አቦይ ስብሓት ነጋ እና ‹ኩሩው አሜሪካዊ› በዋሽንግተን

(Daniel Berhane)

ከትላንት ወዲያ ነው ዕለተዓርብ፤ አንጋፋው የኢሕአዴግ ታጋይ እና የቀድሞ አመራር አቦይ ስብሓት ነጋ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ የስታርባክስ(Starbucks) ካፍቴሪያ ጋዜጣ እያነበቡና ቡና እየጠጡ ነበር፡፡

ድንገት ሳዲቅ አሕመድ የሚባል አክራሪ ወሀቢያ መጣና አምባረቀባቸው፡፡ ‹‹እኔ ኩሩ አሜሪካዊ ነኝ›› ሲል ደነፋ – ለሥራ ጉዳይ በሰው ሀገር ባሉት ኩሩው ኢትዮጲያዊ ስብሓት ላይ፡፡

‹‹29ኙ ተከሳቾች ይፈቱ›› ሲልም ለሁሉም ሰው በሚሰማ ድምጽ ተናገረ፡፡ የሳዲቅን አጀንዳ ለመረዳት ከ29ኙ ተከሳሾች አንዷ ከሳውዲ ኤምባሲ 50000 ብር ተቀብላ ስትወጣ እጅ ከፍንጅ የተያዘችው ሀቢባ መሐመድ እንዳለችበት ማስታወስ ብቻ ይበቃል፡፡

ሳዲቅ ጩኸቱን ቀጥሏል፤
ስድስት ሚሊየን አይሁዶች የተጨፈጨፉበትን ክስተት(Holocaust) እንደጀብዱ በጋዜጣው እንዲስተጋባ ሲያደርግ የነበረውን ግለሰብ ደግፎም ‹‹ጀግናው እስክንድር ነጋ ይፈታ›› ሲልም ጮኸ፡፡

አቦይ በልባቸው ‹‹ድሮንስ ከሳውዲ ቀላጤ ምን ይጠበቃል?›› ሳይሉ አልቀረም፡፡

ለማንኛውም አቦይ ቡናቸውን ጨረሱ – የጋዜጣ ንባባቸውንም፡፡ ሒሳባቸውን ከፍለው ወደመኪናቸው ጉዞ ጀመሩ፡፡ ሳዲቅ ይጮኻል ከሥር ከሥር እየተከተለ፡

ቀጠለናም ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ሲል ጮኸ፡፡ አሄሄ! እውን ድምጹን ለማሰማት ፈልጎ ከነበር አጠገባቸው ሄዶ መወያየት ይችል ነበር፡፡ የአቦይ በዝምታ ቡናቸውንና ጋዜጣቸውን ጨርሰው መሄድ፣ መልስ መስጠት ስላልፈለጉ አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ብቻቸውን ቡና እየጠጡ ባሉበት ቦታ ቀርቶ አዲስ አበባ ያለው ጽሕፈት ቤታቸው እንኳን ከቀበሌ ሊቀመንበር ቢሮ የበለጠ ተደራሽ(accessible) መሆኑን መስቀል አደባባይ አካባቢ ያለ ሱቅ በደረቴ የሚመሠክረው ነው፡፡

ሳዲቅ አጀንዳው ሌላ ነው፤ ባለፈው ዓመት ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊን ስብሰባ ላይ የረበሸውን

Berhanu Nega(on the left) and Sadiq Ahmed (on the right side)
Berhanu Nega(on the left) and Sadiq Ahmed (on the right side)

የአበበ ገላውን ‹‹ሪከርድ›› መስበር፡፡ ልክ እንደአበበ ገላው ሳዲቅ አሕመድም የዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ደቀመዝሙር ነውና፡፡

መለስ አበበ ገላውን ንቆ በዝምታ እንዳለፈውና የራሱን ንግግር ያለቅንጣት መደናቀፍ እንዳጠናቀቀው ሁሉ፤ አቦይ ስብሓትም ለሳዲቅ ቅንጣት ግዜ ሳያባክኑ ቡናቸውንና ጋዜጣቸውን ጨርሰው ወደመኪናቸው ሄዱ፡፡

ይኼ ግን ለሳዲቅ አደጋ ነው፡፡ ብርሀኑ ነጋ ሊቆጣ ይችላልና፡፡

ስለሆነም ልክ አበበ ገላው ‹‹የመለስ ጠባቂዎች ተቆጡኝ፣ ዛቱብኝ›› እንዳለው ዓይነት ታሪክ ያስፈልገዋል፡፡ ስለሆነም ከአቦይ ሹፌር ጋር እንካ ስላንቲያ ለመግጠም ሞከረ፡፡ ለወሬ የሚበቃ ነገር ግን አላገኘም፡፡

የሚገርመው ነገር ግን ከዚህ ሁሉ የከሸፈ ሙከራ በኋላ ሳዲቅ አሕመድ በኢትዮጲውያን ሙስሊሞች ስም የሚነግዱ የዲያስፖራ ራዲዮዎች ላይ ቀርቦ የተናገረው ነው፡፡ አሳጥሬ ሳቀርበው፡- ስብሓት ነጋ ንቀውናል ደፍረውናል፤ እንዴት ‹‹በሾቀ››መኪና ያለአጃቢ በዋሽንግተን ይንቀሳቀሳሉ ሲል ተናገረ፡፡

አንዳንድ ታዛቢዎች ‹‹ሳዲቅ ተምታታበት እንዴ? ዋሽንግንተን እኮ አፍጋኒስታን አይደለም፤ የኢትዮጲያ ዲያስፖራም ታሊባን አይደለም›› ብለዋል፡፡

እኔ ግን ከነሐጂ ነጂብ እና ከነዶ/ር ብርሀኑ የሚውለው እሱ ስለሆነ የበለጠ ያውቃል ባይ ነኝ፡፡

ሳዲቅ ሌላም ታሪክ አለው፡፡ አቦይ ‹‹ሙስሊም›› የሚባል ቃል ሲሰሙ ይደነግጣሉም ብሏል፡፡ አዬ! ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አሉ፡፡ Ethio-American Muslim Ad-Hoc committee የሚባለውን የይስሙላ ኮሚቴ ሲያቋቁም ለሳውዲዎች ቃል የገባላቸው ይሄን ነበር እንዴ? ልክ እንደአሜሪካ ‹‹ሙስሊም›› የሚባል ቃል ሲሰሙ የሚደነግጡ ሰዎች ያሉባት ኢትዮጲያውያን መፍጠር፡፡

ያም ሆነ ይህ ቀጣዩን መተንበይ አይከብደንም፤ ልክ አበበ ገላው የመለስ ስብሰባ ላይ ካጓራ በኋላ ሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲን ሄዶ ‹‹ገብርኤል በሕልም አዞኝ ነው›› ብሎ ገንዘብ እንደተዋጣለት፤ ሳዲቅም ከሰሞኑ ከአንድ የዲያስፖራ አክራሪዎች መስጊድ ሄዶ ‹‹አብዱል ወሐብ አዞኝ – ጂሀድ ፈጽሜያለሁና ብር ስጡኝ›› ማለቱ አይቀርም፡፡

የተለመደውን አገላለጽ ልጠቀምና፡- ‹‹ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎም ስልቻ››

—–

(ማስታወሻ፡- ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ – በእስልምና ስም በሚነግዱ አክራሪዎች እና በቀኝ አክራሪ ጽንፈኞች መሀል ስላለው ጋብቻ በቀጣይ ሳምንታት የማቀርበው ይሆናል)

Daniel Berhane

more recommended stories