የትግራይና የአማራ ሽማግሌዎች ጉባዔ ላይ የተነሱ ነጥቦች

(ይህ ጭማቂ ቅዳሜ ማታ ጉባዔው ባለቀ በሁለት ሰዓት ውስጥ የተጠናቀረና በግል የፌስቡክ ገጼ ያቀረብኩት የነበረ ሲሆን፤ በአንባቢ ጥያቄ መሰረት እዚህ አትመነዋል። ተጨማሪ ሪፖርት በተቻለ ፍጥነት እናቀርባለን።)

በመቐለ አርብና ቅዳሜ በተካሄደው የአማራና ትግራይ ሽማግሌዎች ጉባዔ ላይ የተነሱ ነጥቦች:-

* ከአማራ ክልል ሽማግሌዎች ወገን “የማንነት ጥያቄ” አለመመለሱ ለግጭት ምክንያት ሆኗል የሚል ተደጋግሞ የተነሳ ሲሆን፤ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ቢሰጠው ጥሩ ነው ብለዋል።

* ዛሬ አባይ ወልዱ በሰጡት ምላሽ:- የማንነት ጥያቄ እየተባለ የሚጠቀሰው ወልቃይትን ከሆነ የማንነት ጥያቄ የለም። ጥያቄው ከመጣም ጥያቄውን የማስተናገድ ስልጣን የትግራይ ክልል መንግስት ነው። በኢሕአዴግ ደረጃ የተስማማነውም ይህንኑ ነው ብለዋል።

* ፀገዴ ወረዳ አካባቢ ያለውን የወሰን ጉዳይ ግን ቶሎ ለመጨረስ ቃል ገብተዋል።

* ከሰሜን ጎንደር (ጃን አሞራ?) የመጡ እናት ትላንት በሰጡት አስተያየት:- ልጆቻችን የነገሩን ትግራይ ልዩ ልማት እንዳለ ነበር፤ በአይናችን ያየነው ግን ከኛ አካባቢ የተለየ አይደለም ብለዋል። (ተሳታፊዎቹ በመኪና በምዕራብ ትግራይ በኩል ስለመጡ ግማሽ ትግራይን አይተዋል፤ በየቦታው እየቆሙም ጎብኝተዋል)

* ከጎንደር የመጡ ቄስ የትግራይ ክልል ወጣቱ ስነምግባርና ታታሪ እንዲሆን መስራቱን ታዝቤያለሁ በማለት አማራ ክልልም በዚህ ላይ ትኩረት አድረገው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

* ፕሮፌሰር ፈትየን አባይ በአማራ ክልል በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመስራት በትግራዋይነታቸው የሚደረግባቸው አስተዳደራዊ ገደብ መኖሩን በመግለጽ አቶ ገዱን አስተካክሉልኝ ብለዋቸዋል።

Photo - Amhara and Tigray elders conference, Mekelle, July 21-22, 2017
Photo – Amhara and Tigray elders conference, Mekelle, July 21-22, 2017

* በጎንደር በትግራዮች ላይ የደረሰውን በግልጽ ቋንቋ ያስቀመጡትና የኮነኑት አንድ ከራያ የመጡ እናት እና አቦይ ስብሓት ነጋ ነበሩ።

* አቦይ ስብሓት ነጋ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ የትግራዮች መባረር ብለው በጠንካራ ቋንቋ የኮነኑት ሲሆን፤ ለዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂው ብአዴን ነው ብለዋል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ኢህአዴግ ብአዴን እዚህ ደረጃ እስኪደርስ ዝም ብሎ በማየቱ ተጠያቂ ነው ብለዋል። አቶ ገዱ ከአቦይ ስብሓት በስተግራ ተቀምጠው ነበር።

*አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባደረጉት ንግግር የትግራይ ክልልን ለመስተንግዶው አመስግነው የሚቀጥለውን ጉባዔ በመስከረም በጎንደር ለማስተናገድ ቃል ገብተዋል።

* በጉባዔው መጨረሻ በወጣው የአቋም መግለጫ ላይ ከተካተቱት ነጥቦች መሀል:-

—> በፌዴራል በክልል በወረዳ ደረጃ ለሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት እንቅፋት የሆኑ ነገሮች ተጣርተው እርምጃ ተወስዶ በመስከረም ወር ለሚደረገው ጉባዔ እንዲቀርብ።

—> ሚዲያዎች የግል ፍላጎትን ሳይሆን የህዝብን ፍላጎት እንዲያንጸባርቁ የሚሉ ይገኙበታል።

በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገን ሽማግሌዎች የትግራይና የአማራ ህዝብ የረጅም ዘመን ታሪክና ፍቅር ያለው መሆኑንና ለዚህ ተጻራሪ የሚሆን ነገር ተቀባይነት እንደሌለው – የግል ታሪካቸውን ሁሉ በመጥቀስ – በተደጋጋሚ በአጽንኦት ገልጸዋል።

*********

Daniel Berhane

more recommended stories