Lidetu Ayalew | የኢዴፓ መግለጫ – ሌላኛው የማይፈፀም የተቃዋሚዎች የመተካካት ተስፋ?

ኢዴፓ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ 5ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ.ም እንደሚያሂድ የገለፀ ሲሆን ጉባዔው የስራ ጊዜውን የጨረሰውን አመራር በማሰናበትም ለሚቀLidetu-Ayalew_&_Mushe_Semuጥሉት ሁለት አመታት ፓርቲውን የሚመራውን የአመራር አካል እንደሚመርጥ፤ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና የፖለቲካ ፕሮግራም ላይ ሊያሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ከተገኙ እንደሚያሻሻል እና ከዚህም በተጨማሪ ጉባኤው የፓርቲውንና የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአቋም መግለጫ እንደሚያወጣ ጠቁሟል፡፡

አቶ ልደቱ አያሌው ለ ‘2 ተርም’ በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ በመሆኑ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በድጋሚ መመረጥ የማይችሉ ሲሆን እሳቸውም ደንቡን አክብረው ከፕሬዚዳንትነት መንበር እንደሚለቁ በተደጋጋሚ ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡ መግለጫው ይህን አስመልክቶ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ይሁንና ዛሬ እሁድ የታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ ኢዴፓ ባለፈው ሐሙስ በግዮን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ‘ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉት አቶ ልደቱ አያሌው፣ መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ.ም. በሚካሄደው 5ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ’ አንዳስታወቁ ዘግቧል፡፡

በ1997 በተካሄደው የፓርቲው ጉባዔ በተመሳሳይ አቶ ልደቱ ከዋና ፀሀፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ አቶ አንዱአለም አራጌ (ያኔ የልደቱ ምክትል አሁን የአንድነት አመራር) እና ሌሎች አባላት  በአመራርነት እንዲቀጥሉ በለቅሶና በልመና ያቀረቡላቸውን ጥያቄ ተቀብለው በፕሬዚዳንትነት መመረጣቸውን የጉባዔው ቪዲዮ ያሳያል፡፡ በኢዴፓ የመጀመሪያው ጉባዔ በ1993 ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡት ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ የነበሩ ሲሆን፤ በ1997 በተካሄደው በ3ኛው የድርጅቱ ጉባዔ ላይ እስከዚያ ድረስ ዋና ፀሀፊ የነበሩት አቶ ልደቱ ዶ/ር አድማሱን ተክተው በፕሬዚዳንትነት እንደተመረጡhailu_shawol ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል ከሊቀመንበርነታቸው እንደሚለቅቁ ከሰኔ 2002 ጀምሮ እስከዚህ ወር (ታህሳስ) በተደጋጋሚ ሲገልጹ የነበሩትና ከምርጫ ወዲህ ቢሮ ገብተው የማያውቁት አቶ ሀይሉ ሻውል ባለፈው እሁድ  በተካሄደው የድርጅታቸው ጉባዔ ብቻቸውን ተወዳድረው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ከኦፍዴን ፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው እንደሚለቅቁ ከክረምት ጀምሮ ሲገልጹ የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ታህሳስ 7/2003 በተካሄደው የድርጅታቸው ጉባዔ የበላይ ጠባቂ በሚል ማዕረግ እንዲቀጥሉ መመረጣቸው ተዘግቧል፡፡ አዳዲስ አመራሮች እንደሚመጡ አመልክተው የነበር ቢሆንም ፕሬዚዳንትነቱን የተረከቧቸው ፓርቲው ከተመሠረተ ጀምሮ የአቶ ቡልቻ ምክትል የነበሩት ዶክተር ሞጋ ፍሪሳ ናቸው፡፡

የአንድነት እና ሌሎች የመድረክ ፓርቲ አመራሮች ደግሞ ጭራሹኑ ስልጣን የመልቀቅ ሀሳብ የሌላቸው ሲሆን ይህን አስመልክቶ ከሚዲያ የሚቀርብላቸውን ጥያቄም ‹ኢሕአዴግ መተካካት ስላለ እኛም ያንንMedrek_party_leaders ተከትለን መሄድ አይጠበቅብንም› በማለት እንደሚያጣጥሉት ይታወቃል፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት በአንድ ጊዜ በርካታ ፓርቲዎችን በመምራት የሚታወቁት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም የመልቅ ሀሳብ የላቸውም፡፡

ከዚህ አንፃር በተነፃፃሪ ‘ወጣት’ የሆኑት አቶ ልደቱም የመተደዳሪያ ደንቡን በማሻሻል በፕሬዚዳንትነት ቢቀጥሉ የሚገርም አይሆንም፡፡ ይሁንና ከሌሎች ፓርቲዎች መሪዎች ልቀው መታየት የሚፈልጉትና በፓርቲ አመራር የብሔር ተዋጽኦ በማሳየት አስፈላጊነት የሚያምኑት አቶ ልደቱ የፕሬዚዳንትነቱን መንበር ቢያንስ ለአንድ ተርም እንደሚለቅቁ ይጠበቃል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው እንዳሉት ፕሬዚዳንትነቱን የሚለቅቁ ከሆነ ከሆነ የሚተኳቸው ም/ፕሬዚዳንቱ አቶ ሙሼ ሰሙ ወይም ዋና ፀሀፊው አቶ መስፍን ነመራ እንደሚሆኑ ይገመታል፡፡ አቶ ሙሼ ሰሙ ከጉራጌ ብሔር ሲሆኑ ወይም አቶ መስፍን ነመራ ደግሞ ከኦሮሞ ብሔር ናቸው፡፡

የፓርቲው መሪ ከ 2 ጊዜ በላይ መመረጥ እንደማይችል ብቻ የስልጣን ዘመን በመተዳደሪያ ደንብ ደረጃ በመገደብ ኢዴፓ በኢትዮጲያ ብቸኛው ፓርቲ ሲሆን ተመሳሳይ አሠራር ስለሚከተሉ የሌላ ሀገርBeyene Petros ፓርቲዎች መረጃ የለንም፡፡ ሆኖም ከዚህ በፊት በዚህ ድረ-ገጽ (danielberhane’s blog) ላይ የቀረበው መረጃ እንደሚያመለክተው በበርካታ የአውሮፓና ሌሎች የምዕራብ ሀገራት አንድ ግለሰብ በሀገር መሪነት ከ4 ተርም ወይም/እና ከ20 ዓመታት በላይ፣ በፓርቲ መሪነት ደግሞ ከዚያም በላይ ለረዘመ ጊዜ ሲቆዩ በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ [ጽሁፉን እዚህ ያንብቡ (Link)]

የሀገር መሪን የስልጣን ቆይታ በሁለት ተርም የመገደብ አሠራር ፕሬዚዳንታዊ ስርዐት በሚከተሉት በዩ ኤስ አሜሪካ እና በላቲን አሜሪካ ሀገራት የሚታይ ሲሆን፤ በዩ ኤስ አሜሪካ ገደቡ የተጣለው ከፍራነክሊን ዲ. ሩዝቬልት በኋላ ነው፡፡ ዲሞክራቱ ሩዝቬልት በአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ከ1933-1945 ያገለገሉ ሲሆን፤ በ1945 ለ4ኛ ጊዜ ከተመረጡ ከወራት በኋላ በህመም መሞታቸው ይታወቃል፡፡ በፕሬዚዳንት የስልጣን ዘመን ላይ ገደብ የጣለውም የሩዝቬልት ተሞክሮ እንዳይደገም የሰጉት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት አብላጫውን በያዙበት በ1951ዱ ኮንግረስ በፀደቀው 22ኛው የሕገመንግስት ማሻሻያ አዋጅ ነው፡፡ ሪፐብሊካኖች ሩዝቬልትንና ፖሊሲዎቻቸውን ፖፑሊስት(populist) እና ሶሻሊስት አድርገው የሚቆጥሩ/የሚከሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ፓርላሜንታዊ ስርዐት በሚከተሉ ሀገራት ረገድ  የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ቆይታ በሁለት ተርም የመገደብ አሠራር ያላት ሀገር ቻይና ናት፡፡

የኢዴፓን መግለጫ ከዚህ በታች ያንብቡ፡፡

**************************************

ኢዴፓ መጋቢት 11 ቀን 5ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል

ኢዴፓ መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ.ም 5ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ ያካሂዳል፡፡ በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ከ250 በላይ የሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው ድርጅታዊ መዋቅር ተወካዮች የሚሳተፉ ሲሆን ጉባኤው በተለያዩ አበይት አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዶ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል፡፡

ጉባኤው የማዕከላዊ ኮሚቴውን የሁለት አመት የስራ ክንውንና የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የስራ ሪፖርቶችን አዳምጦ ያጸድቃል፡፡ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና የፖለቲካ ፕሮግራም ላይ ውይይት በማድረግም ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ከተገኙ የማሻሻያ ውሳኔዎችን ይሰጣል፡፡ የስራ ጊዜውን የጨረሰውን አመራር በማሰናበትም ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ፓርቲውን የሚመራውን የአመራር አካል ይመርጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጉባኤው የፓርቲውንና የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአቋም መግለጫ ያወጣል፡፡ ጉባኤው ሊወያይባቸው ይገባል ተብለው የታሰቡ አስር ወቅታዊ ጉዳዮች አስቀድመው ተመርጠው በአሁኑ ወቅት በየሳምንቱ በፓርቲው አባላት ተከታታይ ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውይይቶች የሚመነጩት ሃሳቦች ተጨምቀው ለጉባኤው በረቂቅነት የሚቀርቡበት ሁኔታ እየተመቻቸ ይገኛል፡፡

ጉባኤው በጥልቀት ተወያይቶ አቋሙን ይገልጽቸዋል ተብለው የሚጠበቁት ዋና ጉዳዮች፡-

1.    በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሊብራል ዴሞክራሲ አዋጭነት፣
2.    ህገ-መንግስትና ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ፣
3.    ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣
4.    ወቅታዊ ማሕበራዊ ጉዳዮች፣
5.    ወቅታዊ የውጭ ጉዳዮች፣
6.    ምርጫ 2002 እና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ወቅታዊ የኃይል አሰላለፍ፣
7.    የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋናኞችና ወቅታዊ ሚናቸው፣
8.    የተቋማት ሚና በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት፣
9.    የፖለቲካ ፓርቲዎች የትግል ስልት፣
10.   የኢዴፓ የወደፊት ዋናዋና የትግል አቅጣጫዎች የሚሉ ናቸው፡፡

ኢዴፓ 5ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤው በስኬት ተጠናቆ ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴው ውጤታማ ይሆን ዘንድ ከህብረተሰቡ የተለያዩ ተሳትፎዎችንና እገዛዎችን ይጠብቃል፡፡ ለጉባኤው በመወያያ ሃሣብነት በሚቀርቡ ጉዳዮች ዙሪያ አባላት የሚያደርጓቸው ውይይቶች እስከ ጉባኤው እለት ድረስ በየሳምንቱ በጋዜጦች አማካኝነት ይፋ ስለሚደረጉ ህብረተሰቡ እነዚህን ውይይቶች እየተከታተለ የራሱን አስተያየት እንዲሰጥባቸው፣ጋዜጦችም እነዚህን የውይይት መነሻ ሃሳቦች ለህዝብ በማቅረብ ረገድ ትብብር እንዲያደርጉ ኢዴፓ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ ህብረተሰቡ ኢዴፓ ሊያሻሽላቸው ይገባል ብሎ የሚያምንባቸው የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብን የሚመለከቱ ሃሳቦች ካሉም ጥቆማዎቹን ተቀብሎ ለጠቅላላ ጉባኤው ውይይት ለማቅረብ ያለውን ፍላጎት ይገልጻል፡፡

ከፊታችን የሚካሄደው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ፓርቲውን በሃሳብ ብቻ ሳይሆን በሰው ኃይልም የተጠናከረ እንዲሆን የማድረግ አላማ ስላለው በፓርቲው የፖለቲካ ፕሮግራም እምነት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም በፓርቲው አባልነት እየተመዘገቡ በፓርቲው ውስጥ የጎላ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አዴፓ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ ይህንን ድርጅታዊ ጉባኤ በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ለማድረግም ሆነ ከጉባኤው ማግስት ፓርቲው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርን በምርጫ አሸንፎ ለመረከብ የሚያደርገው ትግል ለውጤት እንዲበቃም የፓርቲውን አላማ የሚደግፉ የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ እርዳታ በማድረግ ፓርቲውን እንዲያጠናክሩ ኢዴፓ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

******************************************

Daniel Berhane

more recommended stories