የመቐለ መርከብ ስም ተስተካከለ – የመንግሰት ሚዲያ እየለገመ ነው

ጉዳዩን አስመልክቶ ከመጀመሪያው በይፋ ድጋፍ የሰጡት እውቁ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ መምህር ገብረኪዳን ደስታ፤ ዛሬ ለሆርን አፌይርስ በሰጡት አስያየት ለውጡን በአወንታዊ እንደሚመለከቱት ከገለጹ በኋላ – የመቐለ አሉላ አባ ነጋን አየርማረፊያ ጨምሮ በሌሎች ሥፍራዎች ማስተካከያ መደረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
‹‹የፌዴራል መንግስት ሚዲያዎች የትግራይ ከተሞችን አዛብተው በመጥራት – በተመሳሳይም ደደቢት አጥብቀው በማንበብ እና በመሳሰለው የሚከተሉት አካሄድ ሆነ ተብሎ ነው ወይስ ባለማወቅ የሚለው ግልጽ አይደለም›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጲያ መርከብ ድርጅት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ የተሰየመችው መርከብ ላይ ‹‹መቀሌ›› በሚል ያሠፈረውን ጽሕፈት ‹‹መቐለ›› በሚል አስተካከለ፡፡

ድርጅቱ አዲስ ባሠራት መርከብ ላይ የሠፈረው ስያሜ የተሳሳተ በመሆኑ፤ ድርጅቱ መርከቧን ከተረከበ ጀምሮ ላለፉት ስድስት ሳምንታት በፌስቡክ እና በፔቲሽን ተቃውሞ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡Ethiopian Shipping lines - Mek'ele vessel name corrected after public backlash

ድርጅቱ እርማቱን ያለምንም ይፋዊ መግለጫ ባለፈው ሳምንት ያደረገ ሲሆን፤ በድርጅቱ የሚሠራ – ስሙ እንዲጠቀስ የማይፈቅድ -ግለሰብ ትላንት ለሊት መርከቧን ፎቶ አንስቶ ለሆርን አፌይርስ በመላክ ለውጡን አረጋግጧል፡፡

ስለጉዳዩ ለሆርን አፌይርስ በስልክ ማብራሪያ የሰጡት የድርጅቱ ም/ሥራ አስኪያጁ አለሙ አምባዬ <<ከሕዝብ በደረሰን አስተያየት መሠረት እና እኛም ጥያቄው ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው ማስተካከያውን አድርገናል>> ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ለውጡ ስለተካሄደበት ሂደት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልፈቀዱም፡፡

በአንፃሩ ኢቴቪ፣ ኢዜአ እና መሰል የፌዴራል መንግሰት ተቋማት በተደጋጋሚ የቀረበላቸውን ጥያቄ በማንአለብኝነት ገፍተው የትግራይን ከተሞች ስም እያዛቡ በመጻፍ ላይ እንደሚገኙ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ከመጀመሪያው በይፋ ድጋፍ የሰጡት እውቁ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ መምህር ገብረኪዳን ደስታ፤ ዛሬ ለሆርን አፌይርስ በሰጡት አስያየት ለውጡን በአወንታዊ እንደሚመለከቱት ከገለጹ በኋላ – የመቐለ አሉላ አባ ነጋን አየርማረፊያ ጨምሮ በሌሎች ሥፍራዎች ማስተካከያ መደረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡Ethiopian Shipping lines - Mek'ele vessel name corrected after public backlash - photo 2

‹‹የፌዴራል መንግስት ሚዲያዎች የትግራይ ከተሞችን አዛብተው በመጥራት – በተመሳሳይም ደደቢትን አጥብቀው በማንበብ እና በመሳሰለው የሚከተሉት አካሄድ ሆነ ተብሎ ነው ወይስ ባለማወቅ የሚለው ግልጽ አይደለም›› ብለዋል፡፡

************
ለተጨማሪ መረጃ፡- Mek’ele vessel’s name corrected after public backlash ያንብቡ፡፡

Daniel Berhane

more recommended stories