ኢህአዴግ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ካውንስል ም/ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ

በሱዳን ኮንግረስ ፓርቲ አስተባባሪነት በካርቱም ሱዳን ከሚያዝያ 19-20 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በተካሄደው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስረታ ጉባኤ ላይ በኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ በአቶ ሬድዋን ሁሴን የተመራ የኢህአዴግ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ተሳትፎ ተመልሷል፡፡

በጉባኤው ላይ ከ35 የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገኝተዋል፡፡ የጉባኤው አላማ በአፍሪካውያን መካከል ያለውን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር እና የአፍሪካን ህዳሴ እውን ለማድረግ ፓርቲዎች የበኩላቸውን ድርሻ የሚወጡበት መድረክ መፍጠር ነው፡፡EPRDF logo

በጉባኤው ላይ የካውንስሉን አስፈላጊነት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና፣ ለአፍሪካ ዕድገት የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚና የሚሉ መነሻ ፅሑፎች እንዲሁም የካውንስሉ ህገ ደንብ ረቂቅ ቀርበው ውይይት ተደርገውባቸዋል፡፡

በካውንስሉ ላይ አባል የሚሆኑት ፓርቲዎች የእያንዳንዱ አገር ገዢ ፓርቲ እና ከየአገሩ በፓርላማ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲሆኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በጉባኤው ላይ ከቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ፣ ከእስያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካውንስልና የደቡብ አሜሪካና ካሬቢያን አገሮች የፖለቲካ ካውንስል ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ጉባኤው በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት የተካሄደ ሲሆን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት 5ዐኛ ዓመት ላይ መካሄዱም ታሪካዊ እንደሚያደርገው ተመልክቷል፡፡

በመጨረሻም ጉባኤው 3ዐ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም አንድ ሊቀመንበርና አራት ምክትል ሊቀመንበሮችን በመምረጥ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ ከአገራችን በጉባኤው ላይ የተገኘው ኢህአዴግ ሲሆን ካውንስሉን በምክትል ሊቀመንበርነት እንዲያገለግል ተመርጧል፡፡

***********

Source: EPRDF

Daniel Berhane

more recommended stories