ወያነ-ትግራይና የሉዓላዊነት አጀንዳ | Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty

[Trouble reading: Download the article in PDF|169 kb ]

መንደርደሪያ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሰሞኑን ‹‹በኤርትራና በትግራይ ይኖሩ የነበሩ የኤርትራና የትግራይ ዜጐች ተግተው ኢጣልያንን ቢወጉ ኖሮ ከሐረር፣ ከሀድያና፣ ከሲዳሞ፣ ከሸዋ… ወደmesfin_woldemariam ሰሜን መዝመት አያስፈልጋቸውም ነበር፤ ይህ ቢሆን ዛሬ ሌሎች ያልሞቱትን ሞት በመሞታቸው አይወቀሱም ነበር›› የሚል አስገራሚ አስተያየት አስደምጠውናል፡፡ የምላስ ወለምታ ነው እንዳይባል በጽሁፍ ነው፡፡ መብራራት የሚያስፈልጋቸው ሀረጎች ቢኖሩም፤ ሰውየው ‹ኢትዮጲያዊነት›/‹ግለሰባዊነት› ወዘተ የሚሉ ጭንብሎቻቸውን በይፋ ማውለቃቸው ይመስላል፡፡ እርግጥ ጭንብሉ ድሮውንም ማንም አላደናገረም፡፡

ያም ሆነ ይህ የሰውየው ንግግር ለአፍታ ወደ ታሪክ ማህደር መመለስን ግድ ብሏል፡፡ በመሆኑም ለመንደርደሪያ ይህን በየካቲት 2000 ዓ.ም. ተጽፎ ነገር ግን ‹‹አዲሰ ነገር›› ጋዜጣ ሊያትመው ያልፈቀደው እናም ሳይታተም የቆየ ጽሁፍ ላካፍላችሁ፡፡

ጋዜጣው ለማተም ያልፈቀደበት ምክንያት ምንም ሚስጥር የለውም፡፡ ጋዜጣው ይህን ጽሁፍ ጥሎ ሲያበቃ ከጥቂት ወራት በኋላ ያተመው የፕ/ር መሳይ ከበደን ‘the underside of the Eritrean Issue’ የተሰኘ ጽሁፍ ነበር፡፡ ትኩረት የሚስበው የመሳይ ከበደ ጽሁፍ በጭብጥ የዚህ ጽሁፍ ተጻራሪ እና የመረጃ ፋይዳው አናሳ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአዲስ ነገር አዘጋጆች የመሳይ ከበደን ጽሁፍ ከ12 ወራት በፊት ከታተመበት ከኢትዮ-ሚዲያ ዌብሳይት ወስደው ወደ አማርኛ ተርጉመው ማተማቸው ነው፡፡ በነገራችን ላይ የመሳይ ከበደ ጽሁፍ ጭብጥ ‹‹ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮጲያ አንድነት በጥብቅ የሚደግፍ መሆኑን እና የትግራይ ኤሊቶች ደግሞ ኤርትራውያን ፖለቲካና ኢኮኖሚ እንዳይቀናቀኗቸው ሲሉ የኤርትራን መገንጠል እንደሚፈልጉት ›› ማሳመን ነው፡፡ የዚህ ወቅታዊ አንድምታ የጽንፈኛ ተቃዋሚዎችን ከኤርትራ መንግስት ጋር መሞዳሞድ ምክንያታዊ ለማድረግ ሲሆን በታሪካዊ ገጽታው ደግሞ የትግርኛ ተናጋሪዎች መለያየት የራሳቸው/በተለይም የትግራይ/ ጥፋት ነው የሚል ሀሳብ ነው፡፡

አሁን ፕሮፌሰሩ መስፍን በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡

እንዲያውም ‹‹ በኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ተሸፋፍኖ የቆየውን እናፍረጥርጠው ከተባለ ለማን አሳፋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው›› ሲሉም ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ ድሮውንም ያለፈ ታሪክ ለምን ይወራል ሲሉ የነበሩት እሳቸውና ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡ ሀሳባቸውን ከቀየሩም መልካም፡፡ የቀኝ አክራሪው ክፍል ፊታውራሪ ናቸውና – እንደሳቸው ሚሊዮኖችን በጅምላ መኮነን ሳያስፈልግ – ጥሬ ሀቆችንና የታሪክ ሰነዶችን በተከታታይ በዚህ ብሎግ ላይ በማቅረብ መልስ መስጠት ግድ ይላል፡፡

አሁን ወደጽሁፉ፡፡

[Trouble reading: Download the article in PDF|169 kb ]

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (2)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (3)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (4)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (5)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (6)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (7)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty [8]

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (9)

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

more recommended stories