የዲሲ ፖለቲከኞች የኋልዮሽ ጉዞ ታሪክ በጨረፍታ [Amharic]

Highlight:

“የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማህበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ (EHSNA) የሚባል ድርጅት ኣቋቋሙ፡፡ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜም ከ ESFNA ጋር በተመሳሳይ ጊዜ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ብርቱካንም የዝግጅቱ እንግዳEthiopian diaspora እንድትሆን ኣደረጉ -ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ፡፡ እንዲህም ኣሉን – “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለዘመናት ስታቀርበውና ስትታገልለት የነበረውን የብርቱካን የክብር እንግዳነት ጉዳይ ይሄው እውነተኛና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኣሳክተውታል፡፡ ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ፡፡ድል ለኛ ሞት ለ ESFNA” ኣሉ፡፡

የወያኔ ነው የተባለው ESFNAም ሃሳቡን ቀይሮ ብርቱካንን ጋበዘ፡፡ እንዲህ ነው ጨዋታ፡፡ “ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው ዘንድሮ 2012 ደግሞ ሌላ “የመላ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ማኅበር ኣንድ (AESAOne)” የሚባል ድርጅት ተቋቋመ፡፡

ይህ ኣጭር መጣጥፍ ዲሲ ላይ ስለመሸጉት ፖለቲከኞቻችን የህይወት ጉዞና የሰሞኑ እንቅስቃሴኣቸውን በተመለከተ የሚያማ ጽሁፍ ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲከኞች መፃፍ ለሚፈልግ ሰው ስለ ዲሲ ፖለቲከኞች መፃፍን የመሰለ ኣዝናኝ ነገር እንደሌለ በዚህ ኣጋጣሚ ልነግረው እፈልጋለሁኝ – ኣያሌ ያልተነገሩ ታሪኮች ኣሏቸውና (ስለ ኢህኣዴግ ብዙ ተጽፏል)፡፡

እነዚህ ሰዎች ባለፉት 21 ኣመታት ኣቅጣጫና መድረሻ የሌለው ተቃውሞ ሲያሰሙ የከረሙ ናቸው፡፡ ኣብዛኞቹ በትርፍ ሰኣታቸው ኣንዳንዶቹ ደግሞ እንደ ሙሉ ጊዜ ስራ (ቢዚነስ) የያዙት ናቸው፡፡ እንደ ሙሉ ሰኣት ቢዝነስ ከያዙት ውስጥ ለምሳሌ ኣበበ በለው፣ ኣበበ ገላው፣ ኣበበ በላቸው፣ ኣበበ ተክሌ፣ ኣበበ ሃይሌና ሁሉም የኢሳት ሰራተኞች ይገኙባቸዋል፡፡

ተቃውሞኣቸው የጀመረው ገና ኢህኣዴግ ምን ኣይነት መንግስት እንደሚያቋቁም ሳያውቁ፣ ዴሞክራሲያዊ ነው ኣይደለም ሳይለዩ ብቻ ኢህኣዴግ የሚባል ድርጅት ስልጣን ስለያዘ ብቻ መቃወም የጀመሩ ናቸው፡፡ በባህርያቸው ብሄር ብሄረሰቦች፣ በኣፍ መፍቻ ቋንቋ መማር፣ የራስን እድል በራስ መወሰን፣ ኦሮሚያ ክልል፣ ሶማሌ ክልል፣ ትግራይ …… ወዘተ የመሳሰሉ ቃላቶች ኣይመቿቸዉም፡፡ ከ 1983 ዓ/ም ጀምሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጥምረቶችን ኣቋቁመዋል፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፎችን ኣደራጅተዋል፣ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከደጋፊ ኣሰባስበዋል፣ ኣልፎ ኣልፎም በስድስት ወርና በኣንድ ኣመት ውስጥ ኢህኣዴግን እንጥላለን ብለው ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተው ባሉበት ጭጭ ብለዋል፡፡ ስለ ዛሬይቷ ኢትዮጵያ ሲኦልነት፣ ስለ ኢህኣዴግ ኣውሬነትና ስለ ኢህኣዴግ ደጋፊዎች ጭራቅነት ብዙ ሺ ኣርቲክሎችን ጽፈዋል፣ ኣሳትመዋል፡፡ ለበርካታ የኣሜሪካ ሴናተሮች በስልክ፣ በኢሜይል በደብዳቤ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ እንዲጣል ኣቤቱታ ኣቅርበዋል፡፡ በኣንድ ወቅትም ወደ ኤርትራ ጎራ ብለው ኣቶ ኢሳያስን ተማፅነዋል፡፡ በርግጥም የዛሬን ኣያርገውና ከ 2000 ዓ/ም በፊት ዋሽንግተን ዲሲ ለኢህኣዴግ የማትመችና የማትደፈር ከተማ ኣድርገዋት ቆይተዋል (ኣሁን ስልታዊ ማፈግፈግ ኣድርገው ይሆን?)፡፡

የውድቀታቸው መጀመርያ በ1997 ዓ/ም ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገው በብዙዎቹ ዘንድ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ነበር የተባለለት ምርጫ ነው፡፡ በወቅቱ እነዚህ የዋሽንግተን ፖለቲከኞች በኣንድ ሺ ኣመት ኣንዴ የማይገኝ እድል (Jackpot ) ከች ኣለላቸው – በምርጫ ተወዳድሮ ብዙ ወንበሮችን ባገኘው በቅንጅት በኩል ፓርላማ መግባትና በሂደት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መቀራረብና ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መንገድ ማሳመን፡፡ ሆኖም ከመጀመርያው መቃወም እንጂ ሌላ ኣላማ ኣልነበራቸውምና እድሉን ሳይጠቀሙበት ቀሩ፡፡ ፓርላማ ኣንገባም የማለታቸው ጦስም ወደ ኣንድ ሺ ኣንድ መቶ ድርጅቶች ፣ጥምረቶችና ግለሰቦች በታትኗቸው ይሄው ኣሁን ያሉበት የኋልዮሽ ጋሪ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ (እዚህ ላይ RIP ብያለሁ)፡፡ በመሆኑም ባለፉት ጥቂት ኣመታት የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅትና ኣላማ ኣጥተዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸው ሁሉ ተሰላችቷል፡፡ ስለዚህ የሚደረጉ ተቃውሞዎች በሙሉ ያልተደራጁና ኣንዳንዶቹም ኣስቂኝ ናቸው – ለምሳሌ የህዳሴ ግድብን መቃወም፣ ቻይና ለኢትዮጵያ እርዳታ እንዳትሰጥ ባንዲራዋን ማቃጠል፣ የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ስብሰባዎችን ሲያደርግ ማወክና ኣጋጣሚው ከተመቻቸም የስብሰባው ተሳታፊዎቹን መደብደብ፣ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኣየር መንገድን እንዳይጠቀሙ መወትወት፣ መንግስትን የሚደግፉ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ መዋእለ ነዋይ ያፈሳሉ ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች ስም ማጥፋት ወዘተ….. ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ዋሽንግተን ዲሲን ከማትደፈር የተቃዋሚዎች ምሽግነት ወደ ትግል ሜዳነት ቀይሯታል፡፡ ባለፉት ጥቂት ኣመታት ደጋፊዎቹን በቅፅበት ኣነቃነቀ፡፡ የተቃዋሚዎቹ ደጋፊዎች ብዛት ኣሽቆለቆለ፡፡ ከዛም ኣልፎ የዋሽንግተን ተቃዋሚዎች የተቃውሞ ኣጀንዳ የሚቀርጽላቸው የኢትዮጵያ መንግስትራሱ ሆነ፡፡ ለምሳሌ የኣባይ ግድብን እገነባለሁ ብሎ ገንዘብ ለማሰባሰብ ከፍተኛ ባለስልጣኖቹን መላክ፣ የግልገል ጊቤ ግድብን መገንባት፣ የእርሻ መሬቶች እንዲለሙ ለውጭ ኣገር ኢንቨስተሮች መሬት መስጠት፣ የእርዳታና በጎ ኣድራጎት ድርጅቶችን ኣዋጅ ማውጣት…… ኣስፈላጊ ሲሆን ደግሞ (ዋሽንግተን ጭር ካለ) ኣንድ ሁለት ጋዜጠኞችን ወይም የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ማሰር፡፡ ስለ

Jossy Romanat

more recommended stories