ሚ/ር ሬድዋን:- የተጠና የሁከት ድራማ ተሞክሯል – 7 ፖሊሶች ተጎድተዋል

ኢስላሚክ ስቴት ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት በሊቢያ በኢትዮጲያውያንን ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመውን ግድያ ቪድዮ ባለፈው እሁድ ማሰራጨቱን ተከትሎ፤ ድርጊቱን ለማውገዝ ዛሬ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡

ያንን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስተር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከጽ/ቤቱ ያገኘነውን የመግለጫው ጭማቂ ጽሑፍ ከዚህ በታች አትመነዋል፡፡

1) የተሳካ ሰልፍ ተካሂዷል፣

* ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ወጥቷል፣

* በሰላማዊ መንገድ በጋራ ሀዘኑ ዙሪያ፣ በቀጣይ የጋራ ጥረቶች ዙሪያ ያጠነጠነ መልዕክቱን አስተጋብቷል፣

* አንድነቱን በማጉላት ሽብርተኞች ለመፍጠር የፈለጉትን የመከፋፈል ሴራ ሙስሊም ክረስቲያን ሳይል በጋራ ተሰልፎ በመምጣት አክሽፏል፣

* ሽብርተኝነት ሃይማኖታዊ መሰረት እንደሌለው በማንኛውም ሃይማኖት ጀርባ መሸሸሸግ እንደማይገባ አረጋግጧል፣Photo - Federal police officer harmed during the demonstration

* ISIS ማንኛውንም ሃይማኖት እንደማይወክል ፅንፈኝነትና አክራሪነትን እንዲሁም የሽብር ተግባርን ብቻ እንደሚወክል ስለዚህም የጋራ ጠላት መሆኑን በአንድ ድምፅ አስረግጧል፡፡

* የፀረ ሽብርና አክራሪነት ትግሉን ከመንግስት ጎን ቆሞ ለማጧጧፍ ያለውን ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፡፡

* ህገ ወጥ ስደትን በመላ ህዝቡ ተሳትፎ ማስወገድ እንደሚገባ በቁጭት ገልጿል፣

* በሀገራችን ሰርቶ መለወጥ የሚቻልበት ዕድል እየተፈጠረ በመሆኑ ከነክብራችን በሀገራችን ሰርተን እንለወጥ የሚል ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፣

* የሃይማኖት አባቶችንና የመንግስትን መልዕክት በጥሞናና በትእግስት አዳምጦ የቀጣይ ትግል ባለቤትነቱን አረጋግጧል፣

* በመሆኑም መንግስት የከበረ ምስጋና ያቀርባል፣

* ከህዝቡ በተጨማሪም የሀገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከአንዳንዶች በስተቀር የደረሰው አደጋ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣ ኢሰብአዊ ድርጊት መሆኑንና የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀዘን መሆኑን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረትም የበኩላቸወን ድርሻ የሚወጡ መሆኑን በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና በተናጠልም ገልፀዋል፡፡ የኸው በጋራ ጉዳይ ላይ በጋራ የመስራት የሰለጠነ ፖለቲካ የማራመድ ጅምር በሀገራችን እየጎለበተ ለመምጣቱ አንዱ ማሳያ በመሆኑ መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል፣ አድናቆቱንም ይገልፃል፡፡

* የተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት የሀዘናችን ተካፋይ መሆናቸውን በመግለፅ ላሳዩት አጋርነትም መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

* በሌላ በኩል መላው የሀገራችን ህዝቦች በሀዘን ላይ ባሉበት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጋርነታቸውን በገለፁበት፣ የዓለም ማህበረሰብ ሀዘናችንን እየተካፈ ባለበት በአሁኑ ወቅት አደጋው ከተሰማበት ዕለት ጀምሮ በዜጎች ደም እና በሟች ቤተሰቦችና በመላው የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀዘን በመነገድ ሁከትና ሌላ እልቂት ፈጥረው በችግሩ ወስጥ ለመጋለብ ያሰፈሰፉ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲና የሃሳብ ተጋሪ ጥቂት ደጋፊዎቹ በዛሬው ዕለትም የህዝቡን ሀዘን ወደ ፖለቲካ ቀውስ ለመለወጥ በርካታ ጥረት አድርገዋል፡፡ በመቶሺዎች የሚቆጠረውን የአዲስ አበባ ነዋሪ ሰልፈኛ በጩኸት፣ በድንጋይ ውርወራም ሊያናጉት ቢሞክሩም ሳይሰማቸው ተነጥለው ሁከት ለመፍጠር ብዙ ጥረዋል፡፡

* በሁለት ሶስት ስፍራ ተሰባስበው በተጠናና ጊዜ ተወስዶ ልምምድ የተደረገበት የሁከት ድራማ ሞክሯል፡፡ነገር ግን ህዝቡ በፍፁም ሳይበገር ፕሮግራሙን አጠናቋል፡፡

* ከሀገራችን ውጭ ያሉ እንደ ISIS የመሳሰሉት ከሀገራችን ወጥተን ካላገኙን ልናመልጣቸው እንችላለን፣ ከጉያችን ውስጥ ሆኖ ሌላ የሰው እልቂት፣ ሌላ ትርምስ መፍጠር ግን በጭራሽ ቸል የማይባል የጥፋት ተግባር ሆኗል፡፡

* ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ተግባሩ ለመቆጠብ ተቸግሯል፡፡

* በሂደቱም 7 ፖሊሶች የተጎዱ ሲሆን ሁለቱ ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡

* የአዲስ አበባ ህዝብ አብሮነቱን የ ISIS ሰይጣናዊ ተግባር በማውገዙ ብቻ ሳይሆን ለሌላ ሁከት ሲቅበዘበዙ የነበሩትን ጥቂት ቡድኖች አሳፍሮ በሰላም አቋሙን ከመንግስት ጎን ቆሞ በማንፀባረቁም የላቀ አድናቆትና ምስጋና ይገባዋል፡፡

2) እንደ ISIS እና መሰሎቹ እና በሌሎችም ሀገራት በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ህገ ወጥ ስደትን በመመከት መከላከል ይቻላል፣

3) ሀገራችን ወስጥ ያለውንና ከጎረቤት ሀገሮች በእንደ ሻዕቢያ አይነቱ እየሰራን የሚገባወን አክራሪነትና ሽብርተኝነት ግን በየዕለቱ የጀመርነው የፀረ-ሽብር እና አክራሪነት ትግል በተባበረ መንገድና በቀጣይነት ተረባርበን ዳር ማድረስ መቻል ይገባል፣

4) ISIS የተፈለፈለው በውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነትና በቀለም አብዮት ሰላማቸው በደፈረሰ ሀገሮች ውስጥ ነው፡፡ እኛ ሀገር ውስጥም በጅምር ላይ ያለውን ዴሞክራሲያችንን ምርጫን ሽፋን በማድረግ ይሁን በተለያዩ ወቅት በሚፈጠሩ የሁከት ክስተቶች አጠቃላይ ቀውስና ኢ-ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ የመንግስት…..[]

* መንግስትቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ህገወጥ ስደትን ለመግታት መነሳት አለበት፣

* በሀገራችን ሰርቶ መለወጥ ስለሚቻል፣ አየተቻለም ስላለ ህይወትን ለአደጋ አናጋልጥ፣

* በህገ ወጥ ደላሎች የተጀመረው ትግል ስር ነቀል በሆነ መንገድ ይፋፋም፣

* ድህነትን በጀመርነው መንገድ በፍጥነት ድል እንንሳ፣

* በፀረ-ሽብር ትግላችን ሃይሎች ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥል፣ የሰሞነየ የአሜሪካ መንግስት አቋምም ተጨማሪ እገዛ ነው፣ ሌሎች ሃይሎችም ተመሳሳይ አርምጃ ይውሰዱ፣

* ነገ በአዲስ አበባ አስተዳደርም ሆነ የአዲስ አበባ ህዝብ የተጠራ ሰልፍ የለም፣፣

* ዛሬ ሶማሌ፣ ሀረሪ፤ ነገ አዳማ፣ አሶሳና ደሴ ሰልፍ ይካሄዳል፡፡

*********

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories