በሀረሪ በተፈጠረ ሁከት 18 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

ከቀናት በፊት በሀረሪ ክልል በተፈጠረ ሁከት በ18 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በሐረሪ ክልል በተለምዶ ሐኪም ጋራ ተብሎ በሚጠራው አካባበቢ ለልማት ከተከለለ መሬት ጋር በተያያዘ በተነሳ ሁከት በ18 ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በተፈጠረው ሁከትም በአካባቢው የሚገነኝ የመዝናኛ ሎጅ ህንፃ፣ የንግድ ድርጅት እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች በቃጠሎ መውደሙን ተገልጿል፡፡

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም አብዱማሊክ በበኩላቸው ቦታው የተከለለው የአካባቢውን አርሶ አደር በማወያያት እና መግባባት ላይ ተደርሶ አስፈላጊውን ካሳ መከፈሉን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ዝግጅት ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ሃምዲ ሪድዋን አካባቢው ለግብርና ስራ የማያመች እንደሆነ ከቦታው ለተነሱ አርሶ አደሮች በደምብና መመሪያው መሰረት አስፈላጊውን ካሳ መከፈሉን ጠቁመው ቦታውም ለኢንቨስተር እና በክልሉ ለሚገኙ መምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ እንደተከለለ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ቅሬታ እንዳልቀረበ እና በቀጣይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች ካሉ በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከካሳ ጋር በተያያዘ በክልሉ ቦታቸው በልማት ምክንያት የተነሱ አርሶ አደሮች ካገኙት ካሳ 90 በመቶ እንዲቆጥቡ በማድረግ በኢንቨስትመንት እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

********

Source: Harari region Government Communication Office

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories