የኢትዮ-ሶማሌ ክልል መንግስት ውሀን እንደፔትሮሊየም መቁጠሩ ምን ይመስላል

ዘጋቢ – አብዱረዛቅ ካፊአርታኢ – አብድ ኡመር

አብዛኛው የክልሉ አከባቢዎች ቆላማና በረሃማ እንደመሆናቸው ዝናብ መጠበቅ የህዝቡ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ በሀገሪቱ ስልጣን ላይ ከነበሩት የቀድሞ ነገስታትና አምባገነኑ ወታደራዊ መንግስታት አይደለም መሰረተ ልማትና ምንም አይነት  ጥቅም ሳያገኝ የቆየ ማህበረሰብ ቢሆንም ባሳለፍናቸው 10 አመታት የክልሉ የገጠሩ አርብቶ አደርና ከፊል አርሶአደሩ ማህበረሰብና እንዲሁም የከተሞች ነዋሪዎች የውሃ ፍላጎትና ጥያቄ በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ እና በአቶ አብድ መሀሙድ ኡመር መንግስት በተሰጠው እልህ አስጨራሽ የውሃ ዝርግታና ፈጣን ምላሽ የክልሉ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር እንዲረጋጋና በውሃ በሳርና በግጦሽ ፈለጋ ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ማህበረሰብ ባለበት አከባቢ በቋሚነት እንዲረጋጋ አድርጓል፡፡

ዱሮ ግን ከክልሉ ዋና ከተማ ከጅግጅጋ በሁሉም አቅጣጫ ትጓዝ በቅርብ ውሃን የምታገኘው ቢያንስ ከ180ኪሜ በላይ አቋርጠህ በደገሀቡር በዋርዴር ቀ/ደሀር ወይም በድሬደዋ መሀከል ምንም አይነት ውሃ የሚባል ነገር እንዳል ነበረ ይታወቃል፡፡

በዚህ መሰረት በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ የሚመራው የክልሉ መንግስት ልዩ ስትራቴጂ በመንደፍ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ከመሆኑ ባሻገር ለሌሎች የኢትዮጲያ ክልሎች ተምሳሌት በመሆኑ ከማንም ያልተሰወረ ጉዳይ ነው፡፡

Photo - Ethiopian-Somali President Abdi Mohammed Omar inaugurating a water project
Photo – Ethiopian-Somali President Abdi Mohammed Omar inaugurating a water project

በሌላ በኩል የክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮና የውሃ ስራዎች ግንባታ ድርጅት ከክልሉ ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፐራይዝ  ጋር በመተባበር በርካታ የውሃ አከባቢዎችን በማጥናት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ የውሃ ማጣሪያ ማሽኖች ከውጭ በማስገባት የዝናብ ውሃ ማቆሪያ ግድቦች በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በመገንባትና በወንዞች አከባቢ የሚኖሩ ማህበረሰብ የተፋሰስ ውሃና መስኖ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ የማይረሳ ታሪካዊ አሻራ ሆኗል፡፡

በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስትም ከ1200 ሜትር በላይ ጥልቀት የከርስ ምድር ውሃ ማውጣት የሚችሉ ጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች መቆፈሪያ ማሽኖችን ከውጭ በመግዛትና አገልግሎት ላይ በማዋል አመርቂ  ውጤቶችን ለማስመዝገብ ችሏል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል መንግስት በዞንና በወረዳ ደረጃ 180 መካከለኛ የውሃ ማቆሪያ ግድቦች ግንባታ የተከናወነ ሲሆን  ግድቦቹ 873,019 851 ሜትር ኪዮቢክ ውሃ መያዝና የማጠራቀም አቅም ያላቸው ናቸው፡፡

በተመሳሳይም መሆኑም ከዛሬ 10 አመታት በፊት የነበረው የውሀ ቢርካዎች ቁጥር ከ320 ወደ 3900 ለማሳደግ ተችሏል፡፡ በዚህ መሰረት  በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል አከባቢ የተለያዩ የአገራችን የግልና የመንግሰት ሚዲያ ባለሙያዎች እንደ EBC ሶማሌኛና አማርኛ ፕሮግራሞች፣ ዋልታ፣EBSTV፣ ኢትዮጲያ ፕሬስ ኤጀንሲ፣ ኢ.ዜ.አ፣ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ ESTVና የመሳሰሉት ሚዲያዎች በክልሉ እየተከናወኑ ላሉ ዘርፈ ብዙ ልማትን በተለያዩ ወረዳዎች በተዘዋወሩና በተላይ ውሃን አስመልክቶ በጎበኙበት ወቅት በፋፈን በቸረርና ቆረሄይ ዞኖች ላይ የተሰሩ የዘላቂ ልማት ሜጋ ፖሮጀክቶች እንደ በካ-ቢርቆት፣ የሻይኮሽ ጎማር ወቺዋችና እንድሁም የመረኣቶ የመስኖ አፈር ግድቦች ለክልሉ ህዝብ ውሃና ገብሪና ፈላጎት ዘላቂ መፍትሄ መሆናቸው አስመስክሯል፡፡

እንደዚሁም የውሃ ቢርካዎችሁ የክልሉ ህብረተሰብ የውሃ ፍላጎት ለመሸፈን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ መሆናቸውም አስረድቷል፡፡

በተመሳሳይም በፋፋን እና ጀረር ወንዞች በከረምት ወቅት የሚፈሰውን የጎርፍ ውሃ 18ሺ ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት በመሮዓቶ፣ በካ፣ ቢርቆት፣ ጎማርና ወቺዋች የተገነቡ ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጅክቶች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ በአከባቢው ህዝቢና መንግስት እየታረሱ ሲሆን እነዚህ ፕሮጅክቶች በቅርቡ በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከውሃ አልፎ በምግብ ዋስትናና ሰብል ራሳቸውን እንዲችሉና ተጠቃሚ እንድሆኑ ያደርጋሉ፡፡

በሌላ በኩል  ከላይ የተጠቀሱት ወረዳዎች ውስጥ በመጨረሻውን  ዓመታት የነበረባቸው የውሃ ችግር ከተቃለለላቸው አከባቢዎች መካከል አራርሶ፣ በለፋእሳ፣ ደኖት፣ ገላዲ ሐሮራይስ፣ መጋለአድ፣ ዱማሌ፣ ዱዱሞአድ፣ ጎግቲ ላሰአኖድ፣ ሌሄለው፣ ቦህ፣ ጉናገዶ፣ ቱሉጉሌድ፣ ጌድሉጋስ (ሚኤይስ) ሽላቦ አዋሬና አሌን ተጠቃሽ ናቸው።

በተመሳሳይም በካሃ ቀ/በየህ ሀርተሼክ ዱርዋሌ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክትና ሙግወይን ፊቅ ሀመሮ ገሳንገስና የገሊል ኦበሌ ጌዲ ህግለሌይ ደ/ቡር የሰውና የእንስሳት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፖሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ የአከባቢው ህዝብ ተጠቃሚ አደርጓል።

በመቀጠልም በፋፈን፣ ቸረር፣ ቆረሔይና በዶሎ ዞኖች ላይ   ከአሁን በፊት በርካታ የውጭና በአገር አቃፍ ድርጅቶች ተጠንቶ ውሃ የለም የተባሉት አከባቢዎች በክልሉ አቅም ተጠንቶ በተላይ  በለሄለው፣ በዋርዴር፣ በደኖት፣ መርሲን፡ጉናገዶ ዲግ፣ ሀርሽን፣ ጋሻሞ ወረዳዎች ላይ ከቢርቆት ተነስቶ 170 ኪሜ በማቋረጥ በቀይ አፈር ላይ የተቆፈሩ የሰውና የእንስሳት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች ለህዘቡ ምላሽ ከመሆናቸው ባሻገር እንደ “ፓትሮሊየም” መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በአጠቃላይ እንደ የክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮ ሪፖርት የክልሉ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የከተሞች ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከአቶ አብድ መሀሙድ ኡመር መንግስት በፊት በአማካኝ 10 በመቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ ደርሷል፡፡

የክልሉ ከተማ መስተዳደሮች እያንዳንዱ 5ኪሜ የዉሃ ጣቢያዎች ተተክሎ እየሰራ ይገኛል፡፡ የገጠር ንጹህ የመጠጥ ውሃ  ሽፋን ከጥቂት አመታት በፊት 8 በመቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደ 59 በመቶ ሽፋን እንዲያድግ ተደርጓል፡፡

የክልሉ መንግስት በአጠቃላይ በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት በማጥናትና ከሁሉም ዘርፍ የተለየ ትኩረት በመስጠት በገጠርና በከተሞች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ስራ በጥቅሉ ከ10 አመት በፊት 278 የነበሩ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን ወደ 670 ለማሳደግ ችሏል፡፡ የእጅ ውሃ ጉድጓዶች ከከጥቅት (10) አመታት በፊት 320 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 2, 934 መድረሱ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡
*******

Guest Author

more recommended stories