Jan 17 2016

አባይ ፀሐዬ፡- "የኦሮሞ ሕዝብ ማን እንደዘረፈው፣ ማን እንደበደለው ያውቃል" [ጽሑፍና ቪዲዮ]

በሚኒስተር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አባይ ፀሐዬ ባለፉት ሳምንታት በማስተር ሰበብ በኦሮሚያ ከተከሰተው ተቃውሞ በተያያዘ አንዳንድ አካላት በትግራይና በህወሓት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ የሚያደርጉት አጀንዳ ለማስቀየስ ነው አሉ፡፡

የህወሓት መስራች እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነት አባይ ፀሐዬ ይሄን የገለጹት በተለይ ለሆርን አፌይርስ በሰጡት አስተያየት ነው፡፡

ከሰሞኑ የዲያስፖራው ሚዲያ ኦ.ኤም.ኤን የእሳቸውን ድምጽ የተቆራረጠ ቅጂ በማቅረብ፣ ታህሳስ 20 በጎንደር ከተማ ታህሳስ አባይ ፀሐዬ እና የመከላከያ ሚኒስተር ሲራጅ ፈርጌሳ የመሩት ስብሰባ መካሄዱን፣ በዚያ ስብሰባ አቶ ሙክታር እና አባዱላ ገመዳ እንደተገኙበት እና አባይ ፀሐዬ በኦሮሚያ ከተከሰተው ተቃውሞ በተያያዘ ተግሳጽ ሰጡ በማለት የተሰራጨው ነበር ለአስተያየታቸው መነሻ የሆነው፡፡

አባይ ፀሐዬ የዘገባውን መሠረተ-ቢስነት የገለጹ ሲሆን፤ በማከልም የዚህ ዓይነት ወሬ የሚነዛበትን መነሻ ዘርዘር አድረገው ገልጸዋል፡፡

ደካማ ኢንተርኔት ላላቸው አንባቢያን ይረዳ ዘንድ የአባይ ፀሐዬን አስተያየት በከፊል በጽሑፍ አቅርበነዋል፡፡

[ቪዲዮውን ከታች ማየት ይችላሉ፡፡]
———

Photo - Abay Tsehaye and Daniel Berhane

Photo – Abay Tsehaye and Daniel Berhane

መጀመሪያ፡- ዘንድሮ ሆነ አምና ካች አምና ጎንደር ሄጄ አንድም ስብሰባ አላደረግሁም፤ አንድም ስብሰባ፡፡ ብቻዬንም ሆነ ከተጠቀሱት ሀላፊዎች ጋርም ሆነ አንድም ስብሰባ አላደረግሁም አልካፈልኩም፡፡ ስለዚህ የሌለ ነገር ነው ከየት እንዳመጡት አላውቅም፡፡ ቪዲዮውን በሙሉ ቢያመጡት ከነንግግሬ ከነምስሌ ጥሩ ነበር፡፡ ለምን እንደዚያ አያደርጉም? ፈጠራ ነው፡፡ ሆን ተብሎ የሚደረግ ያለ ነገር ነው፡፡ ባልሄድኩበት ቦታ ባተሳተፍኩበት ስብሰባ፡፡ እንደዚያ ዓይነት ስብሰባ መኖሩንም እኔ አላውቅም፡፡ እነአባዱላም ሄደው ከሆነ እነሲራጅም ሄደው ከሆነ አላውቅም፡፡

ከዚህ በፊትም ‹‹ወደዱም ጠሉም ልክ እናስገባቸዋለን ማስተር ፕላኑ የግድ ተግባራዊ ይሆናል ብሏል አባይ›› ተብሎ አምና በሰፊው በድረ-ገጽ በተደጋጋሚ ያቀርቡት እንደነበር ሰምቼ፤ ‹‹ምንድነው ይሄ ነገር እስኪ አንድ ነገር በል›› ብለውኝ [መልስ ሰጥቼ ነበር]፡፡ ይሄ ነገር የለም፡፡

የከተሞች አስተዳደሮች እናሰለጥን ነበረ በሀገር አቀፍ ደረጃ፡፡ እኔ ስለከተማ ፖሊሲ አስተምር ነበር ፡፡ ባጋጣሚ እዚያ ላይ ‹‹የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዴት ነው እያከራከረ ነው›› የሚል ተነሳ፡፡

አንደኛ [ማስተር ፕላኑ] ጠቀሜታ አለው የትም ሀገር የሚሠራበት ነው፡፡ እነኚህ ትላልቅ ሜትሮፖሊታን የሚባሉ ከተሞች – ዋና ከተሞች እና ትላልቅ የኢንዱስትሪና የንግድ ማዕከሎች – ከአካባቢያቸው ከተሞች እና ገጠሮች ጋር ተሳስረው ነው የሚያድጉት፡፡ ትልቅ ዕድል ነው ትልቅ ከተማ አጠገብ መሆን፡፡ በአካባቢው ያሉ አነስተኛ ከተሞች፣ መካከለኛ ከተሞች እና ገጠሮችን ይዞ ነው የሚወጣው ትልቁ ከተማ፡፡ ይሄ የትም ዓለም የሚደረግ ነው፣ የትም ዓለም የሚሠራበት ነው፡፡ ስለዚህ ምንም ጉዳት የለውም፡፡

ሁለተኛ የአዲስ አበባ መስተዳድር እና የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር አቶ ኩማ የአዲስ አበባ ከንቲባ በነበረበት ግዜ አቶ ሙክታር የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት እያለ በጋራ ያቋቋሙት ኮሚቴ ይሄ ማስተር ፕላን ሲሠራ ሲረቀቅ በባለሙያዎች የሚመራ የጋራ ኮሚቴ ከአዲስ አበባ መስተዳድር እና ከኦሮሚያ ክልል መስተዳድር በእኩል ቁጥር የተውጣጣ ኮሚቴ ነበር፡፡ ስለዚህ ከመጀመሪያው ፈቅደው ፈልገው የገቡበት ነው የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር፡፡ ማንም አላስገደዳቸው ወይም እነሱ ሳይካፈሉበት የተሠራ ማስተር ፕላን አይደለም፡፡ ይጠቅማል ብለው በጋራ ሲሠሩት የነበረ ነው፡፡ ለመስተዳድር አካላቱም ለባለሙያዎቹም በየጊዜው እየቀረበ ምክክር ይደረግበት የነበረ ነው፡፡

ሦስተኛ ማስተር ፕላኑ ሌላ ትርጉም ተሰጠው – የተሰጠው ትርጉም በኋላ እመጣበታለሁ – ግን በሆነ ምክንያት የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ኃላፊዎች ሳይሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አንዳንድ አስተዳደሮች እና የተወሰኑ ምሁራን አካባቢ ይመስለኛል ማስተር ፕላኑን በትክክል አልተረዱትም ነበር፡፡ ስለዚህ እንዲረዱት ብለው ደግሞ በጋራ ስብሰባ አድርገው አስረድተዋቸው ነበር፡፡ በኋላ የሆነ ግርግር ተነሳ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ፡፡ ይሄ ማስተር ፕላን የኦሮሚያን ክልል መሬት ወደ አዲስ አበባ ለማካለል ነው፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለውን የኦሮሚያ ልዩ ዞን አስተዳደሩን ለማፍረስ ነው፣ አርሶ አደሩን ለማፈናቀል ነው፣ ምናምን የሚል ነገር ተወራ፡፡ የማስተር ፕላኑ ውይይት በባለሙያዎችና በሀላፊዎች ደረጃ ስለነበር፣ ቶሎ ወደህዝቡ ስላልወረደ ስለዘገየ ወርደን ቶሎ እናስረዳ ተብሎ የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር በየአካባቢው ማብራሪያ ሰጡ፡፡

ስለዚህ እኔ ያኔ ስልጠና ላይ ያልኩት ምንድን ነው፤ አብረው የሠሩት ነው -የአዲስ አበባ መስተዳድር እና የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር – ተመካክረው በጋራ እየመሩት የተሠራ ነው፡፡ አሁንም አንዳንድ ብዥታዎች ሲፈጠሩ ማብራሪያ እየሰጡ ነው፤ ስለዚህ አስረድተን እንቀጥልበታለን እያሉ ስለሆነ እስከተስማሙ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል፤ ካልተስማሙ ነው ተግባራዊ የማይሆነው እንጂ ነው ያልኩት፡፡ ይቺ ናት፡፡ በግድም በውድም ወደዱም ጠሉም ተግባራዊ ይሆናል የሚል ቃል የለም፡፡ ቪዲዮው አለ፡፡ ምንም የለም፡፡ ስለዚህ አሁን ብለሀል አላልክም አይደለም፡፡

የጎንደሩም ጠቅላላው ያልነበርኩበት ስብሰባ ነው፡፡ እዚህም ጠቅላላ ያላልኩት ነው፡፡ ደግሞ ፓራግራፍ ወይም ሙሉ ዓረፍተ-ነገሩን እንኳን አያመጡትም ከነድምጼ፡፡ ይሄ አለ ብለው ነው ሐረግ የሚያመጡት – የኔ ድምጽ የለም፡፡ እንዴ ይሄ ያስጠይቃል ያስከስሳል፡፡ የኔ ድምጽ የሌለበት፣ ሙሉ ሙሉ ዓረፍተ-ነገሩ ወይም ሙሉ ፓራግራፉ የሌለበት፣ አንዳንዱ ደግሞ ባልነበርኩበት ቦታ ባልነበርኩበት ስብሰባም ነበረ እሱ እዛ ነው የተናገረው እየተባለ ነው ፈጠራ የሚደረግ ያለው፡፡ ይሄ አላልኩም ሀሰት ነው – የመጀመሪያ መልስ ነው፡፡

ዋናው መልሴ ግን ለምን እንደዚህ እንደሚያደርጉ ነው፡፡ እነኚህ በዚህ በሁከትና በግርግር ሊጠቀሙ የሚፈልጉ ያሉ ኃይሎች፤ እኔን እና ሌሎችን እንደዚህ መርጠው ስማቸውን ሊያጠፉ፣ ሊያጥላሉ፣ ከሕዝቡ ጋር ሊያጋጩ፣ አጀንዳውን ወደሌላ አቅጣጫ ሊወስዱት የሚፈልጉ ያሉ ምክንያታቸውን በግልጽ ሕዝብ ቢያውቀው ጥሩ ነው፡፡

አንደኛ ምክንያታቸው በዚህ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚባል አካባቢ እዚያ ያሉ አንዳንድ አስተዳደሮች እና አዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ባለሀብቶች – የኦሮሚያ ባለሀብቶችም የሌላ ብሔር ባለሀብቶችም – በተለያየ ህገወጥ መንገድ የያዙት የወሰዱት የቸበቸቡት መሬት አለ በስፋት በብዛት፡፡ ሁለቴ ተገላብጦ የተሸጠ የተለወጠ መሬት አለ፡፡ የቸበቸበው እዚያ ያለ አስተዳደር ነው፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር አይደለም፡፡ የገዙት በርካታዎቹ አየር ባየር ነጋዴዎች ናቸው – ጤናማ ነጋዴዎችም የገቡ ይኖራሉ፡፡

ማስተር ፕላኑ እነኚህን ከተሞችና ገጠሮች ከአዲስ አበባ ጋር ሊያቀናጅ በመሠረተ-ልማት በውሀ በመንገድ በባቡር በትራንስፖርት ገበያ ሊያቀናጅ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለ የኦሮሞ ህዝብ አትክልትና ፍራፍሬ ጥራጥሬ ለስጋና ወተት የሚሆን የእንስሳት ተዋጽዖ ሊያቀርብ እንደዚህ ዓይነት ፕላን ነው ያለው፡፡ የአግሮ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ፡፡ ስለዚህ በንግድ በግብይት በመሠረተ-ልማት እንዲተሳሰሩ ነው እንጂ የኦሮሚያን ቅንጣት ያህል መሬት ወደ አዲስ አበባ ለማካተት ያሰበ ማስተር ፕላን የለም፡፡

ለምን ወደዚህ ተረጎሙት፤ ይሄ ነገር ተግባራዊ ይሁን ሲባል፤ መሬቱ እንዴት ይልማ መሠረተ-ልማቱ እንዴት ይዘርጋ ኢንቨስትመንት እንዴት ይሁን ሊባል ነው፡፡ የተዘረፈ መሬት እና የዘረፈ ያስዘረፈ ያኔ ሊታወቅ ነው፡፡ ያኔ ሊገኝ ነው፡፡ ስለዚህ ከአስተዳደሩ አንዳንድ አካላት አሉ፡፡ ከነጋዴውም በዚህ መንገድ የዘረፉ አሉ፡፡ ይሄ እንዳይታወቅ ነው ማስተር ፕላኑ ሊያፈናቅላችሁ ነው፤ የኦሮሚያን ክልል መሬት ሊወስድ ነው ወደ አዲስ አበባ በሚል ተርጉመው አጣመው ወደ ግርግር እና ወደ ብዥታ የወሰዱት፡፡ አንዱ ትልቁ ምክንያታቸው ይሄ ነው፡፡ ስለዚህ ጥቂት የአስተዳደር አካላት አሉ፡፡ ይሄን መሬት መቸብቸብና መዝረፍ ላይ የተሳተፉ የተወሰኑ ነጋዴዎች አሉ፡፡ ይሄ ጉዳቸው ይሄ ገበናቸው እንዳይጋለጥ በዚህ ሂደት ነው ቀድመው የተከላከሉት፡፡ ያኔ ይሄ ነው ምክንያቱ፡፡

አሁን ደግሞ ሁለተኛ ምክንያት አለ፡፡ መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ፡፡ ይሄን ችግር የኔ ችግር ነው ብሎ መፍትሔ አስቀምጦ ቶሎ ይሄን ችግር እፈታለሁ ከሕዝብ ጋር ሆኜ ብሎ አወጀ፡፡ በኢሕአዴግ ጉባዔ ታወጀ፣ በየድርጅቱ ጉባዔ ታወጀ፣ በመንግስት ታወጀ፡፡ አሃ! የመልካም አስተዳደር ችግር ሊፈታ ከሆነ ሌባው መሬት የቸበቸበው ጉቦ የሰጠው ጉቦ የተቀበለው ሌላ ግፍና በደል ህዝብ ላይ ያደረሰው ህዝቡ ሊያጋልጠው ነው ሊጠየቅ ነው፡፡ ይሄ ከመምጣቱ በፊት ማስተር ፕላን ብለን ምን ብለን ግር ግር እንፍጠር የሚል ደግሞ አሁን የጨመሩት ተጨማሪ ምክንያት ነው፡፡

መሠረታዊ ምክንያቶቹ እነዚያ ሆነው፤ ከዚያ አልፎ ደግሞ የተወሰንን ግለሰቦች የተወሰንን ግለሰቦች ላይ – እኔም ሌሎችም ላይ – የሚያነጣጥሩበት ምክንያት ምንድነው፤ ይሄ ሁላ ያበላሹት የዘረፉት ያስዘረፉት ጥቂት ነጋዴዎችና ጥቂት የኦሮሚያ ልዩ ዞን አስተዳደር አካላት ናቸው ያፈናቀሉት ህዝቡን ካሣ ስጡት ተበለው ካሣውን የበሉት እነሱ ናቸው፡፡ እነሱ እንዳይጠየቁ ባንድ በኩል ማስተር ፕላን ነው ይባላል፡፡ በሌላ በኩል ህወሓት ነው ፌዴራል መንግስት ነው፡፡ የማይመለከተው እጁ የሌለበት አካል እዚህ ጉዳይ ላይ ተጠያቂ ሊያደርጉ፡፡ ተጠያቂዎቹ ሌላ ሰው ተጠያቂ እያደረጉ ነው ያሉት፡፡

ህወሓት እዚህ ውስጥ ምን አገባው? ህወሓት ፌዴራል መንግስቱን አያስተዳድረው፣ ህወሓት አዲስ አበባን አያስተዳድረው፣ ህወሓት ትግራይን ነው የሚያስተዳድር ያለው፡፡ በፌዴራል መንግስት ደግሞ እንደሁሉም ሌሎች የኢሕአዴግ አካላት ተሳታፊ ነው፡፡ ለምንድነው ህወሓት ላይ የሚነጣጠር ያለ ለምንድነው? እንዳንድ የሕወሓት አመራሮች ላይ የሚያነጣጥሩብን ያለው ለምንድነው? የትግራይ ህዝብና ሕወሓት ላይ የሚያነጣጥሩ ያለው የዘር ጥላቻ ለመቀስቀሰ ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብ መሬቴን የዘረፋችሁ ያስዘረፋችሁ እናንተ በጉቦ የመዘበራችሁኝ እናንተ ፍትሕ የከለከላችሁኝ የማዳምጡኝ እናንተ እያላቸው እያለ፤ እነኚህ አንዳንድ እዚህ [ልዩ] ዞን አካባቢ ያሉ ወረዳ አካባቢ ያሉ ከተማ አካባቢ ያሉ፤ አይ እኛ አይደለንም ህወሓት ነው፣ አይ እኛ አይደለንም ማስተር ፕላኑ ነው፣ አይ እኛ አይደለንም ኢህአዴግ ነው ብለው ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊያስቱ፤ ህዝቡ ደግሞ ገብቶታል፤ እናንተ ናችሁ! ዞር በሉ ሂዱ ወይ አስተካክሉ ነው ያላቸው ወረዳ አስተዳደሮቹን ከተማ አስተዳደሮቹን ሌሎች ሀላፊዎችን፡፡ ስለዚህ ህዝቡ የሚጠይቀው ያለ የመልካም አስተዳደር ችግር ፍቱ ነው፣ የቸበቸባችሁት መሬት የዘረፋችሁት መሬት መልሱ፣ ለምንድነው እንደዚህ ያደረጋችሁት ነው፡፡: የበላችሁት ጉቦ፣ የበላችሁት ለኛ የተፈቀደ ካሣ፣ አፈናቅላችሁን በትናችሁን የቀራችሁ እናንተ ናችሁ ነው የሚል ያለው፡፡

በነሱ ላይ ያነጣጠረውን የህዝብ ጥያቄ ወደፌዴራል መንግስት፣ ወደ ህወሓት፣ ወደ አባይ ፀሐዬ፣ ወደ እገሌ ወደ እገሌ አቅጣጫ ማሳት ማወናበድ ነው የተያያዙት፡፡ እውነቱ ይሄ ነው፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ ግን ያውቃል፡፡ ማን እንደዘረፈው፣ ማን እንደበደለው፣ ማን እንዳጉላላው፣ ማን እንደዘረፈው፣ ማን እንዳፈናቀለው ያውቃል፡፡ ይዟቸዋል አጥብቆ፡፡ አምጡ መልስ፣ ፍቱ ይሄን፣ እናንተ ናችሁ ብሏቸዋል፡፡ ወደዚያ ወደዚህ ቢያደርጉት አሁን የለም፡፡ በደንብ አስተውሏል የኦሮሚያ ህዝብ፡፡ ጥቅሙን ያውቃል መብቱን ያውቃል፡፡ የሚጎዳውንና የሚጠቅመውን ያውቃል፡፡ የኦሮሚያ ሕዝብ ነው ምሥክራችን፡፡ የኦሮሚያ ሕዝብ እየጠየቀ ያለው ጥያቄውን ይመልሱ አስተዳደሮቹ ነው እያለ ያለው፣ ፀረ-ሰላም ሀይሎቹን ደግሞ እዚህ ውስጥ አይግቡብን ነው እያለ ያለው፡፡ ምንም አያደርጉልንም፣ የሠራልንም ኢህአዴግ ነው ኦህዴድ ነው፣ ጉድለትም ያለው ደግሞ እንደወገን እንደልጆቻችን እስኪ ይቺንም አስተካክሉ እቺንም አርሙ ነው የምንላቸው ያለን ነው የሚል ያለው፡፡ እንደልጆቹ ነው ምክር የሚሰጥ ያለው፤ እርምት የሚሰጥ ያለው፡፡ ስለዚህ በዚህ መንገድ ነው መታየት ያለበት እና አጀንዳቸው የዘር ጥላቻ መቀስቀስ ነው፡፡ አጀንዳቸው እነሱ እያሉ በዳዮቹ ሌላውን በዳይ ለማስመሰል ነው፡፡
———-
ቪዲዮውን ይመልከቱ 

***************

36 Comments
 1. yantewu

  Demo yihe gazetegna tabiyewu tarbatbito limot new ende? minawu shegut eyasayek new ende kala meleles yemitargelat? tiyake matayek men yasfarahal? demtsu lay demo esu erasu astayetun mastet eyachala ante leading question eyatayekawu new….menem neger yelelawu menamen eyalk….endane betmot yeshalakl..fasam gazetegna…

  Reply
  1. how to get free coins hill climb racing cheatnengine

   This book really resonates with me because I remember that as a teenager I was always struggling with "optimism" but over time it has just become habitual. Now, no matter what happens, it seems that I am almost incapable not to immediately look for the best in the situation and I have an attitude that I will always bounce back. I think I was able to develop it through consistent practice and completely agree that this can be learned. Awesome Note, book and episode.

 2. ስናይፐር

  ኣቦይ አንተ ወራዳ በቅርብ ግዜ ዋጋህን ታገኛለህ ጠብቅ ሺ ግዜ ብታስተባብል አንተን እንዴት በእጃችን እንደምናስገባ 100 በመቶ አትጠራጠር እስከዝያው ያንተ ጠባቅዎች ከግንብ(ከብርት)የተሰራ እንደሆነ እስት እናያለን:;አንተ ሌባ

  Reply
 3. tow

  ኣቦይ አንተ ወራዳ በቅርብ ግዜ ዋጋህን ታገኛለህ ጠብቅ ሺ ግዜ ብታስተባብል አንተን እንዴት በእጃችን እንደምናስገባ 100 በመቶ አትጠራጠር እስከዝያው ያንተ ጠባቅዎች ከግንብ(ከብርት)የተሰራ እንደሆነ እስት እናያለን:;አንተ ሌባ

  Reply
 4. bt

  ይህ መልስ የፌስቡክ እስላማዊ ምሊሻ መሪዎችን እውቅና እንደመስጠት እቆጥረዋለሁኝ።የግለሰብን ስይሆን አንድን ብሄር ብሎም ሀይማኖት ለማጥፋትና አገርን ለማተራመስ የሚቃዥ አሸባሪ ግለሰብ ምኑ ነው? እጅግ የሚያሳዝነው ግን ቤት ውስጥ በተፈጠረ ችግር የሺዎች ህይወት የጠየቀ ህገ መንግስት በአንድ ራሱን ማሸነፍ ያቃተው ድርጅት መግለጫ ሲፈርስ ማየት ነው።

  Reply
 5. Oromo

  Abay Tsehaye, we know that you are a pathological liar. May be the only truth you told unwittingly here is the naive confession that the Oromo land is being cashed out at alarming rate at the expense of the poor farmers by “few dishonest” Trojan horses aka OPDO. The other naive confession also included the complete lack of rule of law under your government. If there were a rule of law, criminals in your Trojan horse organization would be brought to justice. But how can that be done when you and your fellow TPLFites, the role-models for your Trojan horses, are immersed in a cesspool of corruption from land grabbing to outright extortion! Also, what is not surprising is the complete disregard of the ongoing daily massacre of Oromos by your thuggish army. You never bothered to mention the fact that more than 200 innocent Oromos are already murdered since November 12, 2015 by your government and the murder has even escalated as you speak; while you are willing to lie at length to defend yourself. The lives of people never matter to you because you are immune to any of the human frailty; your the superman, aren’t you? But in fact your are like the “Bloody Mary” of England, who had a passion for burning people at the stake, particularly people who opposed her ideologies, or Heinrich Himmler of Germany, the leader of the SS, Chief of Nazi German Police, and head of the Gestapo, who personally coordinated the deaths of nearly 10 million people. Don’t you ever forget that a time is coming when you will face justice!

  Reply
 6. Hadush Hagos

  አድናቂህ ነኝ አባይ ፀሃየ!–Best response ever……

  ጎበዝ ቆም ብለን ብናስብ ጥሩ ነው:: አንዳንድ ብሽቅ ሰዎች ስለወያኔና ስለትግሬዎች ካላነሳቹ ይነስራችኋል መሰለኝ!
  በየድህረ-ገፁ ሰው ከመስደብ ስለ ዳቦህ ብታስብ የተሻለ ይመስለኞል::

  Reply
 7. Iddosa Mengistu

  Abay Tsahaye, R U blaming OPDO? How could U dare to say that if OPDO has equal status as TPLF in EPRDF? Did OPDO interfere in any Tigray affairs? So, why do U interfere in Oromiya’s affairs? If the problems are b/n OPDO Officials & Oromo, U don’t have been send ur brainwashed Agazi to kill Us, U don’t have interferd in our problem, simply We can Solve our problem with our OPDO officials. U are just a motharfuker Idiots;

  Reply
 8. Guta Bulcha

  አባይ በጣም አልዘገየም? መወጂ ከሆነ መተገበሩን ለማን ተዋችሁ?

  አባይ ፀሐዬ “….በሀገር አቀፍ ደረጃ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ፡፡ ይሄን ችግር የኔ ችግር ነው ብሎ በኢሕአዴግ ጉባዔ ታወጀ፣ በየድርጅቱ ጉባዔ ታወጀ፣ በመንግስት ታወጀ፡፡ አሃ! የመልካም አስተዳደር ችግር ሊፈታ ከሆነ ሌባው መሬት የቸበቸበው ጉቦ የሰጠው ጉቦ የተቀበለው ሌላ ግፍና በደል ህዝብ ላይ ያደረሰው ህዝቡ ሊያጋልጠው ነው ሊጠየቅ ነው፡፡“ …
  አባይ ፀሐዬ ለዚህ ብላችሁ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለዓመታት ሕዝቡ ላይ አቆያችሁ? እርስ በርስ ተፈራርታችሁም አይደለም? ሕዝቡ በደንብ ያዉቃል፤፤ ለነገሩ ማን ማንን ያጋልጣል ሁሉም አንድና አንድ ናችሁ፤፤
  ሕዝብ በቀኝ ማለት ሲጀምር ባዶ ጩሃታችሁን ጀመራችሁ፤፤

  Reply
 9. mewael

  ትግራይ ህዝብ ላይ የለመዳቹት የወረራና ዘረፋ አመል ካባችሁ ብልጦቹ አሁን አሁን ውልቅልቁን እያስቀሩት ነው። በትግራይ ላይ የምታደርጉት ዘረፋም እንዲሁ እንደማይቀጥል አትጠራጠር። ከንግዲህ በኋላ አብዝተህ እንዲሁ በተደጋጋሚ ይቅርታን በመለመን ብቻ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵታ ህዝብ ይቅር ይለሃል። የሚቀጥለው የቤት ስራህ በ EFFORT, MELES FOUNDATION, REST, VAT, ልማትና ዘመናዊ መዳበርያ ስም የትግራይ ህዝብ ብዝበዛ ማስተካከል መጣር ነው መሆን ያለበት፡፡ ይህንን ባታደርግ ግዜህን ጠብቀህ ዋጋህን ስለምታገኝ ቅር አይለንም። ያንተና ጓደኞችህ ልጆች በምዕራብ አውረፓ፡ አሜሪካና ቻይና በህዝብ ሀብት አለአግባብ ሲንቆላጳጰሱ የትግራይ ገበሬ ልጆች ግን በኈዱበት ይታረዳሉ፡ ከፎቅ ቁልቁል ይጣላሉ በቤንዚን በእሳት ይጋያሉ። አንተና መሰሎችህ ትንሽ ሳታፍሩ ኢትዮጵያ በ11% ዕድገት ዐስወነጨፍናት እያልክ ልጆቻችን የቻይና ኢንቨስተሮች የቅኝ ባርያ አርገህ ለቻይና ዘብ ስትቆም በሂወታችን ታሾፍብናለህ፡፡
  ሁሉም የዘራውን ያጭዳል። ይህንን ደግሞ ጠብቀህ ታየዋለህ፡፡
  የምን መላመጥ ነው አሁን? በግልፅ ይቅርታ አትጠይቅም? የግዜ ጉዳይ ነው እንጂ በትግራይ ህዝብ ዘንድም አንዳች ወዳጅ የለህም፡ የዋጋህንን ሊሰጥህ ግዜው ይደርሳል እየደረሰም ነው፡፡ በድሮ ጠንካራ ስራህ ተከብረህ ብትቆይም ባሁኑ ጨምላቃ ስራህ ደግሞ ልክህን ታያለህ።
  እሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ባለስልጣናትም አብዛኞቻቸው የት እንደሚያድሩ ስለምናውቅ ለነሱ ምንም ክብር የለንም። ምክንያቱም አንድ ሰው መጠጥ አይጠጣም፡ አያጭስም፡ አይሰክርም፡ ምንም ሱስ የለበትም፡ ጀግና ነው፡ አዋቂ ነው፡ ለህዝብ ተቆርቋሪ ነው፡ አይሰርቅም… ወዘተ የምንለው በድሮው ባህሪው ሳይሆን አሁን ባለበት ሰነምግባርና ባህሪ ተሞርኩዘን ነው።
  እናም የመቶዎች ሺ አደራ ረግጣችሁ በ22ና ካዛንቺስ ማደርያሽ ሁላ እንደድሮ ህዝብ የሚወድሽ እንዳይመስላቹ።

  Reply
 10. Gi Haile

  wow! what a tragedy, did Abay Knows all this coruption and he never take any action againest those corupt people? I belive he is one of the organizer of those coruption, b/c he knows them but he do not say nothing to them b/c one day he will arrest them and take all money and invest it in EFFORT, REST, and will say, this money is belongs to tigray people. ha..ha…ha… Abay you need to Visit Psychatric Doctor I reccomend that b/c you need help. if you do not check Doctor then you are lunatic you will kill your self like Hitlor b/c the blood of OROMO, Afar, Ogaden, Amhara, Wolkait, Gambela inocent people blood cry out for Justice. hell will open its mouth to receive you. bye…bye…

  Reply
 11. dergu temelese

  Daniel have you noticed that when the 40th anniversary of the Tigray Peoples Liberation Front (TPLF) was held in Mekelle, the capital of the Tigray Regional State, the following state leaders were invited to attend the ceremony:
  1/ President Omar Al-Bashir of Sudan,
  2/Paul Kagame of Rwanda
  3/President Hassan Sheikh Mohamud of Somalia,
  4/Prime Minister Kamil Abdelkadir Mohamed of Djibouti,
  5/Prime Minister Ruhakana Rugunda of Uganda,
  6/ Dr. Nkosazana Dlamini-Zuma, Chairperson of the African Union Commission.
  7/ Prime Minister Hailemariam and, senior government officials. Whene the OPDO or ANDM celebrate their establishment no one foreign leader is invited. This is because, TPLF is strengthening its relation for the establishment of the future Tigray Tigrign State.So Daniel, Fitsum and Dawit you have to accomplish your task for the formation of Tigray Tigrign State.

  Reply

ስለጽሑፉ ምን ይላሉ? አስተያየቶን ያካፍሉን፡፡