የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ 34 ከመቶ ደርሷል

(ጥላሁን ካሳ)

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራዎች ክረምቱ ከመጠናከሩ በፊት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው አለ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን።

ኮርፖሬሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገረው በዚህ አመት ይጠናቀቃል ከተባለው 40 በመቶ ስራ እስከ ግንቦት መጨረሻ 34 ከመቶ በላይ የሚሆነው ተከናውኗል።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ከሚያልፍባቸው ቦታዎች መካከል በዋነኛነት ጊዮርጊስ አካባቢ በሚገኘውን የዋሻ አናት ላይ አፈር የማልበስ ስራ ተከናውኗል።Addis Ababa ligh train project

ስራውን ለማፋጠን እስከ ምሽት ድረስ በመስራት ርብርብ እየተደረገ በመሆኑ የኮንክሪት እና ብረት ማልበስ እንዲሁም የሀዲድ ስራው እስከ ሀምሌ አጋማሽ እንደሚጠናቀቅም ነው ኮርፖሬሽኑ የገለጸው።

ሳሪስ አካባቢ ባለው የባቡሩ ሳይትም በአካባቢው የብረታ ብረት ማማረቻ ውስጥ የሀዲዱ ርብራብ እየተመረተ በመሆኑ ስራው እንዲቀላጠፍ አስተዋጽአ እንዳለው ታምኖበታል።

በፒያሳ ፣ ጎጃም በረንዳ አውቶብስ ተራ ለሚያልፈው የባቡር መስመር ስራም ጎጃም በረንዳ አካባቢ የመንገድ ዳር ቦታዎችን ለባቡር መስመሩ ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።

ነባሩ የውሀ መስመር ከሜክሲኮ እስከ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ድረስ በአዲስ በመቀየሩም የባቡር መስመሩ ከትናንት እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ ፤ ከስፖርት ኮሚሽን እስከ ቡና እና ሻይ ያለውን ቦታ በማጠር ስራው የተጀመረ ሲሆን ፥ እስከ ቡናና ሻይ ያለው ቦታም በመታጠር ላይ ይገኛል ።

**********

Source: Fana – June 19, 2013, titled “የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ዋና ዋና ስራዎችን ከክረምቱ በፊት ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው”

Daniel Berhane

more recommended stories