውጪ ኢ/ያ አይደለችም፡፡ በማንነት ደግሞ መበላለጥ የለም፡፡ ይሄ የህዝብ ብዛት ጉዳይ አይደለም፡፡ በእርግጥ የህዝብ ብዛት የተከማቸ የገበያ ሀብት ሊሆን ይችላል፤ ገበያ ማለት ግን አይደለም፡፡ ይሄ የህዝብ ብዛት ይፈውዳል መደራደሪያ አስተሳሰብ ነው፡፡ ብዙ ወይም ጥቂት ህዝብ አለን ማለት ፊውዳላዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ፊውዳላዊ አስተሳሰብ ስንት ሰራዊት አለህ፣ ስንት ጋሻ መሬት አለህ ነው፡፡ አሁን በአለም እውቀት ነው ወሳኙ፣ ብዛት አይደለም፡፡ ጥቂት ሆኖ ወደ እውቀት ፣ ብዙ ሆኖ ወደ ገበያ ካልተቀየረ ዋጋ የለውም፡፡

ስለዚህ ቀጣይ ሂወታችን በመተሳሰር ነው የሚመሰረተው፡፡ ለዚህ ደግሞ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ ሁሉም የአ/ያ ህዝብ ዋጋ ከፍለውበታል፡፡ የትግራይ ህዝብም ዋጋ ከፍሎበታል፡፡ በፍላጎት ነው በጋራ አብረው ያሉት አንዱ አፍራሽ ሌላኛው ገንቢ ሊሆን አይችልም፡፡ በመፈቃቀድ ነው አብረው እየኖሩ ያሉት፣ በዚህ ደግሞ ረዥም ተጉዘዋል፡፡ ትልቅ ተስፋመ፣ አለ ለወደፊት፡፡ ስለዚህ ይሄ የአግአዝያን እንቅስቃሴ የህብተሰቡ እድገት ወደኃላ መመለስ አድርጌ ነው የማየው፡፡ ተራማጅ አይደለም፣ ጎታች ነው፡፡ ይሄ ወደኃላ መመለስ ነው፡፡ በዚህ አንፃር (አግባብ) ነው ማየት ያለብን፡፡ በስሜት ቀውስ ተገፋፍተህ ወደ ተሳሳተ መንገድ ልትሄድ፣ የህብረተሰቡ ባህሪያዊ እድገት ወደ ኃላ መመለስ የለብህም፡፡ ካልፈለክም አይሳካልህም፡፡ ሁለተኛ ብዝሀነት ልትቀበል አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎም የምመሰርታት ግዛት የሚላት ለምሳሌ አግአዝያን እንደሚሉት ለሙስሊም፣ ኩናማ፣ ዓፋር የሚቀበሉ አይደለም፡፡ ቀጥሎም ወደታች ወርዶ እኔ መሐል ነኝ የሚል ሊኖር ነው፡፡ ለምሳሌ ተስፋፅዮን አክሱም የስልጣኔ ማእከል የነበረች ፃዕዘጋ ነው የሚለው፡፡ ስለዚህ ሄዳ ሄዳ ወደ ፃዕዘጋ ነው የምትሄደው፡፡ ይሄ በጣም መውረድ ማለት ነው፡፡ ይሄ አፍራሽ ነው፡፡ የኃላቀርነት መግለጫ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከሚያስበው ደረጃ ወርደህ መገኘት ነው፡፡ ይሄ እንዳለሁም ግን ማንነትህና ታሪክህ ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ በደንብ ታሪኮችንና ማንነታችን ማጥናት አለብን፡፡ እሱ ግን ይሄ የጋራ ሀገር ወይም ዓለም የምንለው ባለው አስተዋፅኦ ነው የምናየው፡፡ ለብቻችን ስለማንኖር፡፡ ይሄ እንደ ኤሊ ወደ ሼል መሸጎጥ ማለት ነው፡፡ ኤሊ ጭንቅላቱን ወጣ ያደርጋል ሁኔታዎች እማይጥሙት ከሆነ ተሳክቶ ይገባል፡፡ ተተክሎ መተኛት፣ ከዓለም ተለይተህ ነው፡፡ ይሄ ሽንፈት ነው፡፡ ሌላ ተስፋ መቁረጥ እየተባለ ያለው በጥልቀት ማየት አለብን፡፡ ለምን ተስፋው በራሱ አይሆንም፡፡ ራሱ ተስፋ ነኝ ብሎ የማይነሳው፣ እለውጠዋለሁ ብሎ ለምን አይነሳም፡፡ የመጀመሪያ መፍትሄው እሱ ነው፡፡ በእኔ አስተሳሰብ ራሱ በራሱ ተስፋ ያደረገ ወጣት ነው ሀገር መለወጥ የሚችለው፡፡ ከዚህ አልፎ ይሄ ድርጅት ህወሓትን መንግስት ራሱ በራሱ የሚያርምበት ስርአት ስላለው ተስፋ መቁረጥ ያለበት አይመስለኝም፡፡ በዚህ መሰረት በራሱ ማዕቀፍ ማስተካከል አለበት ከሁሉም በላይ ይሄ ዓላማ ያዋጣናል ወይስ አያዋጣንም ነው መሆን ያለበት፡፡ አሁንም ወደፊት ይወስደናል አይወስደንም የሚል ነው መሆን ያለበት ውይይቱ፡፡ የትግራይ ህዝብ ይሄን ዓላማ ለመፈፀም አደረጃጀት አለ፡፡ ህወሓት ከሌላ ለየት የሚያደርገው በትግራይ ቅቡል ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ከግለሰቦች ጋርም አያስተሳስረውም፡፡ ከዚህ አልፈህ ግን ስልጣን ላይ የወጣ ኃይል ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት መደባላለቅ አለ፡፡ ራሱ ሊያጠራ ይገባል፡፡ ወደ ዓላማው ለትግራይ ህዝብ የሚወግን ሃይል ተለይቶ መውጣት አለበት፡፡ አሁንም ትግል ያስፈልጋል፡፡ እኔ እንደሚስተካከል ተስፋ አለኝ፡፡ ተስፋ ብቻም ሳይሆን ወደኃላ የሚመለስ አይሆንም (አይደለም)፡፡ ምክንያቱም ይሄ መስዋዕትነት የከፈለ ህዝብና የተጋደለ ታጋይ አብዛኛው በህይወት አለ፡፡ ወደፊት ሊመርሽ የሚፈልግ ወጣትም አለ፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ እንደፈለገ መጨማለቅ የሚፈልግ ሃይል መራመድ የሚችል አይደለም፡፡ ለጊዜው ግን ህመም (pain) ሊፈጥር ይችላ፡፡

ውራይና፡- አንድ ነገር ግን ይሄ አግአዝያን እንበለው ያለው እንቅስቃሴ አንድ መፈታት ያለበት

ነባራዊ ሁኔታ ግን አለ፡፡ በመሐላችን ያለው ግንኙነት፣ በአንዳንድ ያለው ማየት  ሳይሆን፣ በእርግጥ ትግርኛ መናገር፣ መተጋገዝ፣ ባህላችን ታሪካችን ማንነታችን ማሳደግ እንዳለ ሆኖ በትግራይና ኤርትራ ህዝቦች መሐል ያለው ያልተፈታ ችግር ብናስበውም ጥሩ ነው፡፡ ስለዚህ ከገበያ መፍጠርና የስነ ልቦና ግንኙነት ያለው ጉዳይ እንዴት ታየዋለህ?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- አግአዝያን የሚለው የተወሰነ ሰበካዎች አንብቤ ነበር፡፡ አንድ ለየት አድርጎ ያስቀመጣት አሁን ባለው ዘመን በብሔር ግንባታ መሰረት ነው፡፡ ማንነትን መሰረት አድርጎ ስልጣኔን የማይገነባ ደግሞ ጠፊ ነው፡፡ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛ የተወለዱበት ቄያቸው (ሀገራቸው) አግአዝያን ተጋሩ አሁን ኤርትራ የምትባል ነች፡፡ መጀመሪያ አክሱም፣ ዓድዋ ነበረ፣ በኃላ ወደ ፃዕዛጋ ቀጥሎ ማእከል ነበረ የሚል አለው፡፡ ስለዚህ እነዛ እስከ ማይጨው፣ ራያ፣ ወልቃይት ተዘርግተው ያሉት ተጋሩ ወደ መነሻ ቦታቸው ኤርትራ መመለስ አለባቸው የሚል ነው፡፡ ስለዚህ እነዛ የራሳቸው ያልሆነ ቦታ ይዘው ያሉት ደግሞ ማኖሪቲ መሆን አለባቸው የሚል ነው፡፡

ሁለተኛ አግአዝያን በመሰረቱ የኦርቶዶክስ ታሪክ ነው ያለው የሚል አለ፡፡ ይሄ ተረት ተረት ነው እያመጣ ያለው፡፡ እነዚህ ራሳቸውን ወስደህ ይሄ እንቅስቃሴ ፀረ-ህዝብ መሆኑን ለማወቅ፣ ፀረ አድገት መሆን ማወቅ የግድ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያ የሚባል ሁሉም የገነባት ሀገር ነች፡፡ ትግሬውም የራሱ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይሄ ግን ያለውን ችግር ማዕከል አድርጎ ከሌሎች ህዝቦች ለመበጣጠስ እና ወደኃላ እንዲመለስ የሚያደርግ ነው፡፡ ሌላ ኑ ተመለሱ የሚል ጤና የለውም፡፡ ይሄ ትግራይ እየተባላ ያለው ህልውናውን መካድ ነው እየሆነ ያለው የሆነ ህብረተሰብ ጂኦግራፊ አይደለም የሚወሰነው በዛ ቦታ የሚኖር (የሚሰፍር) ሰው ነው የሚወሰነው፡፡ ስለዚህ በታሪካዊ ሂደት ትግራዋይ የሚባል ሰፍሮበት ያለው ጂኦግራፊ ተሳስሮ ነው የሚታየው፡፡ ስለዚህ አገሮች የሚባል አርቴፊሻል ክፍፍል ዳር ድንበር አለ፡፡ በአፍሪካ ያሉት ዳር ድንበሮች የውጭ ገዢዎች የፈጠሩት ነው፡፡ እነዚህ ዳር ድምበሮች በራሱ ተፈጥሮአዊ ሂደት መፍረስ አለበት፡፡ኢኮኖሚያዊ ውህደት ሲፈጠር ደግሞ የሚፈርስ ነው፡፡ አዎንታዊ መሳሳብ ካለ ነው፡፡ ለምሳሌ በኤርትራ አርቴፊሻል ክፍፍል አለ፡፡ ለምሳሌ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ሊያብሩ ከሆነ ኢትዮጵያ ሊስባቸው ይገባል፡፡ ኤርትራም ከኢትዮጵያ መሳብ አለበት፡፡ ስለዚህ ይሄ ድንበር ትርጉም ወደሌለበት መቀየር አለበት፡፡

ይሄ በአውሮፓ ለምሳሌ ሊግዘንበርግ ከወሰድን ከ ቤልጄም፣ ፈረንሳይ ያላት አርቴፊሻል ድንበር ጠፍቷል፡፡ ሁለት መቶ ሺ የሚሆኑ ፈረንሳውያን ቤልጄማውያን በሉክዘምበርግ እየሰሩ ይውላሉ አገራቸው ደግሞ ተመልሰው ያድራሉ፡፡ እነዛ የሉግዘምበርግ ደግሞ በሉግዘምበርግ ይሰሩና ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ ይኖራሉ፡፡ ይሄ ድንበር ትርጉም ወደሌላው ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ ለቀጣይ ይሄ የመጣበት ምክንያት የኢኮኖሚ ውህደት ስላለ ነው፡፡ በእያንዳንዱ መሳሳብ አለ ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ መተሳሰር አለ፡፡ ይሄ አንድነት አንድ ባህል፣ አንድ ቋንቋ አለን የሚለው እዚህ ላይ በደምብ ይሰራል ለትስስሩ ያወፍረዋል፡፡ እኛ በፊት አግአዝያን ስለ ነበርን ስለዚህ ወደዚህ እንምጣ የሚል ጎታች ከመሆኑ አልፎ የህ/ሰቡ ተፈጥሮአዊ የውህደት ሂደት የሚፃረር ነው፡፡ አሁን ገበያ ስለሆነ ያስተሳሰረን ገበያው መፈጠር አለበት፡፡ ይቅር በኢ/ያ እና ኤርትራ መሐል በታሪክ የተሳሰረ ህዝብ፣ በሱዳንና ኢ/ያ በኢ/ያና ጅቡቲ ያለው ድንበር በሂደት ይፈርሳል፡፡ ይሄን በሚጠቅም መንገድ ነው ታሪኩ መታየት ያለበት፡፡ ይሄም ነው ሕ/ሰቡን ወደፊት ሊያራምደው የሚችለው፡፡ ስለዚህ ስለፈለከው አይመጣም፡፡ ኤርትራና ኢ/ያ እንደዚህ ሊሆኑ ይገባል፡፡ አንተ ልትፈልግ ትችላለህ ሌላኛው ወገንስ ይፈልጋል ወይ? በዚ ደረጃ ዝግጁ ነው ወይ? ህዝቡ አይደለም፣ ስልጣን ያለው በስልጣኑ ላይ ያለው ኃይል ነው፡፡ ስልጣን ላይ ያለው ሐይልስ ባህሪው ምንድ ነው? በባህሪው ጥገኛ እስከሆነ የራሱ ፍላጎት እንጂ የሀገር ወይም ቀጣይ የሚያስቀድም ኃይል ስለሆነ ውህደቱ ዝም ብሎ አይመጣም፡፡ በሂደት ግን ይፈጠራል፡፡ የጭንቀት ነው የሚመስለኝ፡፡ በቀጣይ ፀረ ሰላም ብሎ ከተሳካ ደግሞ ነገ ጠዋት ይሄ ጴንጤ ነው ይሄ የሆነ ነገር ነው እየተባለ ወደ መጠፋፋት ነው የሚሄደው፡፡

ውራይና፡- ጥሩ ይሄ ወደፊት ለማየት መጀመሪያ ስለ ቀጣይ ጉዳይ ስንናገር አጠር ባለ ልንደርስበት ወደ ምንፈልገው የኢ/ያ ሀገር ግምባታ እንድንጓዝ የታሪክ ልዩነት፣ የኢኮኖሚ ትስስር አለመፈጠሩ እንደ ትልልቅ ምክንያቶች ቀርቧል፡፡ ግን ደግሞ ልንደርስበት የምንፈልገው ጉዞ ምንድ ነው? በሀገር ግንባታ ስምምነት የለም፡፡ የምንፈልጋት ኢ/ያ በጋራ ዓላማ ራዕይ አስቀምጠን መንገድ እንለያይ ለሷ የሚያደናቅፍ ካለ በጋራ እንምታው፡፡ ስለዚህ ይቺ የምንመኛት ኢ/ያ የት ነው ያለችው እያልኩ ያለሁት

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- አሁን ኢ/ያ ወዴት እየሄደች ነው የሚለው ተለይቷል፡፡ በጥንቃቄ ማኒፋክቸሪንግ መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚ መከከለኛ ገቢ ተብሎ የተቀመጠ ነገር አለ፡፡ ለ ዘላቂ ደግሞ ይሄ ተነሳሽነት እንደነ ቻይና የሄዱበት ወደ በለፀገ ህ/ሰብ መሸጋገር ነው፡፡ ይሄ በኢኮኖሚ አንፃር ከየት ወዴት እንደምንሸጋገር በማህበራዊና ፖለቲካዊ መተሳሰርም ከየት ወዴት እንደሚሸጋገርም አስቀምጧል፡፡ ይሄ ለምሳሌ ፌደራል ስርዓት፣ ማንነት መሰረት ያደረገ ፌደራላዊ ትስስር አስቀምጧል፡፡ የራስ በራስ የመወሰን ያለው፤ ትርጉም ወደ ሌላቸው ደረጃ ሊወርዱ ነው፡፡ ልክ ቀደም ሲል በአውሮፓ ያለው የህዝብ ትስስር የበለፅኩት ማለት ነው፡፡ ትግራዋይ፣ አማራው፣ ኦሮሞ የሚል ንግግሮች ትርጉም ወደ ሌለው ደረጃ ይወርዳል፡፡ አርቴፊሻል ድንበር አለ፣ በታሪክ የሚመጣ ማንነትም አለ፡፡ ይሄ ማንነት ይጠፋል ማለት አይደለም፡፡ የሁሉም ማንነት ዕድል አግኝቶ የሚበለፅግበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ የአማራ፣ ትግራዋይ ኦሮሞ ማንነት ግን የብሄር መሸፈኛ ሳይሆን እንደ ገበያ ማስተሳሰሪያ ወይም ሀብት ወደሚሆንበት ደረጃ ይሸጋገራል፡፡

በፊልም ኢንዱስትሪ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎት፣ ዕውቀት፣ ታሪክ፣ ቱሪዝም ሰናይ፣ ለምሳሌ አሁን በትግራይ ያለው ታሪክ ለዓለም ተሸጦ ለኢ/ያ ገቢ ከሆነ የትግራይ ታሪክና ማንነት ለኢ/ያ ሀብት ሁኗል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ድንበር በሂደት ይፈርሳል፣ ጠንካራ ትስስርም ይፈጥራል፡፡ ይሄ የሚመጣ ግን ሁሉም አከባቢዎች የየራሳቸው ሀብት ሲፈጥሩና መተሳሰብ ሲመጣ ነው፡፡ ይሄ ዝም ብሎ በአስተዳደር የሚመጣ ሳይሆን በኢኮኖሚ ትስስር የምትፈጠር ኢ/ያ ነው፡፡ በኢኮኖሚ ትስስር የተፈጠረም የማንነት ትስስር ይፈጥራል፡፡ ከዚህ አልፎም ከዞናችን ትስስር ያላት ሀገርም ትሄዳለች፡፡ ወደዚህ ለመድረስ የሚከፈል መስዋዕትነት ይኖራል፡፡ በዋናነት ዕድገት የሚመጣው በእውቀት ነው፡፡ ዋናው ዋስትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብና ኢኮኖሚ ሲገነባ ነው፡፡ ይሄ አብሮ ነው ሊሄድ የሚገባው፡፡ በእኔ አስተሳሰብ ቴክኖሎጂ፣ ይሄ አሁን ያለው የሳይበር አቅም ከዛም ከዞንም ትስስር ያላት ሀገር ትሆናለች፡፡ ይሄ ቴክኖሎጂ ሳይበር ለዝላይ ልንጠቀምበት እንችላለን ከፊታችን ያሉት ችግሮችም ለመሻገር ዕድል ይሰጠናል፡፡ ስለዚህ የበለፀገች ኢ/ያ ማለት የበለፀገች ትግራይ፣ የበለፀገች ኦሮሚያ የበለፀገች አማራ እና ሌሎች ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትግራይ እዚህ ላይ ታያታለህ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የትግራይ ወጣት የእውቀት ቢዝነስ የኢኮኖሚ ሞተር ሁኖ ስታየው ማለት ነው፡፡ ታሪክ፣ ቅርስና… ትግራይ ለቱሪዝም ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ከርል ማርክስ የተወለደበት አንድ ትንሽ ከተማ ጀርመን ውስጥ አለች፡፡ በዓመት 3.5 ሚሊዮን ጎብኝዎች ያይዋታል፣ ይቀላቀላታል ትንሽ ከተማ ነች ግን የ19 ክ/ዘመን ቅርሶች አሉዋት፡፡ እንደነ ናፖሊዮን ጦርነት የሚካሂዱበት ቦታም ነች፡፡ እኛም የረዥም ክ/ዘመን ታሪክ ነው ያለን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተፈፀሙ ናቸው፡፡ እኛ የሰው ልጅ ስልጣኔ ብለን የምንገልፀው ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ በትግራይ የኢኮኖሚ ዋልታ ሊሆን ይችላል ነው የተከማቸ ሀብት አለ ነው፡፡ ይሄ ሊሆን የሚችለው ግን ዕውቀት መሰረት ያደረገ አካሄድ ካለ ነው፡፡

ውራይና፡- እንደ ተጋሩ የኢ/ያ እንቅስቃሴ የየራሳችን አስተዋፅኦ ስናደርግ በትግራይ ስለሚኖረው ጉዳይ ከተጋሩ በላይ ሌሎች ሊቆረቆሩ የሚችሉ አይሆንም፡፡ ችግሮቻችን ለይተን ፈተን አቅማችን በሚገባ ተጠቅመን ወደ የጋራ ፌደሬሽን ኢ/ያ እንጠጋለን ማለት ነው፡፡ አሁን ባለንበት ግዜ በዚህ መሰረት ነን እንደ ተጋሩ ማሰብ ያለብን የሚል ሐሳብ አለኝ፡፡ ስናስበው ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ ቢሮክራሲ ያለው መንግስትና ድርጅት አለ ይሄ እንዳለ ሁኖ እንደ ማህበረሰብ ግን ይሄን እግረ መንገድ ይዞ የሚሄድ፣ የራሳችን ዓቅም የሚጠቀም የሚያስብ ቡድን ወይም ማዕከል ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ በታሪካችን፣ ቱሪዝም ወደ ኢኮኖሚ ጥቅም ለመቀየር ምን ማድረግ አለብን፡፡ የተቀናጀ ዘላቂ ልማት ሊያስቡ ሊያዘጋጁ የሚችሉ የተመረጡ ተጋሩ ሊኖሩ ይገባል፡፡ የተመረጡ የትግራይ ልጆች ቁጭ ብለው በነፃነት ሊያስቡ ይገባል፡፡ የመንግስት መሰረታዊ ፖሊሲም ወደ ተጨበጠ የሚቀይር እንቅስቃሴ ሊኖሩ ይገባል የሚል ሓሳብ አለኝ፡፡ ይሄ ጉዳይ እንዴት ታየዋለህ፡፡

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ትችላለህ ይሄ በትግራይ ውስት ኢንቨስትመንት ሊካሄድ ከሆነ የግድ ኢንቨስተሮች ተጋሩ መሆን አለባቸው እንላለን ማለት አይደለም፡፡ ኢ/ያውያን ይቅርና ሌሎች የዓለም ዜጎችም ሀገራችን ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ እያጣርን ነው ያለነው አሁን ያለው አጥር ሰብረን እንድንሄድ ዋናው ሞተር ህዝቡ ነው፡፡ እዚህ ህዝብ የምታመጣው አሁን ነው፡፡ ከዛ የህዝቡ ስደተኛም አለ፡፡ አሁን እስራኤል በአይሁድ ስደተኞች ነው ጠንካራ የሆነችው፡፡ ምክንያቱም ይሄ በስደት ላይ ያለው ኃይል የተለያየ ተሞክሮና እውቀት ስለሚያንቀሳቅስ ነው፡፡ በተጨማሪ ካፒታልም አለው፡፡ ስለዚህ ነዋሪው ህዝብ ይሄ ከህዝብ ተሰዶ ያለውና ከሌላ ዓለም የሚመጣ አካል ነው በህብረት የሚያለማው፡፡ ማለት የሆነ ሰራ ሊሰራ ከሆነ ሊወሰን ሊገደብ አይገባም የተጋሩ የሌላ ብለን ከወሰድነው በጠባብ ምህዋር የሚሽከረከር ነው የሚሆነው፡፡

ዋናው ነገር በትግራይ ውስጥ የኢንቨስትመንት ዘመቻ መኖር ካለበት ወይም የህዝቡ የዓቅም ፀጋዎች ሊበለፅግ ከሆነ ምቹ ሁኔታዎች ወይም ሳቢ መሆኑ ነው፡፡ በትግራይ ኢንቨስት የሚደረግ ስበት እንዲኖረው ስራ ሊሰራ ይገባል፡፡ ኢንቨስትመንት ሊያመጣ የሚችል ምቹ ፖሊሲ፣ የአሰራር ስርዓትና ቢሮክራሲ ሲኖር ነው፡፡ በትግራይ ሊሳብ ከሆነ ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኑ ሳይሆን መቀየር አለብን የሚል ራዕይ ያለውና እልህ/ቁጭት/ ያለው በመሰለው መንገድ ሲንቀሳቀስ ነው፡፡ ይሄን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ሁኔታዎች ሲኖር ነው፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ ሲታይ አደረጃጀቶቹ ብዙ ናቸው ማለቅያ የላቸውም፡፡ በተለያየ መንገድ ለምሳሌ በአክሱም ስልጣኔ ወቅት ወይም በትግራይ ህዝብ ትግል ወቅት የህዝብ አስተዳደር ምክር ቤት ከወሰድክ የነበረው ተሞክሮ ለአፍሪካ መሸጥ የሚችል ነው፡፡ በሳይበርም ተመሳሳይ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ብቻ ብዙ ዩኒቨርስቲዎች ምርምር ማካሄድ ይችላሉ፡፡ ሌላ ደግሞ ግዕዝ መሰረት አድርገህ ብዙ መስራት ይቻላል፡፡ በሌላ መንገድ ደግሞ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ብዙ ስታርትኦፕ፣ ብዙ አደረጃጀቶች ሊፈጠሩ ይገባል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ተፈጥሮአዊ ሂደት ነው፡፡ ይሄን ተፈጥሯዊ ሂደት የሚጠልፉ መሰናክሎች ግን ሊጠረጉ ይገባል፡፡ እኛ ይሄንን ነው ማድረግ ያለብን፡፡

ውራይና፡- ምን ዓይነት መሰናክሎች ናቸው አንተ እያልካቸው ያለኸው?

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- የአስተሳሰብ መሰናክሎች ናቸው፡፡ አንደኛው ጠባብ አመለካከት ነው፡፡ ትግራዋይ ካልሆነ ሌላ በትግራይ ውስጥ ኢንቨስት ሊያደርግ ወይም ከኛ ጋር ሊያብር አይችልም የሚል ነው፡፡ ትግራዋይ ብለህም የእከሌ አውራጃ ካልሆነ ከኔ ጋር በጋራ መስራት መሄድ አይችልም የሚል ነው፡፡ ይሄ መዋቅራዊ ችግር የሚፈጥር ነው፡፡ በጣም አደገኛና ኃላቀር አስተሳሰብ ነው፡፡ ቢዝነስ አለምአቀፋዊ ነው፡፡ በእርግጥ ተመሳሳይ ሰዎች ናቸው ወደ አንድ መምጣት ያለባቸው፡፡ ተመሳሳይ ሰዎች ግን ተጋሩ በመሆናቸው የሚመጣ አይደለም፡፡ ትስስር መፍጠር አለብን፡፡ ልንዘል ይገባል፡፡ ዝምብለን በአንድ ቦታ ብቻ መታጠር የለብንም፡፡ ይሄ ይቅርና ከኢትዮጵያዊያን ከሱዳን ከኤርትራ ጋር መተባበር አለብን፡፡ ከዚህ አልፈን ከሌሎቹም ጋር በተመሳሳይ መልኩ፡፡ ስለዚህ ክፍት አእምሮ መኖር አለበት፡፡ ስታስብ መለኪያህ መስተካከል አለበት፡፡

በሌላ መንገድም ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑ አስተሳሰቦች መፍጠር አለባቸው፡፡ የተለያየ አስተሳሰቦች (ሐሳቦች) የማያስተናግድ፣ ሐሳቦች ዝቅ የሚያደርግ የሚፈርድ፡፡ ስለዚህ ዋናው መሰናክል አስተሳሰብ ላይ ነው ያለው፡፡ ይሄ ከሆነ ሕብረት (synergy) መፍጠር አንችልም፡፡ ትልቁ መሰናክል ይሄ ነው፡፡ ነፃ መሆን አለብን፡፡ ነፃነታችን ማወጅ አለብን፡፡ ሌላኛው መሰናክል ማብቃት (empowerment) የሚባል ነው፡፡ ወጣቱ በሌላ ሳይሆን በራሱ ነው መብቃት ያለበት፡፡ ሓላፊነት መውሰድ አለበት፡፡ ራስን ማብቃት (self empowerment) ማስኬድ አለበት፡፡ ይሄ ከሆነ ከፊቴ የሚያደናቅፈኝ ሐይል የለም፣ ካም እሻገረዋለሁ፣ ራሴ የምቀርፃት ሀገር ወይም ሂደት አለ ብሎ የሚያስብና የሚያምን ወጣት፣ ራስ መተማመን ያለው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ እንደዚህ እኮ አደረጉ፣ አባረሩን እኮ፣ መስራ አልቻልንም እያለ ምክንያት የሚፈጥር ሐይል ካለ የመከነ ወጣት ነው፡፡ ከዛ ያ ቢሮክራሲ በአሰራር ፈጣን፣ በቅንነት የበላይ መሆን አለበት፡፡ በእርግጥ ይሄ የተበላሸ እእምሮ ወይም ድህነት በሰፈነበት ሁኔታዎች ዝም ብለህ የምታገኘው አይደለም፡፡ ግን ተልዕኮ ያለው ሓይል በዚኅ ስኩቻ አይገባም፡፡ መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ ነው ሲቪክ ማሕበራት ዝም ብለው የሚመሰረቱ አይደሉም፡፡ ነፃ ሰው ነው የሚፈራቸው፡፡በዘር፣ በብሄር ተመስርቶ የሚያስብ ወይም ራ መተማመን የሌለው ሰው ሲቪክ ማሕበራት መመስረት አይችልም፡፡ እንዲህ ያደርጉኛል፣ ያሩኛል እያለ የሚያስብ ሲቪክ ማሕበራት ሊመሰርት አይችልም፡፡ ሂደት ይጠይቃል ነው፣ ግን ነፃ የሆነ ሰው ያፈልጋል፡፡ ደፋር፣ ቅንና ተነሳሽ ሰው ያፈልጋል፡፡

ውራይና፡- ወጣቱ ምን ማድረግ እንዳለበት በተደጋጋሚ ነግረኸኛል፡፡ ካንተ ትምህርትና ልምድ ጋር ተያይዞ በትግራይ ውስጥ በሚደረገው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ከማማከር በዘለለ በተግባር እንደምትሳተፍ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የሰጠኸኝ ቃል መጠየቅና አክብሮች እያደነቅኩ፤ በወጣቶች፣ ዕውቀትና ሳይንስ ዙርያ ያላነሳናቸው ነጥቦች ምናልባት ካሉ ዕድል ልሰጥህ፤ ከሌለህ ግን በጣም ነው የማመሰግንህ፡፡

ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን፡- ውራይና የትግርኛ ቋንቋና ትውፊት በማስተዋወቅ ያለች መድረክ ናት፡፡ ወይን አለች፡፡ ከዛ በፊትም በትግሉ ጊዜ የሚፃፍ ፅሁፎች ነበሩ፡፡ ዓላማው ሁሉም አይነት አስተሳሰቦች አቀራርበህ ውይይት እንዲደረግ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባህላችን ለማሻሻልም ጭምር ነው፡፡ ይህ የወገን፤ ይህኛው የባዕድ ብለን ለመለያየት ሳይሆን የሃሳብ መድረክ ለመፍጠር ነው፡፡ አንድ ሃሳብ ከሌላ ሃሳብ ጋር በማጋጨት የተሸለ ሃሳብ እንዲፈጠርና ተቀባይነት ያገኘው ሃሳብ ይዞ ለመቀጠል እንዲያስችል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ይህ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ አንዱ አንዱን የመጥለፍ የተለመደ ጉዳይ አለ፡፡ ስለዚህ ውራይና የፋይናንስ ነፃነቱ ጠበቅ መጓዝ አለበት፡፡ ለወጣቱ የትግል መድረክ፣ ልምድ የሚቀስምበት መድረክ ሆኖ እያገለገለች ስለሆነ በእውነቱ ውራይና ምስጋና ይገባታል፡፡ ይህ አንድ አስተዋፅኦ ነው፡፡ በቀጣይነትም ሚዲያው ተጠናክሮ እንዲወጣና እንዲቀጥል የማድረግ ትልቅ አበርክቶ አለው፡፡

ሌላው ጉዳይ ግን ከፍ ባለ ቴክኖሎጂ (high tech) ላይ መሰረት ልናደርግ ይገባል፡፡ ዋስትናችን እሱ ነው፡፡ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርት ሊኖረው ከፈለግህ ቴክኖሎጂ መጠቀም ይገበሃል፡፡ ከፍ ያለ ቴክኖሎጂ ስልህ የተወሰነ ቴክኖሎጂ ማለቴ አይደለም፡፡ ለምሳሌ መሬት የሚመለከት ምርጥ ዘር መጠቀም ከፈለግህ መሬቱ ምን አይነት ከሚካል እንደሚያስፈልገው፣ ምን አይነት አፈር እንዳለው ወዘተ የምታውቀው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው፡፡ በመሬት ላይ የፈለገኸውን አትዘራም፤ ማወቅ ይጠበቅበሃል፡፡ በርግጥ ምርጥ ዘር የምንላቸው ራሱ በቴክኖሎጂ ተዳቅለው ነው በአለም ገበታ ተወዳዳሪ የሚሆኑት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመሬት የጠል መጠንና ቁጥሩና፣ የዘር ጤናማነት ቁጥጥር ለማድረግ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ያስፈልገዋል፡፡ በመቀጠል በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆኑም መገበያየት ከፈለግህ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ መጠቀም አለብህ፡፡ በሁሉም መስክ ቴክኖሎጂ አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንድ የመጀመር ምልክቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ በራያ የተጀመረ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም እርሻ አለ፡፡ እነዚህ በትግራይ ይሁን በአ/ያ ደረጃ መስፋፋት አለባቸው፡፡ ይህ ኢንፎርሜሽን ማለት ነው፡፡ ሌሎች ሃገሮች ስታንዳርድ ነው የሚያስቀምጡት፤ በተቀመጠ ስታንዳርድ የተመረተ መሆን የሚያረጋግጥ የሰራ ሂደት ነው ያላቸው፡፡

ከዚህ ውጭ በሆኑትን መሰረት አለብን፡፡ ትግራይ ውስጥ ብዙ የኤሌክትሮኒክስ፣ ሶፍትዌር፣ ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በአገልግሎት ስታርት ኦፕ ያስፈልጉናል፡፡ የአመራር ስርአታችንም መቀየር አለበት፡፡ የተጣራ መረጃ ማግኘት አለብህ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጥራት ያለው ዕቅድ ወይም ስትራተጂ እንዳታወጣ ዕንቅፋት የሚሆንህ የተጣራ መረጃ አለመኖሩ ነው፡፡ የውሸት መረጃ ካለህ መሰረት አትችልም፡፡ በትግራይ ውስጥ መሰኖ የትና ስንት አለ ብትል በኤርያል ጅኦግራፊ ወይም በሳተላይት ምስል ማወቅ ትችላለህ፡፡ እየዞርክ ማየት አይጠበቅብህም፡፡ የእርሻ /የአዝርእት በሽታዎችም ብትል ከመከሰቱ በፊት በቴክኖሎጂ ማወቅ ትችላለህ፡፡ በሳተላይት ምስል ወይም ኤሪያል ጂኦግራፊ ተጠቅመህ መተንተን የአየር ንብረት ለውጥ፣ የበሽታ አይነትና የጠል መጠን ማወቅ ትችላለህ፡፡ ስለዚህ እርሻ ብቻውን ብትወስድኳ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ነው የሚጠቀመው፡፡ አስተዳደር በሚመለከትም ቢሆን ትክክለኛ ወረጃ ሊኖረው ይገባል፡፡ ትክክለኛ መረጃ ደግሞ ሰዎች እየላኩና የፈለጉት እያደረጉ የሚገኝ አይደለም ስለዚህ ትክክለኛ መረጃ ከቦታ ቦታ ሊመጣ ከተፈለገ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ መጠቀም ግድ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዘፋኖች ሳይቀር እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ድሮ ስንጠቀምበት የነበረው ትልቅ የቪድዮ ካራ ይዞ መቅረፅ ቀርቷል፡፡ አሁን የተሸለ ጥራት ያለው አገልግሎት እየሰጣቸው ይገኛል፡፡ ለምን ለሌሎች የእርሻ፣ የማዕድን እና የማኑፋክቸሪንግ ስራዎች አይውልም፡፡ የተጣራ መረጃ ወሳኝና መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ለማንኛውም ከፍተኛ ቴክኖሎጂ መጠቀም አለብን፡፡ ይህ ለመጠቀም ደግሞ ፊዚክስና ሂሳብ ችግር ፍቺ መሆን አለባቸው፡፡ ዝም ብለህ ለንባብ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ በፊዚክስና በሂሳብ የሚያስብ በነሱ አማካኝነት ችግር መፍታት ይኖርበታል፡፡ እነዚህ በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ የት/ት ስርዓቱን መቀየር አለበት፡፡ እነዚህን መሸከም የሚችል መሆን አለበት፡፡ ስለዚ ወጣቱ በገበያ ዕድል አለው፤ ምቹ ሁኔታዎች በመንግስት መፈጠር አለባቸው፤ ራሱ ታግሎም ምቹ ሁኔታ መፍጠር አለበት፡፡ ቴክኖሎጂ ግን የዘላቂ ሂወታችን መሰረት ነው፡፡ በዚህ ነው መወዳደር የምንችለው፡፡

ውራይና፡- ለሰጠኸኝ ሁለንተናዊ ትንትና በአንባቢዎች ስም አመሰግናለሁ፡፡ ዕድሜ ይስጥልኝ!!

******

Guest Author

more recommended stories