ፕ/ት ሙላቱ:- አንዳርጋቸው ‹ይቅርታ› ከጠየቀ በሕገ-መንግስቱ መሰረት ይስተናገዳል

president mulatu teshome 1ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ዛሬ ጳጉሜ 5፣ 2006 በብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመላው የኢትዮጽያ ብሔር/ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልእክት አዲሱ አመት የጤና፤ የደስታና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አዲሱ አመት የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማብቂያና የሁለተኛው ዘመን እቅድ ለመጀመር ከፍተኛ ዝግጅት የሚደረግበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ያሉ ሲሆን ሃገሪቱ በሁሉም ዘርፍ የደረሰችበትን የለውጥ ጎዳና ለማስቀጠልና የተገኘውን ውጤት አጎልብቶ ወደ ሌላኛው ምዕራፍ የምንሸጋገርበት፣ እየተመዘገቡ ያሉ የልማት የሰላምና የዴሞክራሲ ውጥኖች የሚሳኩበት፣ የዜጎች የኑሮ ደረጃ አሁን ካለበት በተሻለ አኳኋን ከፍ የሚልበት፣ ዜጎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ የሚያረጋግጡበት እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል፡፡

አዲስ አመትን ስናከብር በአዳዲስ ራእይና በአዲስ መንፈስ የምንነሳሳበት እንደመሆኑ በአዲስ የሃገር ፍቅርና መንፈስ በመነሳሳት ሃገሪቱ እያስመዘገበች ያለውን ለውጥ ይበልጥ ለማሳካት የመንሰራበት እና ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን ሁላችንም ለአንድ አላማ የምንቆምበት ይሆናል ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ አክለውም በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለ995 የፌደራል የህግ ታራሚዎች በምህረት እንዲፈቱ ይቅርታ ማድረጋቸውን ገልፀው፤ ታራሚዎችም ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ማህበረሰቡንና ሃገራቸውን በልማት በመደገፍ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በሃገር የደህንነት ሃይሎች የተያዘው የግንቦት 7 የሽብር ቡድን መሪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ “የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባቱን” በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ: ስለተባለው ጉዳይ እስከ አሁን የሰሙት ነገር እንደሌለ ጠቅሰው በጥያቄው እንደተባለው የይቅርታ ደብዳቤ ገብቶ ከሆነ በሕገ መንግስቱ በተቀመጠው አሰራር መሰረት ከይቅርታ ቦርዱ ሲላክ ይስተናገዳል ብለዋል፡፡

********

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

more recommended stories