[Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም

ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ‹‹እኔ የማውቀው ከደርግ ከሚገኘው ንብረት አብዛኛውን ከሕዝብ ስንካፈል እንጂ ከውጭ ለእርዳታ የመጣውን ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለጦር መሣሪያ ስናውል አይደለም›› አሉ፡፡

ጄኔራሉ ይህን ያሉት ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ ላይ፡- ለ1977ቱ ረሀብ የመጣው ዕርዳታ ለድርጅት ሥራ እንዲውል ተደርጓል ስለሚለው የዶ/ር አረጋዊ በርኸ ስሞታ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ ዶ/ር አረጋዊ ከቀደምት የህወሓት አመራሮች አንዱ ሲሆኑ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከድርጅቱ ለቅቀው በአውሮፓ የሚኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዶ/ር አረጋዊ ለዕርዳታ ከመጣው ገንዘብ 50 በመቶ ለማሌሊት ማጠናከሪያ፣ 45 በመቶ ለወታደራዊ ወጪ ተመድቦ 5 በመቶ ብቻ ለሕዝብ እንዲውል በማዕከላዊ ኮሚቴ ተወስኖ ተግባራዊ ተደርጓል የሚሉ ሲሆን፤ በወቅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ግን የዛሬ 5 ዓመት በአሜሪካ ራዲዮ አማርኛ ፕሮግራም ላይ በሰጡት አስተያየት እንደዚያ ዓይነት ውሳኔ አልተወሰነም በማለት መቃወማቸው ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ ሌላው የቀድሞ የድርጅቱ አመራር ገብሩ አሥራት በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ፡- በወቅቱ ድርጅታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ መንግስታት የሚጠቀሙት መሥመር ያንኑ የሰብዐዊ ዕርዳታ የሚመጣበትን መሥመር በመሆኑ እና ሁሉም ገንዘብ አንድ ቋት ውስጥ የሚገባ በመሆኑ ስሞታው የወቅቱን አሠራር ካለመገንዘብ የሚመጣ ነው የሚል አጭር አስተያየት አስፍረዋል፡፡

እነዚህን አስተያየቶች በመጥቀስ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በወቅቱ የማለሌሊት/ህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል እና የሠራዊቱም ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ስሞታውን አጣጥለውታል፡፡

በወቅቱ በተለይ በረሀቡ የተጠቃው የራያ(ደቡባዊ ትግራይ) አካባቢ ሀላፊ የነበሩት ጻድቃን የገንዘብ አወጣጥ የመቆጣጠር ሀላፊነት የሳቸው ሳይሆን የማሕበረ-ኢኮኖሚ ክፍል መሆኑን ከጠቀሱ በኋላ ‹‹እኔ የማውቀው ከደርግ ካገኘነው ንብረት አብዛኛውን ከሕዝብ ስንካፈል እንጂ ከውጭ ለዕርዳታ የመጣውን ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ስንካፈል አይደለም›› ብለዋል፡፡ የዕርዳታ ገንዘብ ለማሌሊት ምሥረታ ግብዣ ዋለ የሚለውን ስሞታም አጣጥለው የታጋዩን ቀለብ ከተቸገረው ሕዝብ ጋር ይካፈል እንደነበር አውስተዋል፡፡

የጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ሙሉ አስተያየት ከታች ባለው ቪዲዮ ላይ ይመልከቱ፡፡

——

Watch Video below.

*************

ተዛማጅ፡- ማሌሊት መሠረታዊ ወታደራዊ ለውጥ አምጥቷል – ጄኔራል ጻድቃን [Video]

 

Daniel Berhane

Daniel Berhane

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago