የሱዳን መንግስት የመለስን ሙት ዓመት መታሰቢያ ያዘጋጃል

ሱዳን በፕሬዝዳንት አልበሽር አነሳሽነት የታላቁን መሪ መለስ ዜናዊን 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ነሀሴ 18/2005 ዓ.ም በሱዳን የወዳጅነት አዳራሽ ልታከብር ነው፡፡Sudan President Al-bashir and Prime Minister Meles Zenawi

የመታሰቢያ ስነስርአቱ አስተባባሪ ኮሚቴ በኢንቨስትመንት ሚኒስትሩ ዶክተር ሙስጠፋ ኦስማን የሚመራ ሲሆን በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደርም የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል ናቸው፡፡

ስነስርዓቱን ዛይን ቴሌኮሙኒኬሽን ካምፓኒ ስፖንሰር ያደርገዋል ተብሏል፡፡

ፕሮግራሙ ላይ ታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ በአፍሪካና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ስለነበራቸው ሚናና በኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት ላይ ስለነበራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተዘጋጁ ፅሁፎች ይቀርባሉ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ለፕሮግራሙ ለመሳተፍ ወደ ካርቱም ያመራልም ተብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ ለመገኘት ነገ ነሃሴ 13/2005 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ሱዳን ቪዥን ዘግቧል፡፡

**********

Source: ERTA – Aug. 18, 2013, titled “ሱዳን የታላቁን መሪ መለስ ዜናዊ 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ልታከብር ነው”

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories