ቤኒሻንጉል:- በዜጎች መፈናቀል ሳቢያ የም/ቤት አባላት ታሠሩ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሽ ዞን በዜጎች መፈናቀል እጃቸው አለበት የተባሉ ኃላፊዎች ያለመከሰስ መብት መነሳቱን ፋና እና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጹ፡፡

*******

ፋና

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ።

ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ የተደረገው በክልሉ ከማሺ ዞን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መለተጊ ቦጋለና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊው አቶ ገርቢ በጊዜው ናቸው።Map of Benishangul-Gumuz Region - Ethiopia

እነዚህ አመራሮች የክልሉ መንግስትና ፓርቲው በማያውቀው ሁኔታ በዞኑ ያሶ ወረዳ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸው በመረጃ በመረጋገጡ ነው እርምጃው የተወሰደባቸው።

በዚህ የማፈናቀሉ ተግባር ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 18 የሚደርሱ ከቀበሌ እስከ ዞን የሚገኙ አመራሮች ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በማጣራት ባአሁኑ ጊዜ ተፈናቃዮች ተረጋግተው ወደቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ኑሮዋቸውን እያከናወኑ ነው።

***************

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔው በአማራ ክልል ተወላጆች ማፈናቀል ላይ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው ሁለት የምክር ቤቱ አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡

ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው በክልሉ የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዞኑ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊን ነው፡፡

ምክር ቤቱ በዋና አስተዳዳሪው አቶ ወልተጂ በጋሎ እና በኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ገርቢ በጊዜ ላይ ከክልሉ ፓሊሲ ኮሚሽን እና ከፍትህቢሮ የምርመራ ቡድኖችን አደራጅቶ መረጃዎችን በማጠናከር ግለሰቦቹን ለህግለማቅረብ የሚያስችል ጥልቅ ምርመራ መደረጉን ገልጿል፡፡

የግለሰቦቹ አድራጎት የክልሉ መንግስትና ህዝብን ስም ያጎደፈ በመሆኑ ከስልጣናቸው ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

*************

Previous:
ከቤኒሻንጉል ክልል ዜጎችን ያፈናቀሉ ኃላፊዎች ተባረሩ
የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተወሰነ
የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ
የቤንሻንጉል ፕ/ት: ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎችም ናቸው – አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን
በቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” በሚል ተባረሩ

Daniel Berhane

more recommended stories