የሀገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ ታሠሩ

የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም ፥ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።

ከፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ፥ ተጠርጣሪው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።

ኮሚሽኑ ግለሰቡ ፈጽመውታል ከተባሉ የሙስና ተግባራት ጋር በተያያዘ ሌሎች ተያያዥ ምርመራዎችን እያካሄደ ይገኛል።

የዛሬ አመት ገደማ ኮሚሽኑ በአቶ ወልደስላሴ ወንበር ላይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ አቶ አይቼው ተፈታን በተመሳሳይ ወንጀል ከሷቸው በአሁን ጊዜ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው ።

አቶ አይቼው ከገቢ በላይ ምንጩ ያልታቀ ሃብት አፍርተዋል የተባሉባቸው ሆቴሎች እና ሌሎች ንብረቶች በአሁን ጊዜ መታገዳቸው ይታወቃል።

*********

ምንጭ፡- ፋና

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories