የነትዕግስቱ አወል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

በአቶ ትእግስቱ አወሉ የሚመራው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን ባለፈው ቅዳሜ በቶፕ ቪው ሆቴል አካሂዷል።

በጠቅላላ ጉባኤው 239 አባላት ተጠርተው 193ቱ ተገኝተዋል። ይህም ከግማሽ በላይ በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዳቸውን በጉባኤው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ትዕግስቱ አወሉ ተናግረዋል።Tigistu Awelu faction - UDJ Andinet party Congress

ሶስት የፓርቲው አባላት ማለትም አቶ ትዕግስቱ አወል፤ አቶ ጋሻው አሰፋና አቶ ደረጄ ሚሊዮን ለፓርቲው ፕሬዝዳንትነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡ ከአዳማ የፓርቲውን ቅርንጫፍ በመወከል የተገኙት አቶ ጋሻው አሰፋ ከውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉ ሲሆን ሁለቱ እጩዎች በሚስጥር በተካሄደ የድምፅ አሰጣጥ ተወዳድረዋል፡፡

አቶ ትዕግስቱ አወል ከተሰጠው ድምፅ 136 ሲያገኙ አቶ ደረጄ ሚሊዮን ደግሞ 48 ድምፅ በማግኘታቸው አቶ ትዕግስቱ ፓርቲውን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ዳግመኛ ተመርጠዋል፡፡

ጠቅላላ ጉባዔው ለኦዲትና ኢንስፔክሽን የቀረቡለትን 10 እጩዎች አወዳድሮ 7 አባላትን መርጧል፡፡ በተመሳሳይ ለብሔራዊ ም/ቤት አባልነት 57 ዕጩዎች ቀርበውለት በ55ቱ ላይ ድምፅ ሰጥቷል፡፡

የጠቅላላ ጉባኤውን እና አጠቃለይ ውሳኔዎቹን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሚያቀርቡም አቶ ትዕግስቱ ተናግረዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉባኤ ላይ ተወካዩን አልላከም፡፡

በሌላ ወገን ያለው የአቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን ደግሞ ምንም አይነት ጠቅላላ ጉባኤ አላካሂድም በሚለው አቋሙ እንደፀና ነው።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለቱ የፓርቲው አመራር ነን የሚሉ ቡድኖች ችግራቸውን በጠቅላላ ጉባኤ ፈተው እንዲመጡ የሰጠው ተጨማሪ የሁለት ሳምንት ጊዜ የፊታችን ማክሰኞ ይጠናቀቃል።

******

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories