ም/ከንቲባ:- ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን በወዲያኛው ቅዳሜ ማድረግ ይችላል

(የትምወርቅ ዘለቀ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ ግንቦት 24 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲያካሂድ ፈቀደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እንደገለጹት ፓርቲው ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል አንድ ሳምንት ተራዝሞ ግንቦት 24 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲካሄድ መፈቀዱን ገልጸዋል፡፡

አስተዳደሩ የፓርቲውን ሰላማዊ ሰልፍ ለአንድ ሳምንት እንዲራዘም ያደረገው ለ50ኛው የአፍሪካ ህብረት በዓል በርካታ እንግዶች አዲስ አበባ ስለሚገቡ አመራሩና የጸጥታ አካላት ሙሉ ሃይላቸውን ለስብሰባው ስኬት እየተረባረቡ በመሆኑ ነው፡፡

ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ-መንግስታዊ መብቱ ስለሆነ ሰልፉን በሚቀጥለው ሳምንት እንዲያካሄድ የተፈቀደለት መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባው የፓርቲው የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ መባሉ ግን ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

አስተዳደሩም ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ግንቦት 24/2005 እንዲያካሂድ መፈቀዱንና የሚመለከታቸው አካላትም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደረጉላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል፡፡

 **********
Source: ERTA – May 24, 2013. Original title “ሰማያዊ ፓርቲ ለጠየቀው ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ተሰጠው”.

**********

Government reply letter to Semayawi party demonstration request

**********

Daniel Berhane

more recommended stories