በርከት ያልን የዓረና አመራሮችና አባላት ወደ አንድነት ፓርቲ ተቀላቀልን (አስገደ ገ/ስላሴ)

ከቀደምት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) አባላት አንዱ የነበሩት እና ከዚያም የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዐላዊነት (ዓረና) ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ አባል የነበሩት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ፤ በቅርቡ ከሌሎች የዓረና አባላት ጋር በመሆን ‹‹አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ፓርቲን›› መቀላቀላቸው ተሰምቷል፡፡

ሁኔታውን አስመልክቶ አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ሚከተለውን ጽሑፍ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

እኛ የዓረና ትግራይ አመራሮችና አባላት የነበርን ዓረና ትግራይን ስንመሰርት አንባገነኑ የህወሓት ኢህአደግ ስርዓት በፈጠረው ኢፍትሃዊ ፖሊሲና ፖለተቲካዊ ዝቅጠት በህዝቦች ላይ የፈጠው ሰቆቃ ነባራዊ ሁኔታ ተገንዝበን ለሰፊው ህዝብ ሊጠቅም የሚችል ፖለቲከዊ፣ ኢኮኖምያዊ፣ ማሕበራዊ፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና መስመሮች በመንደፍ በሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መርሆችም ለሃገራችን ህዝቦች ይጠቅማል ብለን በማሰብ እንዲሁም የሃገራችን ሉኦላዊነት በመደፈሩ የሃገራችን የባህር በር በማጠቱ የኢኮኖሚና የፀጥታ ጥገኛ በመሆናችን እነዚህና ሌሎች ችግሮች ለመፍታት ፖለቲካዊ ፕሮግራምና የውስጥ መተዳደርያ ደንብ በመንደፍ ለተግባራዊነቱ ትግላችን በማጧጧፍ እነሆ 6 ዓመታችን ለማስቆጠር ሁለት ወራቶች ብቻ ቀርተውናል::

በነዚህ 6 ዓመታት እንደነ አረጋዊ ገ/ዩሃንስ የተሰውበት ከባድ መስዋእትና በርካታ እልህ አስጨራሽ ሥራዎች ተሰርተዋል በዓረና ዙርያ በሺ የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ሙሁራን ተማሪዎች ነጋዴዎችና ሌሎች ማሕበረሰብ ተሰልፈዋል::Asgede Gebreselassie

ዓረና ትግራይ ክልላዊ ፓርቲ ሆኖ ሲመሰረት እንደዋነኛው የትግል ስትራተጂ ክልላዊ ፓርቲ ወደ የሚፈልገው ግብ ያደርሰናል ብሎ አይደለም:: በኢትዮዽያ የነበረው ነባራዊ ሁኔታ ስላልፈቀደለት እንጂ በሃገር ደረጃ ከነበሩት ሃቀኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርዎች አንድነት በመፍጠር የኢህአደግ የተበላሸ ጠባብና የከፋፍለህ ግዛ ስርዓት በምርጫ በማስወገድ ኢትዮዽያ ዜጎቿ የብሄር፣ የቀለም፣ የሃይማኖት፣ የዘር ወ.ዘ.ተ ልዩነት ሳይኖራቸው ተፋቅረው ተዋህደውና ተማምነው የሚኖሩባት ኢትዮዽያ እንዲሁም ሉኦላዊነቷና ክብሯ የተጠበቀ የቀድሞ ዝናዋ ተመልሶ ድሮ በስልጣኔ ፊት እንደነበረች ሁሉ አሁንም ሁሉም ዓይነት ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባት አስተማማኝ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት አራማጅ እንድትሆን በማመን ነው::

የሰላማዊ ትግል ለተነሳንበ ዓላማ እውንነት መነሻ የሆነ መጀመርያ በሃገር ደረጃ ከነበሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅንጅት (ጥምረ) በመፍጠር በምርጫ 2002 ዓ/ም በቅንጂት ተዋዳድረናል:: ከዚያ በኋላም ወደ ግንባር ደረጃ ተሸጋግረን ወደ ውህደት ለመሸጋገርም ተወስኖ ነበር::

ውህዱቱ ላለመሳካት በሁሉም የግንባር አባል ፓርቲዎች የየራሳቸው አስተዋፅኦ ነበራቸው:: አሁንም ለስኬቱ እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ:: በተለይ የዓረና ፓርቲ ለውህደቱ ምን ያህል እንቅፋት እንደሆነና ሌሎች ግባቸው ሊመቱ ይዙዋቸው የነበረ ዓላማዎች ለመምታት እንቅፋት መሆኑ ቀጣይ የሰላማዊ ትግል ስትራተጂ መንገዱ ማየት ስለተሳነው በነደፈው ፖሊቲካዊ ፕሮግራም መተዳደርያ ደንብና ፖሊሲው ለማራመድ ባለመቻሉ ነው:: መጀመርያ የነበረው እድገት ወደ ኋላ በመመለሱ ዋና የፓርቲው ምሰሶ የሆነ ነፃነትና በውስጡ ዲሞክራሲ አሰራሩ ከህወሓት የማይተናነስ ዓፋኝ በመሆኑ:: የፋይናንስ ስርዓቱ በጣም የተበላሸና ለሙስና የተጋለጠ በመሆኑ:: በሕገ ደንቡ መሰረት ስልጣን የተሰጣቸው አመራሮች የተገለሉና የጥቂት አባታውያን ፈላጭ ቆራጭነት የነገሰበት በመሆኑ:: የአዲሱ ወጣት አሳታፊነት አለመኖሩ በአጠቃላይ የፓርቲው መሰረት የሚንድ አሰራር በፓርቲው በመስፋፋቱ:: አመራሮቹና ተራ አባላቱ ከፓርቲው እያገለሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነና እየተራቆተ በመምጣቱ ሁኔታው አሳስቦን ውስጣችን ግልፅነት ባለው መንገድ እንፈትሽ እንገምግም ማለታችን እንደወንጀል ተቆጥሮብን ከፓርቲው ተባርረናል::

በዓረና መሰረታዊ የዓላማ መርሆዎች በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሚገኙ ቡድን ልዩነት መፈጠሩ:: በመጨረሻም የህወሓት ተላላኪ ባንዳዎች በፓርቲው ከተራ አባል እስከ አመራር ተሰግስገው በፓርቲው መበታን በመፍጠራቸው:: እነዚህ ቀና ታጋዮች ደግሞ ለሚታዩ ችግሮችና ድክመቶች ጠንክረው በመታገል ፓርቲውን አጠናክረው ወደ ቀና ጎዳና መውሰድ ቢኖራቸወም ከተሞክሮ ማነስና ተስፋ በመቁረጥ ብዙ ታማኝና ጠንካራ አመራሮችና አባላት ከፓርቲው ራሳቸው አገለሉ:: የነዚህ የሰላም ትግል አራማጅ ታጋዮች ማግለል ለነዛ ባንዳዎች እጅጉን አስደስቶቸዋል ተልእኮዋቸው ተሳክቶላቸዋል::

በዓረና ውስጥ ግን የመስመር ትግል አልቆመም:: በፓርቲው በሃገራዊ ውህደት በሚመለከት ከህወሓት ጠባብ አስተሳሰብ የሚመሳሰል አቋም በማራመደ ከአማራ ስብስብ በተለይ ከአንድነት ውህደት የሚባል አይታሰብም ከፈለግን ራሳችን ሃገራዊ አውራ ፓርቲ እንሆናለን በማለት ለአባላት ስልጠና እስክ መስጠት ደረሱ:: በፓርቲው ውስጥ ባለው እንባገነናዊ አስተሳሰብና አሰራር ምክኒያት የፓርቲው አመራሮች ሕገ ደንቡ በመጣሳቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት መስራት ሲገባቸው ከሁሉም ነገር መገለላቸው በተለይ በህዝብ ግንኝነት፣ በድርጅት ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ለተመደቡ የሥራ አስፈፃሚና ማ/ኮሚቴ አባላት ስልጣናቸው ነጥቆ በግለ ሰዎች ግልፅነት በሌለው መንገድ እየተሰራ በውጭ ዲፕሎማሲ ከነባር ፖለቲከኞች ውጪ ወጣት ፖለቲከኞች እንዳይሳተፉ ማድረግ:: በፕሮግራማችንና ፖሊሲያችን የተቀመጡ ዓላማዎች ጠነከረው እንደመታገል የህወሓት ባለስልጣናት ላለማስቀየም ተብሎ መለሳለስ:: አብዛኛው ሥራ አስፈፃሚ ወደ ህዝብ ወርዶ ተንቀሳቅሶ የህዝብ ሰላማዊ ማዕበል ፈጥሮ መታገል ሲገባው አዲስ አበባና መቀሌ ተወሽቆ በዓመት አንድ ጊዜ የማ/ኮሚቴ ስብሰባ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ መወሸቅ:: በፓርቲው አባላት ላይ ለሚደርሰው እስራት፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ግድያና ግርፋት በሕግ መከሰስና መከራከር ሲገባው ከህወሓት ላለመጋጨት ሲል እኛ ተሟጋች ፓርቲ መሆን አንፈልግም በማለት በአባላት ላይ የሚደርሰው ስቃይ ዝም ብሎ ማለፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአባላትን ሞራል እየጎዳና ተስፋ ማጣት እየተበራከተ መምጣቱ:: ስጋት ይፈጥራሉ ተብለው በሚገመቱ የከተማና የገጠር እንቅስቃሴዎች ወደ ኋላ ማፈግፈግ እንዲሁም አለመሳተፍ ይታዩ ነበር:: በተለያዩ ሚድያዎች ማለት በማሕበራዊ ድህረ ገፆች መፅሄቶና ጋዜጦች:: በሃገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የተለያዩ ሚድያዎች ገዢው ፓርቲ የሚያጋልጡ አመራሮችና ተራ አባላት እንደወንጀል ተቆጥሮ መከሰስና በፓርቲው ዋነኛ መስፈርት የሆነው የግለሰውና የቡድን መብት ጭራሹን በመጥፋቱና ሌሎች ችግሮች በመኖራቸው ፓርቲው አደገኛ ለመበተን አደጋ አጋልጦታል::

ጠቀለል ባለ መልኩ የልዩነታችን ዋና ዋን ነጠቦች፦

1. አሳታፊ የሆነ ድርጅታዊ አሰራር ቀርቶ በድርጅቱ አንባገነናዊ ፀረ ዲሞክራሲ አሰራር ስላለ:: ለማስተካከል ግልፅነት ባለው መድረክ እንገመግም በማለተታችን

2. በፓርቲያችን ያስቀመጥነው መተዳደርያ ደንብ በመጣስ የአባላት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ በመታፈኑ የአመራርና እስከ ተራ አባል በሺ የሚቆጠሩ ፓርቲው ለቀዋል:: የዚህ ጠንቅ ምክኒያ በሥራ አስፈፃሚ አባላት የተፈፀሙት ስህተት ስለሆነ ንገምግመው

3. በፓርቲው አመራር ጉባኤው በሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት በተመደቡበት የሥራ መስክ እንዲሰሩ አለመደረጉ ሁሉም ነገር በጥቂ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ፈላጭ ቆራጭነት እየተሰራ ነው:: በመሆኑ ማ/ኮሚቴ ስብሰባ እናድርግ እንገምግም ውስጣችን ይፈተሽ በማለተታችን

4. በዓረና ፕሮግራም የተቀመጠው የውህደት አቋማችን በመጣስ ዓረና ትግራይ ሌሎች የትምክህትና ጠባብ ኃይሎች ለውህደት እንቢ ቢሉም ዓረና የኢትዮዽያ አውራ ፓርቲ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል:: እና ለዚህ የህወሓት ለጋሲ የሆነ ጠባብ አመለካከትና አቋም ቃውመናል

5. በዓረና ፓርቲ ግልፅነትና ተጠያቂነት በሚመለከት በፖለቲካ፣ በአደረጃጀት፣ በፋይናንስ፣ በዲፕሎማሲ ሥራዎች ይቅርና ለብዙሃኑ ለማ/ኮሚቴና ለአብዛኛው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ድብቅ መሆኑ ሁሉም ሥራ በሊቀመንበሩና በጥቂት የሥራ አስፈፃሚ አባላት ሥራው መፈፀሙ በመቃወማችን

6. በፓርቲያችን አመራር በተለይ በሥራ አስፈፃሚ ውስጥ አንባገነንትና አባታዊነት ተስፋፍተዋልና ይስተካከል በማለታችን

7. በፓርቲው ኋላቀር ቡድናውነትና ከፋፋይነት ነግሶዋል:: ይህ አደገኛ ባህል እናስወግደው የሚል እምነት ስላለን

8. በፓርቲያችን ውስጥ የግጭት አፈታት ዲሞክራሲያዊ ባህል ባለመኖሩ ብዙ አመራርና አባላት ዓረና ለቀዋል ሞራላቸው ተነክተዋል:: ስለሆነም ግጭቱን በመፍታት እናስተካክለው ብንል ተቀባይነት በማጣታችን

9. ዋና ዓላማችን የዲሞክራሲያውነታችን መስፈርት የሆነው የግለሰው መብት ማስከበር ቅድሚያ ማየት ስለተጣሰ ይህም አንፈትሸው ብንለም ሰሚ ጀሮ አላገኘንም

10. በአባላቻችንና ደጋፊዎቻችን በአንባገነኑ ገዢው ፓርቲ ብዙ የመንገላታት፣ የመታሰር፣ የመገረፍ፣ የመግደል ወንጀል ሲፈፀምባቸው እንክሰስ ጠበቃ እናደርግ የሰላማዊ ትግል ስልት አንዱ መንገድ ፊት እናገኝ የሚደርስብን ግፍና ግድያ ለህዝብ ለሕግ አካላት እንዲሁም በሃገር ውስጥና በውጭ ላሉ የሰብአዊ መብት ተጣባቂዎች እናሳውቅ እሪታችን እናሰማ ለጠበቃ የሚሆን ገንዘብ ብናጣም ውክልና ስጡን እንማጎት ለሚል ጨለምተኛ መልስ በመስጠት ስለዘጉት ይህም በግልፅ እንወያይበት በማለታችን ሊያድምጡን ባለመፈለጋቸው

11. የሰላማዊ ትግል አቅጣጫ በመሳት ወደ ህዝብ ወርደን ህዝባዊ ማዕበል እንፍጠር ለሚል ሃሳብ ዘጊ መልስ በመስጠት ከአዲስ አበባና ከመቀሌ ውጭ ለመንቀሳቀስ ፍቃደኛ አለመሆን ዘንድሮ ባደረግናቸው እንቅስቃሴዎች ወደ ፊት ሂደን ስንቀሰቅስ ጥቂት የሥራ አስፈፃሚ ካልሆኑ ሌሎች የሰጋት (ፍርሃት) ዝንባሌ ማሳየታቸው

12. የፓርቲ ተራ አባልና ጥቂት የሥራ አስፈፃሚ አባላት በግል ሚድያዎች በድህረ ገፆችና ዌቭ ሳይቶች ሲፅፉና ሊናገሩ መከልከላቸው በመቀዋማችን

13. ወደ ህዝብ የሚሰራጩ ፅሑፎች ሊሳኖች ለገዢው ፓርቲ ማንነት የማያጋልጡና የተለሳለሱ አድር ባዮች ናቸው ብለን ተቃውመን መሻሻል ስለአልታየ

14. በመሬት ባለቤትነትና በፈደራሊዝም ግልፅ አቋም አንወሰድ በማለታችን

ላይ የተዘረዘሩ የዓረና ችግሮች ለመፍታት መጀመርያ እንገምግም ብለን በተደጋጋሚ ጠይቀን መልስ ስናጣ በፓርቲው ሕገ ደንብ መሰረት አስቸኳይ ጉባኤ በመጥራት ስር ነቀል የሆነ ማስተካከያ እንድናደርግ ከ5 እስከ7 ጊዜ በፅሑፍ ጠይቀን ለጥያቄያችን መልስ በመስጠት ፈንታ፦

1. አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ከዚያ በፊት ባልነበረ መሰረታዊ ድርጅት በሌለበት ሳይጠየቁ ሳያነጋግሩዋቸው በዝግ ስብሰባ እንዲባረሩ ተወሰነባቸው

2. መ/ር ገብሩ ሳሙኤል የቁ/ኮሚሸን አባል የሆኑ እሳቸው በሌሉበት ራሳቸው ቁጥጥር ኮሚሸን አያሉ ከስብሰባው በማግለለ ሳያነጋግሩዋቸው ሳይጠየቁዋቸው ምልአተ ጉባኤ ባልተሟላበት ስብሰባ ለ2 ዓመት እግድ ተወሰነባቸው

3. መ/ር ታደሰ ቢተውልኝ የማ/ኮሚቴ አባል በፓርቲው ውስጥ ከፍተኛ ችግር አለ እንገምግመው ብለው ለፓርተቲው ፅ/ቤት በፅሑፍ በመጠየቃቸው እንደወንጀል ተቆጥሮባቸው ምልአተ ጉባኤ ባልሞላበት ስብሰባ ለአንድ ማ/ኮሚቴ አባል ማስጠንቀቅያ ለመስጠት 16 ድምፅ ሲያስፈልገው በ12 ድምፅ ማስጠንቀቅያ እንዲሰጥ በመደረጉ

4. አቶ ሺሻይ አዘናው የማ/ኮሚቴ አባል የሆኑ በተደጋጋሚ ለጠየቁትን ጥያቄ መልስ ሲያጣ ለአባላቱና ደጋፊዎች ብለው በሚድያ ፅሑፍ መፃፍ ወንጀል ተቆጥሮ ልክ እንደ መ/ር ታደሰ ቢተውልኝ በ12 ድምፅ በ14 ቀናት በሚድያ ማስተባበያ ካልሰጡ ይባረራሉ ተብሎ ሕጋዊ ባልሆነ ውሳኔ በመወሰን ፓርቲው ዓይኑ ያፈጠጠ አንባገነናዊ የሆነ አሰራር እንደሚከተል አሳይተዋል:: በዚህ ሳይበቃ የዓረና ሊቀመንበር በኢትዮ ምህዳር በአዲስ አድማስ በነገረ ኢትዮዽያ ጋዜጦችና በሎሚ መፅሄት በተለያዩ ዌቭ ሳይቶች ማሕበራዊ ድህረ ገፆች ስማችን ሲያጠፉ ሰንብተዋል:: ለአባላት በስልጠና ሽፋን የኛ ጉዳይ አንስተው ሲያጠፉ ሙሉ ተቃውሞ አጋጠመቸው:: እጅጉን የሚገርመው አቶ ገብሩ አስራት ከአመሪካ መቀሌ ድረስ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ መጥተው የነዚህ ባንዳዎች ውሳኔ አፅድቀው መሄዳቸው:: በጣም ከማሳዘኑ በላይ እነዚህ ሰዎች ወደ የህወሓ ቤት በበር ወየሰ በጓዳ እየገቡ ናቸው? የሚያሰኝ ነገር ሆኖ አግኝተነዋል

እንግዲህ የዓረና ባንዳዎች በእንደዚህ ሁኔታ ቢያባርሩን በዚህ ሕገ ወጥ ድረጊት ሳንደናገጥ ቃል የገባንበት ግቡን ለመምታት መታገል ስላለብን ከዓረና ፖለቲካዊ ፕሮግራምና ሕገ ደንብ ተመሳሳይ ካላቸው ፓርተቲዎች በመቀላቀል ትግላችን ለመቀጠል ወስነናል:: በዚህ መሰረት ከዓረና ፕሮግራምና ሕገ ደንብ ምንም ልዩነት ከሌለው አንድነት ለፈህና ዲሞክራሲ ፓርቲ ከ 17/01/2007 ጀምሮ ተቀላቅለን ለመታገል ወስነናል::

ከወሰኑት መካከል ጥቂቶቹ፦

1. መምህር ታደሰ ቢውልኝ የዓረና ማ/ኮሚቴ ነበር

2. መምህር ገብሩ ሳሙኤል የዓረና ተቁ/ኮሚሸን ነበር

3. ኦቶ ሺሻይ አዘናው የዓረና ማ/ኮሚቴ አባል ነበር

4. አቶ አስገደ ገ/ስላሴ የዓረና ሥራ አስፈፃሚ አባል የነበሩ ከ3ኛ ጉባኤ በኋላ ተራ አባል

5. ኢንጂነር ዓብደልወሃብ ቡሽራ ማ/ኮሚቴ የነበሩ ከ3ኛ ጉባኤ በኋላ ተራ አባል

6. ወ/ሮ ዘቢብ ተሰማ ማ/ኮሚቴ የነበረሩ ከ3ኛ ጉባኤ በኋላ ተራ አባል

7. አቶ ሰለመሞን አበባይና ሌሎች አባላና በየደረጃው ያሉ አመራሮች

ማሳሰብያ

የተከበራቹሁ ከሁሉም ነገር ንፁሃን የሆናቹሁ አባላና ደጋፊዎች እኛ ሕገ ደንቡን የጣሰ እጅጉን በሚያሳዝን ሁኔታ ከዓረና ፓርቲ ስንባረር እናንተም በጣም አንዳዘናቹሁ ከዛም አልፎ የኛ ጥያቄ የእናንተ ጥያቄ አድርጋቹሁ እየታገላቹሁ እንደሆናቹሁ እየሰማንና እያየን ነው:: በዚሁ አቋማቹሁ በጣም ኮርተናል:: እንዲህ ነው የበሳል ፖለቲከኛ ምልክት:: እነዚህ አንባገነን አመራሮች ሶስት ስላሴዎች ለሶስት ዓመት ስንከራከርበት ስንታገለበት የነበረው ጥያቄችን የተሻለ የመፍትሄ ሃሳብ ያመጣሉ ብለን ስንጠባበቅ እጅጉን በሚያሳዝንና በህወሓት በነበሩበት ጊዜ ይፈፅሙት የነበረ ወንጀልና ኡኩይ ባህረ ጎልቶ የወጣበት ይደብቁት የነበሩ ማንነታቸው ያጋለጠበት አጋጣሚ ሁኔታ ነበር:: ከምንወደውና ወንድማችን አቶ አረጋዊ ገ/ዩሃንስ የከፈልንበት ለ6 ዓማታት በጣም ብዙ የዓረና አባላት የታሰሩበት የተገረፉበት አሁንም እነ አቶ አብረሃ ደስታና ብዙ አሰሶ አደሮችና ሙሁራኖች በአሸባሪነት ስም ታስረው እየተሰቃዩበት ራሳችንና ዘርማንዘራችን የተሰቃየበት ፓርቲ የህወሓት ባንዳዎች ሲያባርሩን አቶ ገብሩ አስራትና ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ የባንዳዎች ውሳኔ አፅድቀው ተመለሱ:: ነገር ግን የአንድነት ዓላማ ከዓረና ዓላማ ምንም ልዩነት ስለሌለው ቃል የገባንበት ዓላማ ከግቡ ለማድረስ አንድነት በመሆን ትግላችን እንቀጥላለን:: ከእናንተ ቅንና እውነተኛ ታጋዮችም በዛው ቀናና እውነተኛ የትግል መንገድ እንገናኛለን:: እነዚህ ባንዳዎችም ነገ በይፋ ወደ አለቃዎቻቸው ይቀላቀላሉ::

በሌላ በኩልም እኛ ያነሳነው ዲሞክራሲያዊና መሰረታዊ ጥያቄዎች ብናቀርብ ባንዳዎችና አጃቢዎቻቸው እንደወንጀል የቆጠሩት የራሳቹሁ ጥያቄ አድርጋቹሁ ታነሱ ዘንድ አደራ እያልን እኛም በሃሳብም በመንፈስም ከእናንተ ጋር ነን::

የተከበራቹሁ በሃገር ወሰጥና በውጭ የምትኖሩ የዓረና ድጋፊ ኮሚቴ አባላት በዓረና ሊቀመንበርና አጃቢዎቻቸው እንዲሁም አቶ ገብሩ አስራት በወጨ ሃገረ በተሌ ኮንፈረነስ እያስተጋቡት ያሉትን አሉቧልታና ስም ማጥፋት በትክክል መዝናቹሁ ጥያቄዎቻችን በማየትና እውነታውን በማጣራት የራሳቹሁ ሚዛን በማስቀመጥ ለእውነት ብትቆሙ የተሻለ ነው:: አንዳንድ በውጭ የምትገኙ የዓረና ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አመራር በተለይ በአመሪካ የምትገኙ ብዙሃን በሁለት ወይም በሶስት ሰዎች የአቶ ገብሩ አስራት ድጋፍ ተጨምሮበት የአንድ ወገን ዲስኩር ሰምታቹሁ በአንድ እጃቹሁ እያንጨበጨባቹሁ ራሳቹሁ ትዝብት ላይ ከምትከቱ ባለው ቴክኖሎጂ ተጠቅማቹሁ ሁኔታውን አጣርታቹሁ እኛም ጠይቃቹሁ እውነታውን አወቃቹሁ አቋም ብትወስዱ የተሻለ ይሆናል:: ይህ አባባል ግን ለሁሉ ዲያስፖራ የሚመለከት አይደለም ሁኔታው የሚያባብሱት ያሉ ከሶስት ሰዎች አይበለጡም::

የተከበራቹሁ የኢትዮዽያ ወጣቶች፣ አርሶ አደሮች፣ ሙሁራንና ተማሪዎች መላው ማሕበረሰብ በውጭ ሃገር ያላቹሁም ጭምር እነዚህ ባንዳዎች የህወሓት ሊጋሲ በመከተል እንደለመዱት ከጠባብ አተሰሳሰብ ባህሪያቸው ተነስተው እነዚህ ሰዎች ትግራይን ለማጥፋት ከተሰባሰቡ የጥፋት ኃይሎች ከሆኑ የአማራ ፓርቲዎች ተቀላቅለዋል አያሉ ስማችን እንደሚያጠፉን ከአሁኑ ፍንጭ እየሰጡን ናቸው:: ይህ ባህሬያቸው የአለቆቻቸው ህወሓቶች የከፋፍለህ ግዛ የሚል ኋላቀር አስተሳሰብ የመነጨ ባህሬያቸው በመሆኑ እናውቃለን:: አኛ ግን ከወንድሞቻችን አማራው፣ ኦሮሞው፣ ደቡብ፣ ጋንቤላው፣ አፋር፣ ሶማል፣ በኒሻንጎል፣ ጉራጌው፣ ሓረር በአጠቃላይ ከመላው የኢትዮዽያ ህዝቦች ሁነን ለፍትህ ለነፃነት ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የሕግ የበላይነት ሉእላዊነት ሃገር ለመጠበቅ የተከበረች ኢትዮዽያ ለመገንባት አሁንም እንደትናቱ ቆርጠን ለመታገል ቃል እንገባለን:: ድል ለኢትዮዽያ ህዝብ!!::

********

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories