የ‹‹መድረክ›› ሰልፍ እንድምታ

(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ)

የተቃዋሚዉ ጎራን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት አብይት ፖለቲካዊ ክስተቶችን አስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ትግል ሲኮላሽ የመድረክ ደግሞ ቀዝቀዝ ያለ በሚመስል መልኩ ተስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በተስተጓጎለ በሳምንቱ የመድርኮቹ መሳካቱ ምን ሊያመላክት ይችላል የሚለውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የመድርኩን ሰልፍ ከራሱ ከመድርክ፣ ከመንግስትና ከህዝብ አንፃር ሊኖረው የሚችለውን እንድምታ አጠር ባለ መልኩ ለማየት እንሞክራለን፡፡

ሀ) ከመድረክ አንፃር

መድርክ ከሌሎችና ፓርቲዎችና ከራሱም ያለፈ የትግል ልምድ የተማረው ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ፓርቲው ቀድሞ ከነበረበት ጽንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ በተወሰነ መልኩ ለዘብ እያለ መምጣት የሚያሳዩ ሁሄታዎችን መታዘብ ይቻላል፡፡Medrek party rally - Addis Ababa Dec. 2014

መድረክ ከሌጋሲው የተማረው ጉዳይ ቀድም ሲል በነበው ፅንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ የመንግስትን የቁጥጥር ጫና እንዲሚያጠብቀው ሳይማር እንዳልቀረ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ባልተለመደ መልኩ ሌሎች ተቃዋሚዎች ክፉኛ የሚጥሉትንና መንግስት እየተጠቀመበት ያለውን ባንዲራ በሰልፍ ውስጥ መጠቀሙ በተወሰነ መልኩ ከአክራሪነት ለዘብ ያለ አቋም እያሳየ ለመምጣቱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ፓርቲው ወዶም ይሁን ተገዶ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢህአዴግ ጋር መመሳሰል ባይችል እንኳን መንግስት ከሚፈልገው የአቋም መለሳለስ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል የሚጠቁሙ ፍንጮች እንዳሉ መውሰድ ይቻለላል፡፡

በሌላ መልኩ መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን ዉጤት ተከትሎ መንግስት የሚሰጋባቸውን ችግሮች እንዳይከሰቱ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ለማድርግ ከመንግስት ጋር ስምምንት ላይ ሳይደርስ እንዳልቀረ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ፡፡ በአቋም እየተለሳለሰ መምጣቱና ለሰልፉ ኃላፊነቱን ከመንግሰት ጋር መጋራቱ ሰልፉን ስኬታማ ለማድረግ ሳይግዘው እንዳልቀረ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በ2002 ምርጫ ከኢህአዴግ ጋር አንገት ለአንገት ተጋጥሞ የተሸነፈው መድረክ በመጪው አገራዊ ምርጫም የፓርቲዎችን ዉህደት በመጠቀም እና እንደ ኢህአዴግ የግንባር መልክ ያለው ጠንካራ ፓርቲ በመፍጠር ብቃት ያለው ተፎካካሪ የመሆን ፍላጎት አለ፡፡ በመሆኑም ሰልፉ በ2002ቱ ምርጫ የተነጠቀውን ድምፅ በአሸናፊነት ለመቀማት ያለመ የምርጫ ስትራቴጂ አካል አድርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ መድረክ መንግስት ጋር እልህ መያያዙ ጠቃሚ አንዳልሆነ በመረዳት ሰልፉን ሰላማዊ ድምጽ ማሰሚያ ለማድረግ ያሰበበት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ መድረክ ለስለስ ብሎ የቀረበበት የትግል አቅጣጫ ዘላቂነት ይኖረዋል ብሎ መውሰድ አይቻልም፡፡ የመድረክ መለሳለስ የመንግስትን የቁጥጥር ትኩረት ለማስወገድና እና ለምርጫው የሚያስፈልገውን ዝግጅት እንቅፋት የመቀነስ ሂደት ሊሆን ይችላል፡፡

ለ) ከመንግሰት አንፃር

የመድረኩ ሰልፍ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጠቃላይ የሌጋሲውን እንቅስቃሴ በማይጎዳ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ ከሚፈለግ የመንግስት ፍላጎት ማዕቀፍ ዉስጥ የሚታይ ነው፡፡

እንደመንግሰት ሰላማዊ ሰልፍን የመሳሰሉ ብዙሀን የሚሳተፍባቸው የተቃዉሞ ትግሎችን በጥርጣሬ የመመልከት ስሜቱን መድርክ የቀረፈው የሚመሰል ምልክቶች አሉ ማለት ይቻላል፡፡ በመንግስት በኩል ያለው ፍላጎት ተአማኒነትን በሚፈጥሩ ጥብቅ ሂደቶች ዉስጥ በማለፍ አቋማቸውን ማራመድ የሚችሉ ለዚህም ኃላፊነት የሚወስዱ ፓርቲዎችን የመደገፍ ፍላጎትን እንዳለው ሊያሳይ ይችላል፡፡ አንደመንግሰት የፓርቲዎች አንቅስቃሴ የሚያሰጋው “ኢህአዴግ በምርጫ ያሸንፉታል”የሚለው ላይ ሳይሆን የትግሉ አቅጣጫ ለአብዮት በር የሚከፍቱ ህዝባዊ አመፆች መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ነው፡፡

የፓርቲዎቹ ግርግር በአገሪቱ የተጠናከረ የመድብለ ፓርቲ ስርአት ተመስርቷል ለሚለው እውነታ ምስክር ሊሆን ስለሚችል እንደ መንግስት የሚፈለግ ፖለቲካዊ ክስተት ነው፡፡ ያም ሆኖ ከሁሉም ነገሮች ቅድሚያ የሚሰጠው ሰላማዊ ሰልፍን የመሳሰሉ ብዙሀን የሚሳተፉባቸው የተቃዉሞ ትግሎች ላልተፈለገ አጀንዳ መጠቀሚያና ለህዝባዊ አመፅ መነሻ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ፍራቻ በመንግስት በኩል ጎልቶ ይወጣል፡፡ በዚህ የተነሳ በመንግስት በኩል ኃላፊነትን የሚጋሩ ፓርቲዎችን ለቀቅ የማድረግ ዝንባሌ እንዳለ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በሌላ በኩል ፓርቲዉ ከቀድሞ አቋሙ ለዘብ እያለ መምጣቱ፣ ከሰልፉ በፊት የነበረው የዝግጅት ሂደት ከአላስፈላጊ ከግርግር የፀዳና ሰላማዊ እንዲሆን ማድረጉ በመንግስት ዘንድ አመኔታን ሳይፈጥርለት አልቀረም፡፡ የኢትዮጵያን ባንዲራ መጠቀሙና የሰልፉን ሂደት ከረብሻ ለማጽዳት በወሰደው ኃላፊነት የተነሳ በመንግስት በኩል ብቻ ሳይሆን በራሱ በኢህአዴግ አባላትም ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡ ፓርቲው አለም አቀፍ ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች ሰብስቦ መያዙ መንግስት በተወሰነ መልኩ ለፓርቲው ይሁንታን እንዲሰጥ ተፅዕኖ ሊሆን እንደሚችልም መገመት ይቻላል፡፡ በመንግሰት በኩል ለዘብተኛ አቋም ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲፈጠሩ የሚያደርገውን ጥረት መድርክን እንደ አንድ አጋዥ ለመጠቀም የመፈልግ ስመቶችም ማንበብ ይቻላል፡፡

ሐ) ከህዝቡ አንፃር

የህዝቡ እንድምታ ሲባል ራሱን ከፖለቲካዉ ባይተዋር ያደረገውን ብዙሀኑን ሳይሆን ለጉዳዩ የይገባኛል ስሜት ያንፀባረቁትን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ እንድምታ ነው፡፡ የመድርክ ሰልፍ ከህዝቡ አንፃር የሚኖረው አንድምታ በተለያዩ መልኩ ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው በሰልፉ ወቅት ያራማዳቸው አቋሞች እንደሚፈለገው ከረር ብለው አለመንፀባረቃቸው ከኢህአዴግ ጋር የተሞዳሞደ አድርጎ የመሳል አዝማሚያ አለ፡፡ ፅንፍ ተቃዋሚ በሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ የመድረክ መለሳለስ መድርክን ነፃ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አድርጎ የመቀበል ችግሮች ሳይፈጥርበት አልቀረም፡፡ በሌላ በኩል ህዝቡ መድረክን ከኢህአዴግ ጋር የሚፎካከር እና የፖለቲካ ኃይሉን ሚዛናዊ የሚያደርግ ፓርቲ እንዲሆን የመፈልግ አዝማሚያ አለ፡፡ በአንዳንዶቹ ዘንድ ደግሞ መድርክ እንስቃሴ የተለመደ ምርጫ ክስተት በመሆኑ በአገሪቱ ፖለቲካዊ ዉጤት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ሊኖር አይችልም የሚልም እንድምታ ሊኖረው ይችላል፡፡

*******

Guest Author

more recommended stories