የፌዴራሉ ካቢኔ የ155 ቢ. ብር በጀት አዋጅ ረቂቅ አፀደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 30/2005  ባካሄደው 49ኛው መደበኛ ስብሰባ የ2006 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ 154.9 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በዚህ መሰረት ለ2006 በጀት አመት በፌዴራል መንግስት ለሚከናወኑ ስራዎችና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን በጀት አጽድቆ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ወቅት ስራ ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ እና የፌዴራሽን ም/ቤት በወሰነው ቀመር መሰረት የፌዴራሉ  መንግት ለክልሎች የሚሰጠውን የድጋፍ በጀት መጠን መወሰን ስለሚኖርበት ከሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በሚፈጸመው በአንድ የበጀት አመት ጊዜ ውስጥ የፌዴራል መንግስት በጀት 154,903,290,899/ አንድ መቶ ሃምሳ አራት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር/ እንዲሆን ወስኗል፡፡

ከዚህ ውስጥ፡-

* ለመደበኛ ወጪዎች——————–ብር 32,530,000

* ለካፒታል ወጪዎች ——————- ብር 64,321,732,351

* ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ————— ብር 43,051,558,548

* የምዕተ ዓመቱን ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ– ብር 15,000,000,000 እንዲሆን ተመድቧል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት  በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስተላልፏል፡፡

**********

Source: ERTA – June 7, 2013, titled “የፌዴራል መንግስት የ2006 በጀት 154.9 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ተወሰነ

9.14540.489673
Daniel Berhane

Daniel Berhane

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago