የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 30/2005 ባካሄደው 49ኛው መደበኛ ስብሰባ የ2006 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ 154.9 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ፡፡
በዚህ መሰረት ለ2006 በጀት አመት በፌዴራል መንግስት ለሚከናወኑ ስራዎችና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን በጀት አጽድቆ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ወቅት ስራ ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ እና የፌዴራሽን ም/ቤት በወሰነው ቀመር መሰረት የፌዴራሉ መንግት ለክልሎች የሚሰጠውን የድጋፍ በጀት መጠን መወሰን ስለሚኖርበት ከሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በሚፈጸመው በአንድ የበጀት አመት ጊዜ ውስጥ የፌዴራል መንግስት በጀት 154,903,290,899/ አንድ መቶ ሃምሳ አራት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር/ እንዲሆን ወስኗል፡፡
ከዚህ ውስጥ፡-
* ለመደበኛ ወጪዎች——————–ብር 32,530,000
* ለካፒታል ወጪዎች ——————- ብር 64,321,732,351
* ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ————— ብር 43,051,558,548
* የምዕተ ዓመቱን ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ– ብር 15,000,000,000 እንዲሆን ተመድቧል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስተላልፏል፡፡
**********
Source: ERTA – June 7, 2013, titled “የፌዴራል መንግስት የ2006 በጀት 154.9 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ተወሰነ“
To Daniel,
I think the recurrent budget is missing the last three zeros. It should read 32,530,000,000
in addition to the projects, wish if they could spend more money on housing, esp for civil servants! and on ICT simplifying and making the governmental works more transparent.