አለማየሁ አቶምሳ ከኦህዴድ አና ከኦሮሚያ የመሪነት ቦታቸው ለቀቁ

በሁሉም የልማት እና የመልካም አስተዳደር መስኮች የታቀዱትን ተግባራት ለማሳካት ኦ.ህ.ዴ.ድ የመንግሥት እና የሕዝብ አቅሞችን በማስተባበር ርብርብ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የኦ.ህ.ዴ.ድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን አቶ አለማየሁ አቶምሳ ያቀረቡትን ከኃላፊነት የመልቀቅ ጥያቄ ማዕከላዊ ኮሚቴው ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የታላቁን መሪ ጓድ መለስ ዜናዊን የአረንጓዴ ልማት ራዕይ ለማሳካት የተከናወነውን ሥራ በዘንድሮው ዓመትም በሁሉም የክልሉ ቀበሌዎች አመርቂ ውጠየት የተገኘበት በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በግብርና ልማት ረገድ በተለይ በሰብል ልማት ምርት እና ምርታማትን የሚያሳድጉ ግብዓቶችን በመጠቀም እና ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል ረገድ አበረታች ለውጦች በመታየታቸው ለዚህ ሥራ ቁልፍ ሚና የነበራቸው የድርጅት፣ የመንግስት እና የህዝብ የተደራጀ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል፡፡

በሠራ አሰፈጻሚው የተገመገመው በከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማት፣ በሲቪል ሰርቪስ እና መልካም አስተዳደር፣ በመሰረተ ልማት የከተሞችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚን ወደ ልማታዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ በመቀየር ረገድ የተጀመሩት ሥራዎች በተቀመጠው አቅጣጫ እየሄዱ እንደሆነ አመልከቷል፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ ዘርፍ የሥራ አፈጻጸሙ በቀሪ ጊዜያት በሚፈለገው ጥራት፣ ፍጥነትና ቅልጥፍና መከናወን እንዳለበት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አስምሮበታል፡፡

በትምህርት መስክ ጥራትን ለማረጋገጥ በጤና የዕናቶችን እና ህጻናትን ሞት በመቀነስና የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በመተግበር ረገድ ግንባታውን እውን ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በማያያዝም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተያዘው ዓመት ለማከናወን የተያዙ ግቦችን ሁሉም የሰራዊት አቅሞችን በማጠናከር በድርጅት መሪነት ከሁሉም የልማት እና የመልካም አስተዳር ግንባሮች የህዝብን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አኳያ እንዲፈጸም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመጨረሻም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአንክሮ የተመለከተው የድርጅቱ ሊቀ-መንበርና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አለማየሁ አቶምሳ ያቀረቡትን ከኃላፊነት የመነሳት ጥያቄ ጉዳይ ተቀብሎ ተወያቶበታል፡፡

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቶ አለማየሁ ድርጅታቸው፣ መንግስትንና ህዝባቸውን እስከ መጨረሻው ለማገልገል ቁርጠኝነት ያሳዩ ሆነው እያለ ከቅርብ አመታት ወዲህ ያጋጠማቸው የጤና ችግር የኃላፊነት ተልዕኳቸውን ለመወጣት የሚያስቸግራቸው በመሆኑ የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ለኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅርቦ አጽድቆታል፡፡

አቶ አለማየሁ አቶምሳ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የኦህዴድ ለቀ-መንበር እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት የተወጡ እንደሆኑና ክልላዊ መንግስቱ እና ድርጅቱ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የራሳቸውን የማይተካ ድርሻ የተወጡ በመሆናቸው በድርጅቱ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ሊሰጣቸው የሚገባ እንደሆነ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አመልከቷል፡፡

**********

Source: ERTA, Feb. 20, 2014. አለማየሁ አቶምሳ, titled “የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አለማየሁ አቶምሳ በፈቃዳቸው ከስራ ለቀቁ”

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago