መርዶ ነጋሪ ፖለቲከኞች ከሞት ሊታደጉን አይችሉም

(ኤቢሳ ከጨፌ ዶንሳ)

በርግጥ ምንም ከተፈጥሮ ሞት ማንንም ሊታደግ አይችልም፡፡ ነገር ግን ረጅም እድሜ፤ የደስታና የተድላ ህይወት ለማሳለፍ የሚቻልበትን ዘዴ ፈጣሪ በሰጠ አእምሮ መርምሮ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ሳይንስ እድገትና ብልፅግና ይህ ሊሆን እንደሚችል በኛም ባይሆን ራሳቸውን ሀገራዊ ውርደት ከሆነው ድህነትና ኋላቀርነት ባላቀቁትሀገራት መሪዎችና ህዝብ ዘንድ በተጨባጭ አይተናል፡፡ እያየንም ነው፡፡

ታዲያ ይህን የፍሰሀ ዓለም በምኞትና በተስፋ አንደበት ብቻም አይደለም ዜጎቻቸውን ማስታጠቅ የቻሉት፡፡ በመተማመን፤ በመሰረታዊ ፍላጎቶች ላይ ቆመው የትየለሌ የሰው ልጅ ፍላጎቶችን በራሱ ትግል ዜጋው እንዲያሟላ በማድረግ እንጂ፡፡ ረጅሙን ጎዞ በአንድ እርምጃ ጀምረው እርምጃዎቻቸውን ሁሉ በድልና በስኬት በመሙላት ጭምርም እንደሆነ የታሪክ ድርሳናትን ማገላበጥ በቂ ነው፡፡

ታዲያ የኔዋ ምስኪን ሀገር (ለድህነቷ ብቻ ሳይሆን የዋህ ህዝቦችም ስላሉባት ጭምር የተጠቀምኩት ቃል ነው) ለዚህ የታደለች አልሆን እያለች ብታብሰከስከኝ በዚህ በኩል ልተንፍስ ብዬ ነውና ሀሳቦቼ ደካማ ቢመስሉ አትፍረዱብኝ፡፡ ለነገሩማ ሀገር ምን ብትበድል ብትሉኝ ትክልል ናችሁ፡፡ ሀገር ሳትሆን ሀገርን እንደሀገር አቆምን አሊያም ልናቆማት ባሉት ጥበበኛ ፖለቲከኞች ስህተት እንጂ፡፡ ስህተትን ለመሳሳትም ባይሆን አንዳንዴ ድብቅ አጀንዳዎቻቸውን በመጪው ትውልድ ላይ በመጫን ዘለዓለማዊ መታወሻ ለማግኘትም ይሁን ለአጉል ጀብድ ያደረጉትን የሚያደርጉት ይመስለኛል፡፡ ነውም፡፡

ታዲያ በዚህ በኃያ አንደኛው ክፍለ ዘመንም ያውም የሰው ልጅ በስልጣኔ ማማ ከጫፍ ቁሜአለሁ እያለ በሚፎክርበት፤ እኔ በተፈጠርኩባት ምድራገር በተለይም በዚህች የደምዋ ክፋይ በሆንኩባት የኦሮሞ ቀዬ የሚበቅሉት የፅንፍ ፖለቲከኞቻችን ከመርዶ ነጋሪነት አልዘል ቢሉኝ ምን እርግማን ተጣብቶን ይሆን ለማለት ተገደድኩ፡፡ እነ እንቶኔ የዚህን ህዝብ ማንነት በበትረ ንግስናቸው በጨፈለቁበት ዘመን ያደረሱትን ግፍ እንዳንረሳው ብቻ ሳይሆን እሱኑ እያሰብን ስንብሰከሰክ ጀንበራችን እንድትጠልቅ የቀየሱት ስትራተጅ ሰርቶላቸዋል፡፡

እውነት መነገር ካለበትና መወቀስ ያለባቸው እኩል መወቀስ ካለባቸው ይህ ብቻ ሳይሆን እንቁ የሆነውን የዴሞክራሲን ፀሀይ በዓለም የፈነጠቀው ገዳ የወለዳቸው የገዳ አባቶች ስልጣን ሲጥማቸውና የገዢ መደብነት ፍላጎታቸው ሲንር በፈጠሩት መከፋፈል በኦዳ ዛፍ ስር ሳንነጋገር የምንግባባትን ቋንቋ ደበላልቀውት አራርቀውናል፡፡ በወዲህ የዚህ ታላቅ ህዝብ የሰፈረበት ለም መሬትና ያፈራው ድንቅ ሀብት እንዲሁም በኩሽ ዘርነቱ የወረሰው የቅድመ ስልጣኔ ልቀት በቅናት ያንገበገባቸው የሰሎሞኖቹ ባለዘውድ ጋሻ ጃግሬዎች ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር አሳምረው መቁረጣቸው ሌላው ሌላው ምክንያት ነው፡፡ ስንቱ ይነገራል ዘመዶቼ!

ይህ ሁላ ቅርና ታዲያ በዚህኛው ስልጣኔ በር ወለል ብሎ በተከፈተበትና ዓለም አንድ ቀዬ የመሆን ፍላጎቱን በመረጃ መዳረሶች በተረጋገጠበት ዛሬ እንኳን መረጃን ሀብት ለመፍጠር፤ የኦሮሞን ህዝብ አንድነት ጥንተ ጠዋት በነበረበት መልሶ ፈርጣማ የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካና የማህበራዊ ህይወት ባለቤት ለማድረግ በመጠቀምና በማስተላለፍ ፈንታ እከሌን አሰሩት እከሌን ገደሉት ዘራችንን አጠፉት በሚል ሙሾ ሀገር ለመገንባት የሚደረጉ ትንታኔዎች መድረሻቸው አልገባህ ይለኛል፡፡

በርግጥ ጥፋት ምነው ይነገራል ከሚል ጭፍን አስተሳሰብ እንደማልነሳ ይታወቅልኝ፡፡ ጥፋትም ሲሆን ሲሆን መወገዝና መቆም አለበት፡፡ በተለይም ደም የሚያፋስስና ህይወት የሚቀጥፍ ጥፋት መወቀስ ባለበት አግባብ መወቀስ አለበት፡፡

ሀሳቤ ጥፋት የሚነገረንን ያህል ደግሞ ደግ ደጉስ ወዴት አለ ለማለት ያክል ነው፡፡ አሁን ታሪክ በፈጠረው እድል ይህን ታላቅ ህዝብ የሚመራው ኦህዴድ ነው፡፡ ይህንን ታሪክ ፈፅሞ መፋቅ አይቻልም፡፡ ታዲያ ለኦሮሞ ህዝብ ያስገኛቸውንና የሚያስገኛቸውን እድሎች ለመናገር አፋቸው የሚለጎም ነገር ግን መርዶ ለመንገር ወፍ የማትቀድማቸውን ፖለቲከኞች በጥንተ ነገራችን ለተለያየ ዓላማ ይህንን ህዝብ ወደ ሀዘኖቹ እንጂ ወደተስፋዎቹ እንዳይመለከት ካደረጉት ከነዛ የዘመን ተወቃሾች በምን ልልያቸው እችላለሁ ጎበዝ!

በርግጥ አንድን የፖለቲካ ስርዓት ከሚያጥላላ አካል ሙገሳ መጠበቅ የማይሆን ነገር ነው፡፡ ሁለቱም ዓላማቸው የራሳቸው የማእዘን ዲንጋይ ነውና፡፡ ህዝባዊነታቸውም የሚለካው ከተግባር ከሚገኝ ፍሬ ብቻ ነው፡፡ ለህዝብ ግን ሙሾን ብቻ ሳይሆን ተስፋን፤ ብሩህ መፃኢ ድልን፤ ተንበርካኪነትና ወቃሽነትን ሳይሆን መቆም መቻልን መስበክ ለሁላችንም የሚበጅ ይመስለኛል፡፡ ይህ ካልሆነ እሱ አጎንብሶ ሀዘኑን እያላመጠ ጀርባው ላይ ተፈናጦ ሌላ…ሌላ የገዢ መደብ ለመሆን ለማለም ካልሆነ በስተቀር አንጠቅመውም ማለቴ ነው፡፡ አሊያም እኔ የሌለሁበት የፖለቲካ ስርዓት ሁሌም ፉርሽ ነው ከሚል ፉርሽ ቀመር የሚነሳ ካልሆነ በስተቀር፡፡

ምክንያቱም በአንድ ትውልድ ውስጥ በአብዛኛው የሚኖረው አንድ ድርጊት፤ አስተሳሰብና መርህ ነው፡፡ ቁጣ ሆኖ በዛው ትውልድ ውስጥ አሰር አስተሳሰብ መርህና ድርጊት ወደስልጣን መጥቶ ሀገር ካልበተነ በስተቀር፡፡ ለሁሉም የኦሮሞ ፖለቲካ ተንታኞች ከሙሾ ነጋሪ የፖለቲካ ፊት አውራሪነት ወጥተው አብዮተኞቹ ጀመሩትን የኢኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ አብዮት አቅማቸው በቻለ ቢደግፉና ቢሳተፉ፤ ተራቸው ደርሶ ወደስልጣን የመጡ ለታም የቀረንን በመሙላት ድህነታችን በአጭሩ በተቀጨ ሰል አሰብኩ፡፡ ከሆነ ነው ታዲያ፡፡

ቸር እንሁንማ!

*********

Guest Author

more recommended stories