የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ-ሶማሌ ክልልን ጎበኙ

(አብዱረዛቅ ካፊ)

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከኢትዮጲያ-ሶማሌ ክልል አገር ሽማግሌዎችና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራር ጋር በፀጥታ እና ከጎረቤት አገራት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ዙሪያ ትናንት ውይይት አደርገዋል፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሶማሊያና ከሌሎች ሀገራት ለተሰደዱ በርካታ ስደተኞች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መጠሊያ በመስጠት የቆየ የህዝቦች ወዳጅነት ለማጠናከር እየሰራች መሆኑን አውስተዋል።

የክልሉ መንግስትና ህዝብ በሰላምና በእንዳተቀባይነት በተላይ ለዓመታት በሶማሊያ የዘለቀው እርስ በእርስ ጦርነት ለተሰደደዱ የሶማሊያ ዜጎች በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በሚገኙ የመጠሊያ ጣቢያዎች ያለምንም ችግር እንዲኖሩ የክልሉ ህብረተሰብ ሀገር ሽማግሎችና የመንግስት  አካላት ላበረከቱት አስተዋኦም አመስግኗል፡፡

Photo - Foreign minister Workneh Gebeyehu with Ethiopian-somali elders, Jigjiga, Sept. 26, 2017
Photo – Foreign Minister Workneh Gebeyehu with Ethiopian-Somali elders, Jigjiga, Sept. 26, 2017

እንዲሁም በቅርቡ ከጎረቤት ሀገራት የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ዜጎች በክልሉ መንግሰትና ህዝብ እየተደረገለት ያለው ወገናዊ ድጋፍ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በቶጎ ውጫሌ ከተማ የሚገኙና ከጎረቤት ሶማሊላንድ የተሰደዱ የኢትዮጵያ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቶ በሰላም እንደሚኖሩና አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የአትየጵያ-ሶማሌ ክልል ሀገር ሽማግሌዎች የውስጥ ሰላማችን ለማደፍረስ ብሄር ብሔረሰቦችን ለማጋጨት ለሚፈልጉ ኃይሎች የሚያስተጋቡትን አሉባልታ ሳይደናገሩ የቆዩ የሕዝቦች አንድነትና መቻቻል እንዲያጠናክሩ ቃል ከመግባታቸው ባሻገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጉብኝታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

**********

Guest Author

more recommended stories