የነበላይ ፍቃዱ አንድነት ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ [+video]

(ሔኖክ ሰለሞን)

በእነ አቶ በላይ የሚመራው የአንድነት ፓርቲ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ መበተኑን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉዮች ቢሮ አስታወቀ Protesters at Andinet UDJ Party office

አዲስ አበባ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ የሚመራው አንድነት ለዴሞክራሲና  ለፍትህና ፓርቲ ዛሬ በህገ ወጥ መንገድ ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ መበተኑን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉየዮች ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታወቀ

ፓርቲው ለሰልፉ ከከተማ መስተዳደሩ በህጋዊ መልኩ ፈቃድ ሳያገኝ ነው፣ ሰልፉን ቀበና አከባቢ በሚገኘው ቢሮው ለማድረግ መሞከሩን ነው ቢሮው የገለፀው።

ፖሊስ ህጉን በተከተለ መንገድ ሰልፉን ለማስቆም ቢሞክርም አንዳንድ የፓርቲው አበላት በፖሊስ ላይ  አምባጓሮ ለማስነሳት ሞክረው ነበር ብለዋል የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ፍሬሀይወት አያሌው።

ይሁንና ፖሊስ በትአግስት ሰልፉን ለመበተን መቻሉን ገልፀዋል።

በሰልፉ ለመሳተፍ ከሞከሩት ውስጥ የታሰረ የፓርቲው አባል እንደሌለም አስታውቀዋል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ቡድኑ ሰላማዊ ሰልፉን እንዳያካሂድ የተከለከለው ሰለማዊ ሰልፍ ሲካሄድ መሟላት ያለበትን አስፈላጊ ቅጽ ባለሟሟላቱ መሆኑ ተገልዖ ነበር።

ቅፁ የሚጠይቃቸው በሰልፉ ላይ የሚያዙ መፈክሮችን እና ሰልፉ ከየት ተነስቶ የት እንደሚጠናቀቅ የሚገልፁ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄጃ መስፈርቶችን አንዳላማላም በመግለጫው መጠቀሱ የሚታወስ ነው።

*********

ምንጭ፡- ፋና፣ ጥር 17፣ 2007

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories