​ግለሰቦችን በመግደል የሚመጣ ለውጥ የለም

(ካሕሳይ ቃሉ ከአዲስ አበባ)

ባለፈው ሳምንት የነሻዕቢያ ፣ ኦነግና ግንቦት ሰባት የከፈትዋቸው የፌስ ቡክ አካውንቶች ጄኔራል ሳሞራ ሞቱ ብለው በቅብብሎሽ ሲያናፍሱ ተመለከትኩ፡፡

እነዚህ አቅመ ቢስና ፀረ-ሰላም ሃይሎች ለቀናት ሳይሆን ለሰአታት እድሜ የሌለው የውሸት ጋጋታ ሲነዙ አዲስ ነገር ሆኖ አላገኘሁትም፡፡

ግለሰቦች በመግደል ሰርዓት/አስተሳሰብ መቀየር የሚቻል ቢሆን ኢህአፓና ደርግ በውሸት ሳይሆን በተግባር የገደሉዋቸው ታዋቂ ሰዎች በርካታ ነበሩ፡፡

ገዳዮች በአስተሳሰብና በአላማ ማሸነፍ ሲያቅታቸው በውሸትም ጭምር እገሌ የሚባል ሞተ እያሉ ያወራሉ፡፡

ታላቁ መሪ ክቡር አቶ መለስ ከተሰዋ በኋላም ኢትዮጵያን የተቆጣጠሩዋት ይመስል ያልደለቁት የደስታ ከበሮ አልነበረም ስርዓቱና አስተሳሰቡ ግን የመላ ኢትዮጵያዊያን ስለሆነ አሁንም ድረስ አለ ለወደፊትም ይቀጥላል፡፡

አሁንም ቢሆን ጄኔራል ሳሞራ ተቋም እንጂ ቡድን ወይም ቤተሰብ አይደለም እየመሩ ያሉት፡፡

በመሆኑም ጄኔራል ሳሞራ የራሱ እምቅ አቅምና ብቃት በሰራዊቱ ግንባታ ያለው የላቀ አስተዋፅኦ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰራዊቱ ውስጥ ከላይ እስከታች ብቃት ባለው አመራር የተገነባ በአጠቃላይ ሰራዊቱም ባለው ህዝባዊ ወገንተኝነቱ በጉልህ የሚታይ ለህገ-መንግስቱና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በፍፁም ታማኝነት እስከመጨረሻ የሚዋደቅ በዚህም በህዝብ ዘንድ አሜኔታና አድናቆት ያተረፈ ጠንካራ ሰራዊት እንጂ የእምቧይ ካብ አይደለም በጩኾት የሚፈርስ፡፡

ስለሆነም ለአገራችን ብሄር ብሄረሰቦችም ሆነ በአገራችን እድገት ለምንኮራው ዜጎች በህግደፍ፣ በኦነግና ግንቦት ሰባቶች የኛ ጀግና፣ የኛ ሰራዊት ቢባል ነበር ሞት የሚሆነው ስለሆነም እናንተ ውሸታችሁ ቀጥሉ ሰራዊቱ ደግሞ ጀግና ቢሰዋ ጀግና ይተካል እያለ በህገ-መንግስቱና በህዝብ የተሰጠውን ተልእኮ በአግባቡ ይፈፅማል ፡፡

ለኢትዪጵያ ህዝቦች የደስታ ለፅንፈኞቹና ለፀረ-ሰላም ራስ ምታት የሆነ ሌላ ተጨማሪ ዜና እንዲሆናችሁ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአቢሲንያ ሽልማት የተባለ ለአገራቸው ታላቅ ስራ ለሰሩ የሚሸልም አለም አቀፍ የሽልማት ድርጅት የዘመኑ ታላቅ ሰው በሚል የክቡር /ሎሬት/ H:E ሽልማት እናንተ ሞተ ባላችሁበት ማግስት ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም ለጀነራል ሳሞራ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

የልማት፣ የሰላም የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታችን ሳይሸራረፍ ይቀጥላል!!

ክብርና ሞገስ ለሰማእታት!!

********

Guest Author

more recommended stories