ዘንድሮ 11.3% ሀገራዊ እድገት ይጠበቃል – ሚ/ር ሶፊያን አህመድ

(ሰኢድ አለሙ)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና በስሩ ተጠሪ የሆኑ ስድስት አጀንሲዎችን የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ በሪፖርታቸው እንዳመለከቱት በዚህ አመት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፎች እየታዩ ያሉ ለውጦች 11.3 በመቶ ሀገራዊ እድገቱን ለማSofian Ahmed - Minister of Finance and Economic Developmentረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

የዋጋ ንረቱን ወደ 6.1 በመቶ ማውረድም እንደተቻለና መንግስት መሰረታዊ ሸቀጦችን ከውጭ እያስመጣ ገበያውን ለማረጋጋት ባደረገው ጥረትና ከብሄራዊ ባንክ ብድር ባለመውሰድ ነው የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚውን መስመር ማስያዝ እንደተጀመረ ሚኒስትር ሶፊያን የተናገሩት፡፡

ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 2.2 ቢሊዮን ዶላር ፣ ከሀገር ውስጥ ደግሞ 77 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል፡፡

ሚኒስትር ሶፊያን እንዳሉት ከአበዳሪዎች ቃል ከተገባው 64 ቢሊዮን ብር ውስጥ 32 ቢሊዮን ብር መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ በወጪ አሸፋፈን የ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ጉድለት ታይቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ አለማየሁ ጐጂ ክፍተቱን ለመሙላት ከመንግስት ግምጃ ቤትና ሌሎች አማራጮች ጥቅም ላይ ውለዋል ብለዋል፡፡

የበጀትና ፋይናንስና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዋና ወጎ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ወጥ አሰራርን ከመዘርጋት አንስቶ የቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ችግሮቹን እየቀረፈ የመንግስትን የፋይናንስ አፈጻጻምን የበለጠ ማጠናከር እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

እንዲሁም የመንግስትን የፋይናንስ አፈጻጻም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እየታየበት ያለውን የማስፈጸም አቅም ውስንነት ሊቀርፍ እንደሚገባም ምክር ቤቱ አሳሰቧል፡፡

***********

Source: ERTA – May 25, 2013

Daniel Berhane

more recommended stories