ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን አመራሮቻቸውን መረጡ

ባለፉት ቀናት መቀሌ ፣ ባህር ዳር ፣ ሃዋሳ እናEPRDF አዳማ ከተሞች ላይ ጉባኤያቸውን ሲያካሂዱ የሰነበቱት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሊቀ መንበሮቻቸውን በመምረጥ ጉባኤያቸውን አጠናቀቁ።

መቀሌ ላይ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው ህወሃት አቶ አባይ ወልዱን ሊቀ መንበር እንዲሁም ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

ለዓመታት ፓርቲውን በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ያገለገሉት አምባሳደር ስዩም መስፍን ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶምን ጨምሮ ፥ ዘጠኝ አባላት ባቀረቡት ጥያቄና ፓርቲው እየተገበረ ባለው የመተካካት ሂደት መሰረት ፤ በአዲስ አባላት እንዲተኩ የተወሰነ ሲሆን አንጋፋ አባላቱ በክብር ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተሰናብተዋል።

ዘጠኙ ነባር አባላት በኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ በድምፅ ተወክለው እንዲሳተፉም ተወስኗል ።

በጉባኤው 45 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫን ጨምሮ ፥ አቶ አባይ ወልዱ ፣ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፣ አቶ በየነ ምክሩ ፣ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፣ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ ፣ አቶ ገብረመስቀል ታረቀኝ ፣ አቶ አለም ገብረዋህድ እና ወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም የኢህአዴግ እና የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ባህርዳር ላይ ጉባኤውን ያካሄደው ብአዴን አቶ ደመቀ መኮንን ሊቀ መንበር እንዲሁም አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

አቶ ደመቀ መኮንን ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ አቶ በረከት ስምኦን ፣ አቶ አያሌው ጎበዜ ፣ አቶ ተፈራ ደርበው ፣ አቶ አለምነው መኮንን ፣ አቶ ብናልፍ አንዷለም ፣ አቶ አህመድ አብተው እና ዶክተር አምባቸው መኮንን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ አቶ በረከት ስምኦን ፣ አቶ አለምነው መኮንን ፣ አቶ አዲሱ ለገሰ ፣ አቶ አያሌው ጎበዜ ፣ አቶ ተፈራ ደርበው ፣ አቶ ብናልፍ አንዷለም ፣ አቶ አህመድ አብተው ፣ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ፣ አቶ መላኩ ፈንታ ፣ ዶክተር አምባቸው መኮንን እና አቶ ጌታቸው ጀምበር የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱን ወክለው በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አባላትንና 65 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫንም አካሂዷል።

በተያያዘ ዜና አዳማ ላይ መደበኛ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ/ ፥ አቶ ዓለማየሁ አቶምሳን የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ሙክታር ከድርን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል ።

የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበርን ጨምሮም ፥ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ፣ አቶ ሱፍያን አህመድ ፣ አቶ ድሪባ ኩማ ፣ አቶ አብዱልቃድር ሁሴን ፣ አቶ ኡመር ሁሴንና አቶ አበራ ሀይሉ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት አባላት ሆነው ተመርጠዋል ።

እነዚህ ስራ አስፈፃሚዎች በሚካተቱበት የኦህዴድ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት አቶ ዋቅ ቤካ ፣ አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድ ፣ አቶ ኑሬ ቀመር ፣ አቶ ሰለሞን ቁጩ ፣ አቶ በከር ሻሌና አቶ እሸቱ ደሴ ተመርጠዋል።

በተመሳሳይ ሃዋሳ ላይ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው ደኢህዴን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ሊቀ መንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ደግሞ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

ጉባኤው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ አቶ ሬድዋን ሁሴን ፣ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ፣ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ፣ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ፣ አቶ ዓለማየሁ አሰፋ ፣ አቶ ደሴ ዳልኬና አቶ ተስፋዬ በልጂጌ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል ።

ዘጠኙን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባላትን ጨምሮ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ፣ አቶ መለሰ ዓለሙ ፣ ወይዘሮ ሙፍሪያት ካሚል ፣ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ አቶ ደበበ አበራና አቶ ሳኒ ረዲን ደግሞ ለደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቋል ።

********

Compiled by Fana.

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories