በአምስት ዩኒቨርስቲዎች የአእምሮ ህክምና ስልጠና ሊሰጥ ነው

በኢትዮጵያ የአእምሮ ህክምና ባለሞያዎችን በብዛት ለማፍራት የአማኑኤል አዕምሮ ህክምና ሆስፒታልን ጨምሮ በአምስት ዩኒቨርስቲዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስልጠናውን ከሚሰጡ ከባህርዳር፣ሀዋሳ፣ መቀሌ፣ሀረማያ፣ ጅማ ዩንቨርስቲ እንዲሁም የአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ተወካዮች ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ትናንት ተፈራርመዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደኤታ ዶክተር ከበደ ወርቁ እንደተናገሩት በስምምነቱ መሰረት ተቋማቱ ለአዕምሮ ህሙማን ቀላል የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን ያሰለጥናሉ፡፡

ባለሙያዎቹም 160 በሚጠጉ የጤና ተቋማት ውስጥ የሕክምና አገልግሎቱን እንዲሰጡ እንደሚደረግ የገለጹት ዶክተር ከበደ ከፍተኛ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ ወደ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚገኙበት የጤና ተቋማት እንዲያስተላልፉ ይደረጋል፡፡

የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና ከ2003 በፊት ከአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ጋር በመተባበር ቢጀመረም በሰው ሀይል እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ርቀት መሄድ እንዳልተቻለ ሚኒስትሩ ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

አሁን ባለው እንቅስቃሴ በቀጣይ አምስት አመታት ውሰጥ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ እንደሚፈታ እምነት አለን ብለዋል፡፡

*********
ምንጭ፡- ኢዜአ – የካቲት 15/2006፤ ‹‹በኢትዮጵያ በአምስት ዩኒቨርስቲዎች የአእምሮ ህክምና ስልጠና ሊሰጥ ነው››

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago