የብሪታኒያ ፖለቲከኞች የተገኙበት የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተካሄደ

ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ባለፉት 20 ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ህዳሴ ለነበራቸው የላቀ አስተዋጽኦ ዕውቅና ለመስጠት የብሪታኒያ ከፍተኛ ሚኒስትሮችና ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት በአጠቃላይ ከ700 በላይ እንግዶች በተገኙበት በለንደን የመታሰቢያ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡

ማክሰኞ ሚያዚያ 22/2005 በተካሄደው በዚህ ስነ ስርዓት ላይ ከተናገሩት መካከል የቀድሞ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን የድህነትን አስከፊነት ለማጥፋት እንደ መለስ ዜናዊ ጥረት ያደረገ መሪ የለም ብለዋል፡፡Meles-Zenawi-and-Gordon-Brown-World-Economic-Forum-on-Africa-2012-Addis-Ababa_thumb.jpg

መለስ በኢትዮጵያ ላመጡት የፖለቲካ ለውጥና ፖሊሲያቸው ላስገኘው የኢኮኖሚ ዕድገት ብራውን አወድሰዋቸል፡፡

ለመለስ ዕድገት ማለት በርካታ ክሊኒኮችንና ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በዚህም ድህነትን በመቅረፍ የሚሊዮኖችን ህይወት ማሻሻል ማለት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚ/ር መለስን ለማስታወስ ሀውልቶች፣ መንገዶች፣ ትምህርት ቤቶች ሊሰየሙ ይችሉ ይሆናል፤ ለእሳቸው ግን ምርጡ መታሰቢያ በሰሩት ስራ ወደፊት የተሻለ ዕድል የሚኖራቸው ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ናቸው ብለዋል፡፡

የቀድሞ የብሪታኒያ ፓርላማ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሀፊ ሎርድ ትሬይስማን በበኩላቸው መለስን የተግባር ሰው፣ ራሱን ችሎ ሀሳብ አመንጪና ዘላቂ ልማትን አራማጅ ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡

መለስ በሶማሊያና ቀሪው ምስራቅ አፍሪካ ላይ የነበራቸው ጥልቅ መረዳት ማንም የሚስተካከው አልነበረውም ነው ያሉት፡፡

የቀድሞ የብሪታኒያ ምክትል የፋይናንስ ኃላፊ ሎርድ ቦአቲንግ ደግሞ መለስ የፓን አፍሪካኒዝምን ነበልባል ያስቀጠለና ከታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ጎራ የሚመደብ እንደሆነ በመግልጽ የአፍሪካ ህብረት ዛሬ ላይ ላለበት ደረጃ የመለስን አስተዋጽኦ አውስተዋል፡፡

መለስ እንደ አለም ባንክ ያሉ ተቋማትን ምክር ባለመቀበል ከፍተኛ ትምህርትንና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ጎን ለጎን በማስፋፋት እንዲሁም ለግብርና ቅድሚያ በመስጠት በኋላ ትክክለኛ መሆኑን ያስመሰከረ መሪ ነበርም ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ ተናጋሪዎችና ሌሎችም ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ በአፍሪካ ጉዳዮች፣ በአየር ንብረት ጉባኤዎችና በብሪክስ መድረኮች ላይ አህጉሪቱን በመወከል የተጫወቱአቸውን ሚናዎችና ያበረከቷቸውን ፈርጀ ብዙና ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦዎችን በየተራ ዘርዝረዋል፡፡

*********

ምንጭ፡- በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ via ERTA – May 1, 2013

Daniel Berhane

more recommended stories