የሂውማን ራይት ዎች የቴሌኮም መስመሮች ጠለፋ ክስና የተዓማኒነት ጥያቄ

የሰብአዊ መብት ጠበቃው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ከናይሮቢ ጽ/ቤቱ ያወጣው የዚህ ዓመት ሪፖርት በቴሌኮም መስመሮችና የመረጃ መረብ ጠለፋ ላይ ያተኩራል:: ሪፖርቱ በተዓማኒነቱ ላይ ጥያቄ በሚያስነሱ ጉዳዮችም ታጭቋል:: ለዛሬ የምንመለከተው ከዚህ በታች የተሰጠው አጠር ያለ የአንድ ተገልጋይ ምላሽ ይገኝበታል:: የዚህ ተገልጋይ ምላሽ ወደ መቶ ሰው ለተስተናገደበት ጥናት መደምደሚያ ጎላ ተደርጎ የሚጠቀስና አብዛኛውን ስለዚህ ጉዳይ ጥልቅ ዕውቀት የሌላቸውን የዋህ አንባቢዎችን እንዲስብ ተፈልጎ በመግቢያው ላይ ቀርቧል::

” One day they arrested me and they showed me everything.They showed me a list of all my phone calls and they played a conversation I had with my brother. They arrested me because we talked about politics on thephone. It was the first phone I ever owned, and I thought I could finally talk freely.” — Former member of an Oromo opposition party, now a refugee in Kenya, May 2013 Annual ‪#‎HRW‬ Report on Ethiopia

ጥቅሱን ከዚህ እንደሚከተለው ተርጉሜዋለሁ::

“አንድ ቀን ያዙኝና ሁሉንም ጉዳይ አሳዩኝ:: ሁሉንም ወደ ወንድሜ የደወልኩባቸውን የስልክ ጥሪዎቼን ዝርዝር አሳዩኝ:: ከወንድሜ ጋር ያደረግኋቸውን የስልክ ውይይቶች እንደገና አጫውተው አሰሙኝ:: የያዙኝ ፖለቲካ በስልክ በማውራታችን ነው:: ይህ የስልክ መቀበያ ለመጀመሪያ ጊዜ የያዝኩት ስልክ ስለሆነ ከእንግዲህ በነጻነት አወራለሁ ብዬ አስቤ ነበር::” – በኬንያ የስደተኛ ጣቢያ የሚገኝ አንድ የቀድሞ ኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ግንቦት 2013

ይህን ምስክርነት ተመርኩዘን ጥቂት ሀሳቦች እንሰንዝር::

በመጀመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ሲሆን ከ2011 ጀምሮ ከ15 ሚሊዮን በላይ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያላቸው ወይም የያዙ ግለሰቦች ነበሩ:: ከቅርብ ዓመታት ወዲህም የቴሌኮሚዩንኬሽኑ መስሪያ ቤት በቀጥታ ይታደል የነበረውን የተንቀሳቃሽ ስልክ ሲም የሦስተኛ የሻጭ ሱቆችን መልምሎ በእነርሱ አማካይነት መስመር መሸጥ ከጀመረ ሰነባብቷል::

ስለዚህም የትኛው ተገልጋይ የስልክ መስመሩን እንዳገኘ ለማወቅ ከነዚህ በሀገሪቱ ካሉ በርካታ የቴሌ ቅርንጫፎችና ሻጭ ድርጅቶች የገዥውን ዝርዝርና የፖለቲካ ዝንባሌውን የሚያሳይ መረጃ ማግኘት ይኖርበታል:: ከዚያ በየቀኑ መስመር ከሚረከቡ በአስር ሺህ ከሚቆጠሩ ደንበኞች በተጨማሪ ቀደም ተብሎ መስመር የተሰጣቸውን እስከ 15 ሚሊዮን ደንበኞች ፕሮፋይል አድርጎ ማስቀመጥ ይኖርበታል:: ይህ ስራ በራሱ ቢያንስ አስርተ ዓመታትንና በርካታ ሰራተኛ ይፈጅ ይሆናል::

በዚህ መሠረት ከ15 ሚሊዮን ደምበኛ መካከል ይህ ሀሳቡን ያካፈለን ልዩ ሰው አዲስ አበባ የሚኖር ደንበኛ ነው እንበል:: እንዲያ ከሆነ ምናልባት ከበርካታ የቴሌ የራሱ መሸጫዎችና ከመለመላቸው ሻጮች መሀል ምናልባትም በአስር ሺዎች ከሚቆጠሩ ግለሰቦች መርጦ አንድ አዲስ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ የተንቀሳቃሽ ስልክ ሲም ካርድ ገዝቷል ብሎ እሱን ለመከታተል አጠመደው የሚለው ያን ያህል የሚያሳምን አይደለም::ከዚያም ስልኩን በገዛ በጥቂት ቀናት ውስጥ የደህንነት ሰራተኞች ጠርተው የስልክ ጥሪውን የየ24 ሰዓት ጠልፋ ውጤት አስደመጡት::

ይህ ደግሞ ቴሌ አሁን ባለው ከ 20 ሚሊዮን በላይ የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪዎች ላይ የሚፈጸም ተግባር ሊሆን ነው:: ቴሌ ወይም የስለላው ድርጅት ለዚህ ስራ የሚጠቀመው ጠለፋውንና የጠለፋውን ጥናት ሰርቶ ለቅርብ አለቃው የሚያቀርብ ሰራተኛና በኮምፒውተር የዚህን ሁሉ ሰው ጠለፋ ዝርዝር ፋይል ለመያዝ ያለውን ቦታ(memory) ሲታሰብ ቴሌ ቢያንስ አሁን ባለው አይደለም የዓለም ቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ሠራተኞችንም ጨምሮ የሚችል አይመስለኝም::

በማንኛውም ዜጋ ላይ እንዲህ አይነት ስለላ እንዲካሄድ አያስፈልግም ብቻ ሳይሆን ተገቢም ህጋዊም አይደለም:: ከመንግስት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በሚጠረጠሩ ግለሰቦች በኩል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥያቄ የሚያስነሱ የግለሰብ የስልክና የመረጃ ልውውጦች በተደጋጋሚ ያለሀፍረት 10ይፋ ተደርገዋል:: ይህ ተግባር ትክክል አለመሆኑ እንዳለ ሆኖ ግን የሰባአዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶችም ለሚሰበስቧቸው መረጃዎች ተገቢውን ትኩረት ቢሰጡ መልካም ይመስለኛል:: አለበለዚያ የአይዲዎሎጂ ግብ ግብ የገጠሙ ግለሰቦች በድርጅቶቹ ሽፋን እየተጠቀሙ እንደሆነ መታሰቡ አይቀርም::

በመጨረሻም በተለያዩ ግለሰቦች ዙሪያም ይህን አይነት የማጥመድ ሥራ ተሰርቶ ሊሆን ይችላል:: ምንም እንኳን የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በዚህ ስለላ መረብ መያዝ ተገቢ አለመሆኑ እንዳለ ሆኖ አንዳንድ ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶች ስለሀገሪቱ ደንታ ከሌላቸው ወገኖች ጋር አብረው በመስራት ሊያመጡ የሚችሉትን አደጋ ለመቀነስ የሀገር ውስጥ ደህንነት ይህን አይነት ስራ መስራቱ አይቀርም:: ይህ በብዙ ሀገሮች እንደሚሰራ የስኖውድንና የአሜሪካ የቅርብ ጊዜ ሁኔታ ይነግረናል:: ዩስ አሜሪካ ይህን ስለላ በሌሎች ርዕሰ ብሄሮች ላይ ጭምር ማድረጓን ያጋለጠው ስኖውድን ከፍተኛ ቅጣት ስለሚጠብቀው ለመሰደድ ተዳርጓል:: ይህ የሚያሳየው ሁሉም ሀገሮች አነሰም በዛም የስልክና የመረጃ መረብ ይጠልፋሉ::

እንዲያውም በታዋቂው ምሁር ኦርዌል 1984 ትንበያ መሰረት መንግስታትና ድንበር ተሻጋሪ ኩባንያዎች የዜጎችን ፍላጎትና እንቅስቃሴ እስከ መከታተልና መቆጣጠር እንደሚደርሱ አስቀድሞ አጋልጧል:: የወደፊቱ የቴክኖሎጂ ግስጋሴም ስራ በማቅለል ብቻ ሳይሆን ስጋትም እየሆነ እንደሚሄድ በርካታ ጥናቶች መጠቆም ከጀመሩ ከራርሟል:: ለምሳሌ የሲሲ tvዎችና የመንገድ ካሜራዎች በብዙ ሀገሮች ክርክር አስነስተዋል:: ልዩነቱ የህግ የበላይነት በተረጋገጠባቸው ጥቂት ሀገሮች በነዚህ መረጃዎች ግለሰብን ለመክሰስ መጠቀም አለመቻሉ ነው::ያም ሆኖ በአደጉት ሀገሮች በርካታ ወንጀሎችን በመቆጣጠር፣ አስቀድሞ በመታደግና የግለሰብ ህይወት ድንበርን (privacy) በመጣስ በኩል ከፍተኛ ግጭት እየተከሰተ ነው:: ይሁንና አዲስ የስልክ ተጠቃሚን ገና ለገና የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ይኖረዋል ብሎ ዲያግኖስ የሚያደርግና የሚከታተል መሳሪያ አልተፈለሰፈም::

ቸር ሰንብቱልኝ!
*******

Reagan Solomon

more recommended stories