የአንድነት አባላት በፓርቲው ላይ የተጋረጠውን አደጋ ሊፈቱ ይገባል – ኢንጀነር ዘለቀ ረዲ

(ዳዊት መስፍን)

የቀድሞው የአንደነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ዋና እና ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቶች የፓርቲው አባላት የቡድን ፓለቲካ የወለደውን የአንድነት መከፋፈል በጋራ ጉባኤ እንዲፈቱት ጥሪ አቀረቡ።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው በሴራ ፓለቲካ ህልውናው አደጋ ውስጥ የወደቀውን ፓርቲ ሊያድኑ የሚችሉት ህጋዊ አባላቱ ናቸው ብለዋል።

አሁን ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው የሚሉት ኢንጅነር ግዛቸው፥ የፓርቲው አባላትም የአንድነትን የቀደመውን ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመፍታት ስልት ተጠቅመው በሰከነ መንፈስ ችግራቸውን በመፍታት የፓርቲውን ህልውና እንዲታደጉት ጠይቀዋል።Photo - Zeleke Redi

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኢንጀነር ዘለቀ ረዲም የፓርቲው አባላት በሁለቱም ጎራ በቆሙት ህገወጥ አመራሮች ላይ ጫና በመፍጠር ወደ ውይይት መድረኩ እንዲያመጧቸው ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የፓርቲው የ2000 እና የ2004 ውስጠ ደንብ ለአንድ ወር ፓርቲው በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቱ ይመራ ይላል።

በወቅቱ ወንበሩ ላይ እንዲቀመጡ ደንቡ ይፈቅድላቸው የነበረው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ ይህ እንዳልሆነ አንስተዋል።

ከአንድነት ፓርቲ የስልጣን ወንበር ጀርባ ያለውን ሹክቻም ፕሬዝዳንቱን አስለቅቆ ቀጠለ ያሉት ኢንጅነር ዘለቀ፥ የእሳቸውም በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንትነት መዝለቅ በደባ ተገዝግዞ እንዳጋደለ ተናግረዋል።

በፓርቲው ውስጥ ያለው ሴራና ሽኩቻ እጅግ ስላሳዘነኝም ስልጣኔን በይፋ ልለቅ ችያለሁ ነው ያሉት ኢንጂነር ዘለቀ።

ኢንጅነር ግዛቸው በፕሬዝዳንትነት ዘመኔ ለፓርቲው ድጋፍ ከውጭ ሀገራት የሚመጣው ገንዘብ በግለሰብ የሂሳብ ቁጥር መሆኑ ቀርቶ በፓርቲው የባንክ ደብተር ይሁን ማለታቸውንም አውስተዋል።

የቀድሞቹ አመራሮች የተጎነጎነው ሴራ ከእኛ አልፎ ፓርቲውን ጠልፎ እንዳይጥለው ስንል ቀዳሚውን እና ተከታዩን የፓርቲውን የስልጣን እርከን ትተን ወጣን የሚሉት ኢንጅነሮቹ፥ የዲያስፖራው ህገወጥ የሆነ አካሄድ አንድነትን አፍርሶታል ይላሉ።

በአንድነት ቤት የተፈጠረው የአመራር ክፍፍል ካለበት ሳይንቀሳቀስ፣ የኢትዮያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

ስለ መስማማት ብሎ ከሰጠው የሁለት ሳምንት ጊዜ አንድኛው ዛሬ ተጠናቋል።

አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ህጋዊ አመራር የማግኘቱ ጉዳይ ፓርቲው እጩዎቹን አስመዝግቦ ወደ ምርጫ መሙ የመመለሱ እውነት፤ በሁለቱ ቡድን አመራሮች ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ የመፍታት ጥበብ እና የቀረውን አንድ ሳምንት በመጠቀም ብልጠት ይወሰናል።

***********

ምንጭ፡- ፋና፣ ጥር 12-2007

     

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories