የዲሞክራሲ አመለካከታችን ሲቃኝ – የገባው፣ ያልገባው፣ ግራየገባው እና ግራ የሚያጋባው

(Tazabi)

የሀገራችን ከድህነት መውጣት ፣በእድገት ጎዳና ውስጥ ገብታ የብዙ ዜጎችዎን ጥያቄ እና ፍላጎትን ማሟላት የሁሉምኢትዮጵያዊ የዘመናት ሃሳብ እና ናፍቆት ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ታዲያ የዚህ ምኞት እና ናፍቆት ማሟያአንዱ መንገድ እና መሣሪያ ነው፡፡ እዚህ ጋር መስተዋል የሚገባው የዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ በራሱ አንድ ሀገራዊየእድገት ግብ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ የዲሞክራሲ ሥርዐት ማለትም በዜጎች መካከል ያለ እኩልነት፣ በሀገር ያለ የመልካምአስተዳደር ሥርዐት እና የህግ የበላይነት ሀገራዊ እድገትን ለማምጣት ትልቅ መሣሪያ ነው፡፡

አሁን ሀገራችን ያለችበትን ጎዳና መርምረን ሀገራችን በዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ላይ ነች ብንል ከዕውነታ የራቅንአንሆንም፡፡ የዜጎች እኩልነትን፣ የመልካም አስተዳደር ሥርዐትን እና የህግ የበላይነትን ለማስፈን በጉዞ ላይ ነን ፡፡ ይህ ማለትፍፁም የሆነ የዲሞክራሲያዊ ሥርዐት በሀገራችን አለ ማለት አይደለም፡፡ ብዙዎች የላስተዋሉት ዕውነታ ይህ ነው፡፡ ሂደትፈፅምናን ወይም ማለቅን አያመላክትም ፡፡ ወደ ፍፅምና ያለ ጉዞን እንጂ ፡፡ በእርግጥም ደግሞ የዲሞክራሲያዊ ሥርዐትግንባታ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ሁሌም ቀጣይ ሂደት እንደሆነ በዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ለዘመናት ከቆዩ ሀገሮች እንማራለን፡፡

እንግዲህ በዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ውስጥ ታዲያ ሀገራዊ የሆነውን ዲሞክራሲያዊ አመለካከት መፈተሽ እና ማጤንበስርዐቱ ግንባታ ሂደት ውስጥ በቀጣይ ሊተኮርበት የሚገባን አቅጣጫን ያመለካከታል፡፡ ለምሳሌ በሀገራችን ስለሴቶችእኩልነት ያለውን አመለካከት በህፃናት፣ በወጣቱ ፣ በጎልማሳው፣ በአዛውንቱ፣በተማረው ሃይል እና በፖለቲከኞች እንዴትነው ብሎ መፈተሽ በቀጣይ በሀገሪቱ ውስጥ የሴቶች እኩንልነትን ለማስፈን ሊደረጉ እና ሊሠሩ የሚገባቸውን ነገሮችያመላክታል፡፡

በእርግጥ የአንድ ሀገር የዲሞክራሲያዊ አመለካከት ፍተሻ ትልቅ ሳይንሳዊ ጥናት ነው፡፡ ለእያንዳንዱ የዲሞክራሲያዊሥርዐት ግንባታ ጥያቄ ትክክለኛ የአመለካከት መስፈርት እና መለኪያ በማስቀመጥ ሰፊ የህብረተሰብ ክፍልን በመዳሰስየሚሠራ ሥራ ነው፡፡ ይሄንን የሳይንሳዊ ጥናት አቅጣጫ ለተመራማሪዎቻችን ጠቁመን እንለፍ እና እንደው በደፈናው እናበግርድፉ ሀገራዊ ዲሞክራሲያዊ አመለካከቶቻችን እንፈተሽ፡፡

ለፍተሻእንዲመቸን ህብረተሰባችንን ፖለቲከኞች ፣የተማረው ሀይል እና ሰሠፊው ህዝብ ብለን እንከፋፍለው፡፡“ፖለቲከኞች” ስንል በገዠው ፓርቲ፣ በተቃዋሚ ፓርቲ፣ በመብት ተሟጋቾች እና እንዲሁ ራሳቸውን ከፖለቲካ ጋርእያዛመዱ የሚያቀርቡ ሰዎችን (ምሁራንን፣አርቲስቶችን፣ ፀሐፊዎችን ..ወዘተ) ያጠቃልል፡፡ “የተማረው ሃይል” ስንል ደግሞበትምህርት ፣ በልማት፣ በሀገር አስተዳደር እና በመሳሰሉት ተቋማት ውስጥ በትምህርት ባገኙት ዕውቀት ለሀገር ልማትየሚሠሩትን ያጠቃል፡፡ “ሠፊው ህዝብ” እንግዲህ የተቀረውን የህብረተሰብ ክፍል ማለትም ህፃናትን፣ ወጣቶቸን፣ ሴቶቸን ፣ወንዶችን፣አረጋውያንን ያካትት፡፡

እንግዲህ ሀገራችን በዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ሂደት ውስጥ የመጀመሪያው ደረጃ ላይ ስላለች አብዛኛው የዲሞክራሲሥርዐት አመለካከቶቻችን ከ “ፖለቲከኞች” ካልነው የህብረተሰብ ክፍል ይመነጫል፡፡ከዚህ ክፍል የሚመነጨው አመለካከትደግሞ ወደ “ተማረው ሃይል ” እና “ሠፊው ህዝብ” ይዛመዳል፡፡ ይህ ከ“ፖለቲከኞቻችን” የሚመነጨው አስተሳሰብ ታዲያጤናማ የዲሞክራሲ ሥርዐት አመለካከት ከሆነ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው አመለካከት ጤናማ ይሆናል የዲሞክራሲሥርዐት ግንባታውም ፈጣን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከ“ፖለቲከኞቻችን” የሚመነጨው አስተሳሰብ ጤናማ ካልሆነ የዲሞክራሲ ሥርዐት ግንባታው ይጓተታል፡፡ እንዲሁም የሀገር ልማታችን ይጓተታል፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ በሀገራቸን ያለውንየዲሞክራሲያዊ ሥርዐት አመለካከትን ለመፈተሽ የ “ፖለቲከኞች”ን አመለካከት ማጤን አመላካች የሆነን ውጤት ይሠጠናልማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ የ “ፖለቲከኞችን” አመለካከት በምን መለኪያ እንፈተሸው?

አንድ ሰሞን “ የአራዳ ልጆች ” የሰዎችን ሁኔታ ለመተንተን ይህን አባባል ይጠቀሙ ነበር፡፡ “የገባው” ፣ “ያልገባው” ፣“ግራየገባው” እና “ ግራ የሚያጋባው” ፡፡ እኛም ይህንን “ የአራዳ ልጆች ” አባባል ለተነሳንበት የ “ፖለቲከኞች”ን የዲሞክራሲያዊአመለካከት ለመቃኘት እንጠቀምበት፡፡

“የገባው ” በሚለው መስፈርት ውስጥ የሚገቡት “ፖለቲከኞች” የዲሞክራሲ ሥርዐት እሴቶችን፣ አፈፃፀማቸውን፣በህብረተሰቡ ውስጥ የሚያመጡት በጎ እና ገንቢ አስተዋፅኦ በደንብ ፈትሸው እና ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው፡፡ እነኘህሰዎች የዲሞክራሲያዊ ሥርዐት አመለካከቶችን በደንብ ስለተረዱ ለሌሎች ተንተነው ሊያስረዱ ይችላሉ፣ በተግባራቸውምእሴቶቹ እንዲፈፀሙ ያደርጋሉ፡፡

በ“ያልገባው” መስፈርት ውስጥ የሚገቡት ደግሞ የዲሞክራሲ ሥርዐት እሴቶችን በስም ያውቋቸዋል፡፡ እሴቶቹ በህብረተሰቡውስጥ ስላላቸው አስተዋፅኦም ሲባል የሰሙት አለ ፡፡ ነገር ግን አልተረዱትም፣ አፈፃፀማቸውንም አያውቁም፡፡ ስለዚህተግባር ሳይሆን ንግግር ብቻ ነው ያላቸው፡፡

“ግራ የገባው” ውስጥ የሚካተቱት ጥራዝ ነጠቅ የሆነ የዲሞክራሲያዊ እሴቶች ዕውቀት አላቸው፡፡ በዚህ ላይ ስሜት እናአሉባልታ ስለሚጨምሩበት በስም የሚያውቋቸውን እሴቶች በአንደበትም በተግባርም ሲያጎድፉ ይታያሉ፡፡

“ግራ የሚያጋባው” በሚለው ሥር ያሉት ደግሞ ስለዲሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ደንታም የሌላቸው ናቸው ፡፡ ዋናአላማቸው የግል የስልጣን፣ የገንዘብ እና የዝና ጥቅማቸው ነው፡፡ ስለዚህ በዙሪያቸው ያለውን መስለው ይቀርባሉየሚባለውን አስመስለው ያስተጋባሉ፡፡ በጊዜ ሂደት እና ጠለቅ ባለ ፍተሻ ግን ማንነታቸው መታወቁ አይቀርም፡፡

በነዚህ መስፈርት በሀገራችን ያሉ “ፖለቲከኞች”ን መመዘኑን እና መለየቱን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል መተው ይሻላል፡፡ግን እነኘህ የአመለካከት ይዘቶች በሀገራዊ የዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ እና የእድገት ዙሪያ ያላቸውን ድርሻ ማስተዋልግን ያስፈልጋል፡፡

“ያልገባው” ፖለቲከኛ አፈፃፀሙን የማያውቀውን እሴት እየተናገረ ተግባር ላይ የ “ተማረው ሃይል”ን እና“ሠፊው ህዝብ”ን ማማረሩ አይቀርም፡፡ ስለዚህም እድገትን ልማትን ያዳክማል፣ ሀገራዊ ስሜትን ያዝላል፡፡ “ግራ የገባው” ፖለቲከኛ ደግሞ ዕውቀት እያወራ እየመሰለው ራሱን እና ሌላውን ግራ ያጋባል፡፡ የተደናገረ ህብረተሰብን ይፈጥራል፣በህብረተሰቡ ውሰጥ ያለውን ትስስር ያበላሻል፣ ሀገሪቱንም ለከፋ አደጋ ያጋልጣል፡፡ “ ግራ የሚያጋባው” ፖለቲከኛ በግልጥቅሙ ላይ ያተኮረ ስለሆነ የተበላሸ ሥርዐትን ይፈጥራል፣ ሙስናን ያስፋፋል ፣ የሀገር እና የሥራ ፍቅርን ያጠፋል ፣እድገትን ያበላሻል፡፡ ስለዚህ ከ“የገባው” ከተባሉ ት ፖለቲከኞች ብዙ ብዙ ስራ ይጠበቃል ፡፡ በኃላፊነት ሥርዐትን መገንባትእና መጠበቅ፣ በኃላፊነት ህዝቡን ማስተማር እና በኃላፊነት አመለካከትን ለሌላው ማካፈል ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

እንግዲህ በሀገራችን የዲሞክራሲ ሥርዐትን ለመገንባት እና እድገታችንን ቀጣይ ለማድረግ ዲሞክራሲያዊ አመለካከታችንላይ መሥራት ይገባናል፡፡ በዚህ አቅጣጫ በሀገሪቱ በየትኛውም አካል የሚሠሩትን ስራዎችንም መፈተሽ እና ለላቀ ውጤትመቃኘት ይገባናል፡፡ ምክንያቱም የዲሞክራሲ ሥርዐት አመለካከት የፖለቲከኞች ወሬ ብቻ ሳይሆን የአንድ ህብረተሰብአብሮ የመኖር እና ለጋራ ውጤት አብሮ የመስራት ዋነኛ መሠረት ነውና፡፡
********

Tazabi Yehuneta (Pen name)

more recommended stories