የአዲስ አበባ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ የ 40 በ 60 ፣ የ 10 በ90 እና 20 በ80 የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታና የምዝገባ ስነ ስርአት ይፋ አደረገ ፡፡
በዚህም መሰረት የ 10 በ 90 እና የ 20 በ 80 ምዝገባ ከሰኔ 3 እስከ 21 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙት በሁሉም ወረዳዎች ይደረጋል ፡፡
የ 40 በ 60 ምዝገባ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመረጡ ቅርንጫፎች ከሀምሌ 5 እስከ 17 የሚካሄድ ሲሆን ፥ በማህበር ለሚደራጁ ደግሞ ምዝገባው ከ ሀምሌ 15 እስከ 30 የሚካሄድ ይሆናል ፡፡
ለመንግስት ሰራተኞች ደግሞ በተለየ ሁኔታ 117 ኛ መመዝገቢያ ቦታ ተዘጋጅቶ ምዝገባው ለብቻ የሚካሄድ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ አሳውቋል ፡፡
ለምዝገባ ብቁ ለመሆንም በቢሮው የሚከተሉት መስፈርቶች ተቀምጠዋል ፡፡
* እድሜው/ዋ ከ 18 አመት በላይ የሆነ
* በከተማው ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ አመታት የኖረና እየኖረ ያለ።
* የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ አመታት በስራ ወይም በትምህርት ምክንያት ከከተማዋ ውጪ የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና
፥ ማስረጃው ቦታውን ለምን ያክል ጊዜ እንደቆየ ወይም እንደሚቆይ በዝርዝር ካቀረበ ብቁ ይሆናል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈግ የቁጠባ መጠን ደግሞ ይሄ ነው ብሏል ቢሮው ፥
ለ 40 በ 60
* ለባለ 3 መኝታ ቤት ብር 2453
* ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 1275
* ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር 1053
ለነባር 20 በ 80
ከምዝገባ ቀን ጀምሮ በየወሩ በተከታታይ 5 አመት መቆጠብ ይኖርበታል
* ለ ባለ 3 መኝታ ቤት ብር 685
* ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 561
* ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር 274
* ለስቲዲዮ መኝታ ቤት ብር 151
ለአዲስ 20 በ 80
* ለባለ 3 መኝታ ቤት ብር 489
* ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 401
* ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር 196
ለ10 በ 90
የመጀመሪያ የቁጠባ መጠን ብር 187 ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ሳይቋረጥ በተከታታይ ለ 2 አመታት መቆጠብ ይኖርበታል
***********
Source: Fana.