Ethiopia | እነሚኒስተር መላኩ ፈንታ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ሌሎች አስራ ሁለት ሰዎች ዛሬ ግንቦት 5/2005 ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የቀረቡበት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አቃቢ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሟላት አለብኝ በማለት ባቀረበው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ የቃል ክርክር አካሂዷል።Minister Melaku Fanta and Gebrewahed Woldegiorgis [Director General and Deputy of Revenues and Customs Authority] Left to Right

ችሎቱ ተጠርጣሪዎቹን በሶስት የክስ መዝገቦች በመከፋፈል የተመለከተ ሲሆን በእነ አቶ መላኩ ፋንታ የክስ መዝገብ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ተካተዋል ።

በዚህ መዝገብ የቀረቡት ተከሳሾች ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች መካከል ቀረጥና ታክስ ማጭበርበር፣ አራጣ በማበደር የተከሰሱ ግለሰቦችን ክስ ስልጣንን በመጠቀም እንዲቋረጥ ማድረግና በዚህም ያልተገባ ሀብት መሰብሰብ ይገኝበታል፡፡

የአንደኛው ተጠርጣሪ የአቶ መላኩ ፋንታ ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ለመለቀቅ ያስችሏቸዋል ያሏቸውን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በቃል አቅርበዋል።

ሀሳቡን ያደመጠው ፍርድ ቤትም በጊዜ ቀጠሮው ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ግንቦት 6/2005 ስምንት ሰዓት ቀጠሮ ይዟል።

በተመሳሳይ በነገብረዋህድ ገብረ ጊዮርጊስ የክስ መዝገብ ተጠርጣሪዎችንና የአቃቢ ህግ መከራከሪያን ያደመጠ ሲሆን መደበኛ የስራ ሰዓት በመጠናቀቁ በጊዜ ቀጠሮው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ግንቦት 6/2005 ቀጠሮ ይዟል።

በዚህ መዝገብ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎች ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች መካከል ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለ ሲሚንቶ እንዲገባ ማድረግ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን ማገዝ፣ ከተጠርጣሪዎች መካከል የሁለቱን ክስ የሚደግፉ ሰነዶችን ማሸሽ ይገኝበታል።

በሶስተኛው የክስ መዝገብ የሚገኙ ስድስት ተጠርጣሪዎች ደግሞ የናዝሬት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ባልደረቦች ሲሆኑ ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች መካከል በኮንትሮባንድ የተለያዩ እቃዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግና ያልተገባ ሀብት መሰብሰብ ይገኝበታል።

**********

Source: ERTA – May 13, 2013. Originally titled “በሙስና የተጠረጠሩት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ”.

Check the Melaku Fenta et al saga archive for previous posts.

Daniel Berhane

more recommended stories