ያለፈው እንዳይመለስ፣ የተገነባው እንዳይፈርስ – ብዝሃነት!

(እውነቱ ብላታ –  የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ)

የህብረ-ብሔራዊነት ዋነኛ መገለጫ ከሆኑ አበይት ጉዳዮች የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት እና የባህል ብዝሃነት ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ብዝሃነት በህብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት ውስጥ በሂደት የግድ መፈጠር የሚገባው ነው፡፡ ብዝሃነት ልዩነቶችን በሚያስተናገድ ሥርዓት ውስጥ ከህብረ-ብሔራዊ ውበትነት አልፎ የሥርዓቱ ዋልታና ማገር እንዲሁም ምሰሶ ሆኖ በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት ያጠናክራል፡፡

ብዝሃነት በተሻለ ደረጃ ግልጽነትን ስለሚፈጥር ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ጥበትና ትምክህት እንዲሁም የፀረ ሰላም ኃይሎች መደበቂያ ዋሻን ለመናድ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

የዘርፉ ጠቢባን ብዝሃነት ከባድና አድካሚ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሂደት ውስጥ ታልፎ የሚገኝ ወይም የሚደረስ መሆኑን ለማስረዳት ሲሉ ህብረ ብሔራዊነትን እንደ ድፍድፍ ነዳጅ ይመስሉታል፤ ብዝሃነትን ደግሞ እንደ ተጣራ ነዳጅ እና እንደነጠረ ወርቅ ወይም ውድ ማዕድን ይቆጥሩታል፡፡Minister Ewenetu Blata

ብዝሃነትን የሚያስተናግድ የአመለካከት የበላይነት ባልሰፈነበት ወቅትም ቢሆን ህብረ-ብሔራዊነትን በሕግና በመመሪያ ደረጃ መተግበር የሚቻል ሲሆን፣ ብዝሃነት ግን የህብረ-ብሔራዊነትን የአመለካከት ልዕልና ማረጋገጥን ይጠይቃል።

ሀገራችን ለረጅም ዓመታት ወይም ዘመናት ብዝሃነትን ማስፈንና ማክበር ይቅርና በተፈጥሮ ብቻ በውስጧ ያለውን ልዩነት እንኳን ማስተናገድ ተስኗት ቆይቷል፡፡ ህብረ-ብሔራዊት የሆነችው ሀገራችን በውስጧ ያሉትን ልዩነቶች አምና መቀበል ተስኗት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥና የኋልዮሽ ጉዞ ሽምጥ ስትጋልብ ኖራ ለመናድ ጥቂት ሲቀራት ህብረ-ብሔራዊነትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበለችው በሽግግሩ ዘመን ቻርተር ኋላም በ1987 በኢፌዴሪ ሕገመንግሥት ነው፡፡

ሀገራችን ልዩነቶችን አምና ለመቀበል ረጅም ዘመናትና መራራ ትግል ቢጠይቃትም አሁን ከዚያ ሁሉ አስከፊ የጨለማ ዘመን አልፋ ብዝሃነትን በተግባር ለማረጋገጥ ረጅሙን ጉዞ በቁርጠኝነት ጀምራለች፡፡ የብዝሃነት መረጋገጥ እንደ እኛ ባለ ህብረብሔራዊ ሀገር የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ማስፈኛ ወሳኝ መሠረት ስለሆነ በሚገባ አውቀን የበኩላችንን ድርሻ የመወጣት ኃላፊነት አለብን፡፡

በሀገራችን ብዝሃነትን እውን ለማድረግ ከሚሠሩ ሥራዎች የመጀመሪያዎቹ በህብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓቱ ላይ በቂ ግንዛቤ፣ መግባባት እና የአመለካከት የበላይነት በሁሉም ደረጃ ማረጋገጥ ይገኝበታል። በህብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓታችን ውስጥ በተፈጥሮ ያለው ልዩነት በሥራና በሂደት ወደ ብዝሃነት ሲያድግ፤ ህብረ ብሔራዊነታችን በተግባር፤ በሥራ ሲረጋገጥ ሀገራዊ ውበታችንና ኩራታ ችን ይሆናል፡፡

ለብዝሃነት መሠረት በሆነው የፌዴራል ሥር ዓቱ ላይ በቂ ግንዛቤ ሳይኖር የሚሰራ ሥራ ለአንድ የፖለ ቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ግንባታ፣ በተለይም ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ልማት በጎ አስተ ዋፅኦ አይኖረውም፤ ከዚህም ጎን ለጎን የገ ንዘብ፣ የጊዜ፣ የዕውቀ ትና የጉልበት ብክነት ማስከተሉ አይቀርም፡፡ በመሆ ኑም ስለ ብዝሃነት መሠረታዊ መነሻና መድረሻ በአግባቡ መረዳትና ማስረዳት ያሻል::

በመጀመሪያ ደረጃ ብዝሃነት በተፈጥሮ የሚገኝ፣ በዓይነት ወይም በልዩነት ላይ የተመሠረተ የቁጥር ብዙነት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን በልዩነቶቻችን ውስጥ ያለውን አንድነት የውበትና የጥንካሬ ምንጭ ለማድረግና ለማጎልበት በቁርጠኝነት የምንሠራበትና የምናረጋግጥበት የጥምረት እና የጥረት ውጤት የሆነ ህብር ነው፡፡

ብዝሃነት የሚሠራበትና በአብሮነት ሂደት ልናሳካውና ልናጎለብተው የምንችል የመስ ተጋብር ውጤትም ነው፡፡ ብዝሃነት በሃይ ማኖቶችና በተቋሞቻቸው እንዲሁም በብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል ሊኖር የሚገ ባው ግንኙነት በመቻቻል፣ በመከባበርና በመረዳዳት ላይ በተመሠረተ ጠን ካራ ህብረት መል ካም ግንኙነት የሚረጋገጥበት የአብሮነት ውጤት ነው፡፡

ብዝሃነት እንደ ልዩነት በተፈጥሮ ብቻ የሚገኝ ሳይሆን በተጨባጭ እንዲኖርና እንዲረጋገጥ ለማድረግ ሥራን እና ጥረትን የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም አኳኋን ሲገነባ በህብረ ብሔራዊ ሥርዓት ውስጥ ያለው ልዩነት የውበትና የአብሮነት ማሳያና መገለጫ ይሆ ናል፡፡

በሌላም በኩል ብዝሃነት ከመቻቻል ባለፈ ልዩነቶቻችን በፈጠሯቸው እሴቶች እና ለልዩነታችን መኖር ምክንያት በሆኑ ማንነቶ ቻችን ላይ መግባባት እና የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ማለትም ነው፡፡

መቻቻል ለአብሮነት የሚያስፈልግ የጋራ እሴት ቢሆንም ተቻችሎ ለመኖር አንዱ የሌላውን እምነት ምንነት እና ማንነት በጥልቀት ሊያውቅ አይገደድም፡፡ የማንነት እና የሃይማኖት ጥንቅሯ ብዙ በሆነባት ዓለማችን መቻቻል ብቻውን ቁንፅል የሆነ እና በሃይማኖቶች/ በማንነቶች መሀል ሊኖር የሚችለውን ጨለምተኝነትንና ቅድመ-ቅኝት (Ster eotypes) ለማስወገድ በራሱ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡

በተለያዩ ማንነቶችና ሃይማኖቶች መሀል ሊወገድ የሚገባው ጨለምተኝነት እስካለ እና እስካልተወገደ ድረስ ጊዜያትን ቆጥሮም ቢሆን በአሉታዊነቱ ዋጋ የሚያስከፍል ዕዳ ሊሆን ይችላል፡፡ ጨለምተኝነት መወገድ የሚችለውና የሚገባው ባማሩ እና በተዋቡ ቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር በተረጋገጠ ቁርጠኝነት እና የሥራ ውጤት መስዋዕት ነው፡፡

ብዝሃነት በተለያዩ ሁኔታዎች በአጋጣሚ የሚፈጠር አንፃራዊነት (relativism) እና እንደ ሁኔታው የሚለያይ/የሚቀያየር ሳይሆን በማንኛ ውም ሁኔታ እንዲኖር ለማድረግ የግድ ዋጋ ወይም መስዋዕት የሚከፈልለት/ የሚከፈልበትም ነው፡፡ ብዝሃነት ዋጋ የሚከፈ ልለት እንደመሆኑ መጠን በአሁኑ ወቅት ይህንኑ አስመልክቶ ያለው የአቅጣጫ ምልከታና እርምጃ የማንነት መገለጫዎቻ ችንን እንድንተው የሚጠይቅ አይደለም፡፡ ይህ ሲባል ለአብሮነ ታችን ሲባል በሃይማኖቶች /በብሔር /ብሔረሰቦች/ሕዝቦች ወይም ማንነቶች መሀል ያሉ ልዩነቶቻችንን መተው ወይም መካድ ሳያስፈልግ የጋራ በሆኑ ጉዳዮቻችን ላይ ግንኙነቶችን በመፍጠርና በማጠናከር አንድነትንም ጭምር ማረጋገጥ እንችላለን ማለት ነው፡፡

በአጠቃላይ ብዝሃነትን የውይይት፣ ድርድር እንዲሁም የሰጥቶ መቀበል ባህል መጎልበት ውጤት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሰጥቶ መቀበልን መሠረት ያደረገ ድርድርን፣ የጋራ መረዳዳትን እና ግንዛቤ የሚፈልግ ሂደትም (ሥርዓት) ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሚደረግ ውይይት የተሳታፊዎች ሁሉ መስማማት እንዲኖር ሳያስገድድ ለውይይቱና ድርድሩ መሳካት ከመነሻው እስከ መድረሻው ለጉዳዩ ተግባቦት ቅን እና ፅኑ ፍላጐትን ይጠይቃል፤ መልካምና ገንቢ የመወያያ ሃሳቦችንም ያስተናግዳል፡፡

ይህንንም ለማሳካት ሁለት አበይት ጉዳዮችን (ሃሳቦችን) መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በአንደኛ ደረጃ ልዩነታችንን አክብረን በአንድነት ለመኖር የሚጠቅሙን አስተሳሰ ቦችንና ግንኙነቶችን ማዳበር አለብን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ አንዱ ከሌላው ጋር የሚጋራቸው መደበኛ ያልሆኑ መግባቢያዎች ጭምር ህብረ ብሔራዊነትን የሚያከብሩና የሚያንፀባርቁ መሆን ይገባቸዋል፡፡

በጥቅሉ የአንድ ሀገር ሕዝብ የጋራና የተናጠል የማንነት መገለጫ በየአውዱ የብሔሩን፣ ብሔረሰቡን ወይም ሕዝቡን፣ በሌላም በኩል ሃይማኖት ተከታዩን ማህበረሰብ እምነት ወይም እሴት በጠበቀ አኳኋን ግለሰቡንም ይሁን ማህበረሰቡን እንደ ዜጋ ሊገነቡትና ሊያሳድጉት ይገባል፡፡

*******

Ewnetu Bilata Debela is a Special Assistant to the Prime Minister. Previously, he served as State Minister of Government Communication Affairs Office and a senior official at the Ministry of Federal Affairs. Ewenetu studied Chemistry in Bahir dar University, Political Science at Addis Ababa Univercity and Economics at Civil Service University. He occasionally writes on HornAffairs.

more recommended stories