ከአንድ ሺህ ሦስት መቶ ላይ በላይ የሳዑዲ ተመላሾች በተለያየ ሙያ ተመረቁ

(በብርሃኑ ወልደሰማያት)

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሳዑዲ ተመላሾችን በሃገራቸው ሰርተው ለመለወጥ የሚያደርጉትን ጥረት መንግስት መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ።

በአዲስ አበባ ነዋሪ ከሆኑና በ6 የቴክኒክና ሙያ ተቃማት ከሰለጠኑ 2021 የሳዑዲ ተመላሽ ሰልጣኞች መካከል 1371 ያህሉ ዛሬ ተመርቀዋል።

ሚንስትሩ አቶ አብዱል ፈታህ አብዱላሂ ተመላሾቹ በሃገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ያመኑና ይህንንም በተግባር እያሳዩ ያሉ በመሆናቸው የመንግስት ድጋፍ ከጎናቸው እንደማይለይ ነው የገለጹት።

በአዲስ አበባ የተጀመረው ይህንን ስራም በመላ ሀገሪቱ በተሳካ መልኩ ለማስፈጸም ሚንስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አተ አባተ ስጠታው በበኩላቸው ፥ ተመላሾቹ ወጣቶች በመሆናቸው ለከተማዋ ተጨማሪ የልማት ሃይል ስለሆኑ አስተዳደሩ ስኬታማ እንዲሆኑ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።

ተመራቂዎቹ በበኩላቸው ያላቸውን ሃይልና ግዜያቸውን በማስተባበር መንግስት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ውጤታማ ለመሆን ተግተው እንደሚሰሩ ነው ያረጋገጡት።

ሚንስትሮች የፌደራል ተቃማት ሃላፊዎችና የአለም አቀፍ ተቃማት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በፕሮግራሙ ታድመዋል።

********
ምንጭ፡- ፋና –
በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ 1371 የሳዑዲ ተመላሾች ተመረቁ – የካቲት 22፣ 2006

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories