ህወሓት የመራው ትጥቅ ትግል ባለቤት ትግራይ ነው – ይድረስ የታሪክ ቅርምት ትርጉም ላልገባችሁ!

ሰሞኑን ከተከናወነው የኢህዴን/ብኣዴን 35ኛው የምሰረታ በዓል ተያይዞ በማሕበራዊ ሚድያና በተለያዩ የሕበረተሰብ ክፍሎች ውሎዎች ቡዙ ኣከራካሪ ጉዳዮች እየተነሱ ይገኛሉ፡፡ ወደነዛ የክርክር ኣርእስቶች ከማግባቴ በፊት ግን ለብኣዴን ኣባላት የታሪኩ ባለቤት ለሆኑት የኣማራ ክልል ህዝቦች እንካን ለ35ኛው የምሰረታ በዓል በሰለም አደረሳችሁ ለማለት እፈልጋሎሁ፡፡

ከዚህ በመለስ ባለፉት ሳምንታት የኢህዴን/ብኣዴን የምስረታ በዓል መሰረት በማድረግ የተከነዋነኑት ፍፃሜዎች እና ትዝብቶችን ለማስቀመጥ እመኩራሎሁ፡፡ ኣስታየቴቼ በተለያዩ መንግስት ሚድያዎች የተለላፉ ዘጋቢ ፊልሞች፣ ቃለ-መጠይቆች፣ በማሕበራዊ ሚድያ የተሰጡ ኣስታየቶች ና በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከተለያዩ የህብረተስብ ክፍሎች የተንፀባረቁ ስሜቶችን መሰረት ያደረጉ ይሆናሉ፡፡

መጀመርያ ግን እኔ እንደ ግለ ሰው ለ17 ዓመታቱ የትጥቅ ትግል ያለኝ ስሜትና ትርጉም ላጋራችሁ፡፡ እኔ እንደ ኣብዛኘቹ የዚህ ዘመን የትግራይ ወጣቶች በዚህ ትጥቅ ትግል የተከፈለው መራራ መስዋእት ና እሱን ተከትለው በትግራይ የተፈጠሩት ማህበራዊ መመዛበሎች ኣልፌ የወጣሁ ወጣት ነኝ፡፡ በኛ ቤት ና እኛ ቤተሰብ ኣከባቢ በትጥቅ ትግሉ ወቅት የተከፈለው መስዋእት ኣሁንም ገና ትኩስ ነው ያለው፡፡ ኣልበረደም የኛ ቤተሰብ የኢኮነሚ ድቀትና ማህበራዊ ቀውሶች ከትግሉ መስዋእት ጋር የተያያዡ ናቸው፡፡

እሩቅ ሳልሄድ እኔ ኣባቴ በመልክ ኣላቀውም፡፡ የት እንደተሳዋና የት እንደተቀበረ ኣላቅም፡፡ በወሬ እንደሰማሁት ጉና ተራራ ኣከባቢ እንደሆነ ነው፡፡ ገና ጨቅላ ህፃን እያሎሁ ታግሎ ተሰውተዋል ተብለን የህወሓት ተጋዮች የመስዋእትነት መታቅያ የተሰጠንም 1988/89 ኣከባቢ መሆኑን ኣስታውሳሎሁ፡፡ የኣባቴን መስዋእት በተነገረበት እለት እኔ ልጅ ሰለነበርኩ እምብዛም ትርጉሙ ባይገባኝም፤ በኛ ቀጠና (30-40) ኣባወራዎች በሚኖሩባት መንድር በዛን እለት በግምት እስከ 30 የሚሆኑ ታጋየች መስዋእት መርዶ ተነግሮ ኣዛኝም ለቀስተኛም መለየት የከበደበት ጨለማ ቀን እንደነበረ ኣስታውሳሎሁ፡፡

ወደኛ ቤት ስመጣም ከኣንድ ቤት 5 ሰዎች ነበር ለትግል የወጡት፡፡ ኣባቴ፣ ኣጎቴ(የእናቴ ታናሽ ወንድም ና የኣክስቴ ልጅ፡፡ ኣባቴ ና የኣክስቴ ልጅ ሲሰው በሂወት የቀረው ኣጎቴ ነው፡፡ ኣጎቴ እስቅርብ ግዜ ድረስ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የቆየ ሲሆን ኣሁን ጥሮታ ወጥቶ በምእራብ ትግራይ ኣንድ ጎስቃላ ገበሬ ሆኖ እየነረ ይገኛል፡፡

ይህንን የትግል ተሳትፎና መስዋእት ወደ ቅርብ ዘመዶቻችን ሳሰፋው ከዚህ የተለየ ኣይደለም፡፡ ከኣባቴና ከናቴ ቅርብ ዘመዶች ያልከፈለ የለም፡፡ የኣባቴ የኣክስት ልጆች፣ የኣባቴ የኣጎት ልጆች፣ የእናቴ የኣክስት ልጆች፣ የእናቴ የኣጎት ልጆች ተሰውተዋል፡፡ ለምስሌ በናቴ በኩል ከ20-30 ሜትር ርቀት ከሚገኙት 3 ጎጆዎች 5 ሰው ተሰውተዋል፡፡ ቅድም የጠቀሰኩት የኣክስቴ ልጅ፣ የኣጎቴ ታደሰ ሁለት ልጆች፣ ና የኣገቴ ትክለሃይማኖት ሁለት ልጆች፡፡ በተለይ የኣጎቴ ተክለሃይማኖት በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡ ኣጎቴ ተክለሃይማኖት ሁለት ልጆች ብቻ ነበር የወለደው ሀሉቱም ተሰውተዋል፡፡ ይሄ ምስኪን ኣጎቴ የልጆቹን መርዶ ከተነገረው በኋላ በሽተኛ ሆነ ለረጅም ኣመታት ቆይቶ በቅርብ ኣመታት ኣልፈዋል፡፡

ይሄ ታሪክ በግለሰብ ደረጃ ስነግራችሁ የኣብዛኛው የትግራይ ቤተሰብ ታሪክ ለመዘርዘር ሰለሚከብድ የኔው ምሳሌ በማድረግ የትግራይ ህዝብ ለትግሉ የከፈለው መስዋእት ይወክልላ ከሚል እምነት ነው፡፡Photo - TPLF revolutionary torch

ከዚህ ኣንፃር ሲታይ ትግራይ ከ 60 ሺ በላይ ሰማእታት፣ ከ100 የጦርነት ኣካል ጉዳተኞች፣ በ10ሺዎች የሚቆጡሩ በኣውሮፕላንና በከባድ መሳርያ የተጨፈጨፉ ንፁሃን ዜጎች ኣሉዋት ሲባል ከሞላ ጎደል እያንዳዱ የትግራይ ቤተስብ ይነካል ማለት፡፡

የትግራይ ህዝብ እንደዛ ኣምርሮ እንዲታገል ና መስዋእት እንዲከፈል ምክንያቱ ምን ነበረ ብለን ስንጠይቅ ከምናገኛቸው መልሶች ኣንዱ የታሪክ ና የማንነት ጉዳይ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ከኣፄ ሚኒሊክ መምጣት በኋላ ኣልጣመውም፡፡ ተዋረደ፣ ታሪኩ ተዘመተ፣ መንነቱ ተናቀ፡፡ ጭቆና ኣንገሸገሸው፡፡ በየግዜው መማረሩን ገለፀ፡፡ እስከ ኣመፅም ደረሰ፡፡ በተለይ በ20ኛው ክ/ዘመን ኣንደኛው ኣጋማሽ ብረት እንስቶ እስከመታገል ደረሰ፡፡ ይሄ ክስተት ቀዳማይ ወያነ የምንለው ክስተት ነው፡፡ ሆነም ግን ተዳፈነ፡፡

የሁለተኛው ወያነ የኣመፅ መንስኤም ምክንየቱ ግልጥ ያለ የማንነት ጥያቄ ነው፡፡ ይህ በህወሓት መሪነት ለ17 ዓመታት የተካሄደው ትግል ድል እንድያደርግም ቁልፍ ምክንያት የነበረው፤ ድርጅቱ የትግራይ ህዝብ ጥያቄ የብሄረዊ ማንነት ጥያቄ መሆኑን በማመን ትግሉ በብሄር ማንነት ጥያቄ በመቃኘቱ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነበር የትግራይ ህዝብ ከጫፍ እሰከ ጫፍ ከድርጅቱ ጎን የተሰለፈና መስዋእት የከፈለው ብየ ኣምናሎሁ፡፡

ከድሉ ማግስትም የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱ ተቀብሎ የራሴ የሚለውን ታሪክ ና ማንነት ጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ህገመንግስታዊ ስርዓት በመተከሉ ዴሞክራስያዊ ብሄርተኝነቱ ጠብቆ እንደማንኛውም የሃገሪቱ ህዝቦች በሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ግምባታ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

የትግራይ ህዝብ ደርግ ለመጣል ትልቁን ድርሻ የተጫወተ ብቻ ሳይሆን ትልቁን መስዋእት የከፈለ መሆኑን እያወቀ፤ የተለየ ካሳ ሳይጠይቅ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ኣብሮ ለመልማትና ለበልፀግ እየሰራም ይገኛል፡፡

የትግራይ ህዝብ ለከፈለው መስዋእት ከሳ መከፍልም ኣይቻልም፡፡ የተከፈለው መስዋእት በቁሳዊ ምንዛሬ ካሳ ይከፈል ከተባለ ከተከፈለው መስዋእት ኣንፃር በጣም ከባድ ብቻ ሳይሆን ከሰብኣዊነትም የራቀ ነው፡፡ ለትግራይ ህዝብ ካሳው ግን ምስጋና ነው፡፡ በጦርነቱ ወቅት ለከፈለው የሂወት መስዋእት ብቻ ሳይሆን በሳላማዊ ትግሉ ላሳየው ዴሞክራስያዊ ብሄርተኝነት ጭምር፡፡ ከነዛ በፊልም የምትመለከትዋቸው ጀግና ተዋጊ ታጋዮች ኮ 35ሺ በላይ የሚሆኑት በ1987 ዓ/ም ህብረ-ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ሲወሰን ተቀንሰው እዚ ግባ የማይባል መሸኛ ተስጥተዋቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል፡፡ እነዛ ምልሶች ኣሁን ጀግንነታቸው ድብዝዞ ኣረጌ ኣንበሳ ሆነው በየገጠሩ ንሮ ከብደዋቸው ጨልቃማ ገበሬ ሆነው ይኖራሉ፡፡ ኣልያም በተከተሞች ዝቅተኛ የእለት ንሮዋቸው እየገፉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ መስዋእት የተከፈለው ለኢትዮጵያ ዴሞክራስያዊ አንድነት ሲባል ነበረ፡፡

የሰማእታት ቤተሰቦች እነደዚሁ፡፡ እኔ እስከማቀው ለሰማእታት ቤተሰብ (ለሁሉም ባይሁንም) ማቃቃምያ ተብሎ ከ3000-3500 ብር ከ1988-89 ዓ/ም በነበሩት ግዝያት ተሰጥተዋቸዋል፡፡ ይሄ ካሳ ኣይደለም፡፡ በትግልና በመስዋእትነት የተራቆተው የትግራይ ህዝብ ንሮ በዚህ ኣይካስም፡፡ ኣብዛኞቹ የሰማእታት ልጆች ኣሳዳጊ ኣጥተው ተንከራተው ኣድገዋል አልያም መድረስ ያነበረባቸው የሂወት ደረጃ ሳይደርሱ ቀርተዋል፡፡ የሰማእታት ወላጆች እንዲሁ ጧሪ ሳይኖራቸው የእርጅና ዘመናቸው በችግር ና እንግልት እየገፉ ይገኛሉ፡፡

ይሄ ሁሉ መስዋእት የተከፈለው የትግራይ ህዝብ ማንነት ለማክበርና ዴሞክራስያዊ ኣንድነትዋ የጠበቀች ኢትዮጵያ ለመገባት ነው፡፡ ታድያ የትግራይ ህዝብ ማመስገን ሲገባ የሰራው ተሪክ ላይ መቀራመት ምን ኣመጣው?

የትግራይ ህዝብ ለከፈለው መስዋእት ካሳ መክፈል ባይቻልም፤ ለሰራው ታሪክ ምስጋና መስጠት ና ተከብሮ በታሪክ ማህደር እንዲኖር ማድረግ በራሱ በቂ ካሳ ነበረ፡፡ ሆኖም ግን በ35ኛው የብኣዴን የምስረታ በዓል እንደታየው ከሆነ የትግራይ ህዝብ ታሪክ የሚፈታተን ሌላ ጋሬጣ የተከሰተ ይመስላል፡፡

ብኣዴን እንደ ድርጅት ዴሞክራስዊ ድርጅት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ከህወሓት ጋር ኣብሮ የተገለ ና ባለፉት 24 የሰላም ዓመታት የትግራይ ህዝብ መስዋእትን በኣግባቡ እውቅና የሰጠ ድርጅትም ነው፡፡

ሰሞኑን በተከበረው 35ኛው የምሰረታ በዓል ግን ከተለመደው ሂደት ወጣ ያሉ ንግገሮች የሚሰሙበትና የታሪክ ጨረታ የሚመስል ይዘት ያላቸው ዘጋቢ ፊልሞች ለኣድማጮች የበቁበት ሁኔታ ታይተዋል፡፡

ብኣዴን ያለወትሮው ለየት ያለ የትግል ታሪክ ኣቀራረብ ይዞ መጥተዋል፡፡ ብኣዴን ምናልባት ይህ ያደረገበት ሁኔታ ከኣንዳድ ትምክህተኛ ሃይሎች የሚመጣውን የህወሓት ተለጣፊ ነው የሚል ፍረጃ ለመከላከል ይመስላል፡፡ ትምክህተኞች ለመታገል ቆርጦ መነሳቱ ጥሩ ነው፡፡ ሆነም ግን ሌላ ጫፍ ረግጦ ሌላ ኣላስፈላጊ ንትርክ የሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ልብ ያለ ኣይመስልም፡፡

ብኣዴን የህወሓት ተለጣፊ እንዳልሆነ በትግራይ ክልል ከተመሰረተበት ወቅት ጀምሮ በቂ ማስረጃ ኣለው፡፡ ወደ ትግራይ ክልል ሂዶ፤ ቀድሞ ከኢህኣፓ ስር እያለ የተዋጋውን ህወሓት ነፃ ያወጣውን መሬት ላይ ቁጭ ብሎ፤ ከህወሓት ፕሮግራም የማይስማ ፕሮግራም ቀርፆ፤ ኣቃሙን በግልፅ ኣስቀምጦ የነሮ ጠንካራ ድርጅት ነው፡፡ ይሄ ኢህዴን ብኣዴን የማንም ተለጣፊ እንዳልሆነ የሚመሰክር ኣኩሪ ታሪክ ነው፡፡

ሌላ የደርግ ሰራዊት በኣፍዓበት፣ ሽረ እንዳስላሴ፣ ምፅዋዕ ስትራቴጂካዊ ጦርነቶች ድባቅ ተመቶ ዳግም ወደማይመለስበት ደረጃ ወርዶ፤ የተበታተነው የደርግ ሰራዊት በመሃል ሃገር በሰፈረት በወቅት፤ ደርግን ሙሉበምሉ ለመደምሰስ በተደረጉት የሁለት ዓመት ውግያዎች፤ በብኣዴን መሪነት የኣማራ ክልል ህዝብ ያሳየው ኣኩሪ ገድል ነው፡፡

ብኣዴን ብቻውን ና ከህወሓት ጋር በመሆን ነፃ ባወጣቸው መሬት ሲንቀሳቀስ ቆይቶ፤ ትግራይ ነፃ ከወጣ በኋላ፤ የህወሓት ሃይል ወደ ኣማራ ክልል ሲሻገርና ለተቀሩት ፊልምያዎች ሲዘጋጅ፤ ብኣዴን የነበረው ዉሱን ሃይል ከህወሓት ጎን በማሰለፉ ና መታገሉ ሳይሆን ዋናው ትልቅነቱ፤ የኣማራ ህዝብ ከህወሓት ታጋዮች እንዲተባበር የሰራው ትልቅ ፖለቲካዊ ስራ ነው፡፡ ያለ ኣማራ ህዝብ ድጋፍ ግዝፉ የህወሓት ሃይል በመሓል ኣገር የተከሃዱት ጦርነቶች ማሸነፉ አይቀሬ ቢሆንም፤ ኣሰቸጋሪ ይሆን እንደነበረ ግን ጥርጥር የለውም፡፡ በተሳካ ድል እንዲገኝ ታድያ ኢህዴን በሃይል ደረጃ የቻለውን ማድረጉ ሳይሆን፤ በፖለቲካ ስራው መስክ የኣንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ከደርግ ውድቀት ብኋላም ትምክህት በመታገል ያሳየው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እጅግን የሚደነቅና እያንዳንዱ የብኣዴን ኣመራር ና ኣባል ሊኮራበት የሚገባ ነው፡፡ ምስጋናም ይገባዋል፡፡ እነዚህን ነው ኣጉልቶ ማውጣት ና ለተተኪው ትልውድ መተላለፍ ያለባቸው፡፡

ይህ በንዲህ እያለ፤ ሰመኑን ግን ከዚህ እውነታ ወጣ ያለና ኣነጋጋሪ ክስተቶች በብኣዴን መንደር ተከስተዋል፡፡ በርግጥ ኣነጋጋሪው ክስተት የትግል ታሪኩ እውነታ እንዳለ ሲያስቀሙጡ ለነበሩት ነባር ኣመራሮች ኣይመለከትም፡፡

በጀመርያ ደረጃ በተለያዩ ዘጋቢ ፊልሞች ስናየው እንደሰነበትነው ብኣዴን እንደ ድርጅት ብቻውን ያስመዘገባቸው የውግያ ውሎዎች ኣሁን እየቀረቡ እንዳሉት ማቅረብ ከፈለገ እስካሁን ለምን ዘገየ? በኣንዳንድ ፊልሞች እንዳየነው (ለምሳሌ ፍልምያ በተሰኘውና በኣማራ ተሌቭዥን በተከታታይ በተሰራጨው ዘጋቢ ፊልም የዋግ-ህምራ ኣከባቢ ነፃ ለማውጣት የተካሄደው ጦርነት) በተመለከተ ኣንዳንድ ትረካው የሚነግሩ ሶዎች የህወሓት ሃይሎች እንቅስቃሴ መጥቀስ ለምን ኣልፈለጉም? በዚህ ተመሳሳይ ፊልም የጉና ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሃይሎች የተፈፀመ ሆኖ እያለ ኢህዴን/ብኣዴን ባልነበረበት እንደነበረ መስሎ ማቅረብ ለምን ኣስፈለገ? በግልፅ በዚህ ፊልም የህወሓት ታጋዮች በሰማእት ታጋይ ጎምፅ መሪነት የተቆፈረ ምሽግ በታንክ ሲዘሉ ይታያል ስማቸው ግን ኣይጠቀስም ለምን?

ኣልያም ከ1982-83 ዓ/ም በኣማራ ክልል የተደረጉት የውግያ ውሎዎች እንደከዚህ በፊቱ የኢህኣዴግ ሰራዊት ውሎ እየተበሉ መቅረብ ኣልነበረበቻውም ወይ? ለምሳሌ ከዚህ በፊት የተሰሩ እንደነ የህዳሴው ዋዜማ፣ ቀሺ ገብሩ ና ኣሞራ ፊልሞች፤ ዓጃቢ ትረካዎች የኢህኣዴግ ሰራዊት ነው የሚሉት፡፡ ለምን በዚህ ኣካሄድ ኣልተቀጠለበትም? እዚህ ላይ ብኣዴን የራሱን በዓል እያከበረ እንደሆነ ዘንግቼ ኣይደለም፡፡ ግን ብኣዴን/ኢህኣዴግ እየተባለ መተረኩ ቡዙም ትኩረት ያልተሰጠው እንደነበረ ለማስገንዘብ ና ከቆየው ኣካሄድ ግልጥ በላ መልኩ የተለየ እንደነበረ ለመናገር ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በበዓሉ ዋዜማ ከተለያዩ የመንግስት ና የድርጅቱ ባለስልጣና ይሰጥ የነበረ መግለጫ ትንሽ ያልተለመደ ባህሪና መንፈስ ይንፀባረቅበት ነበረ፡፡ በተለይ በተለይ ኣንዳንድ የኣማራ ክልል ባለስልጣናት ና የድርጅቱ ሓላፊዎች በመጀመርያው የባዓሉ የዝግጅት ምዕራፍ ወቅት ይሰጡት የነበረ ኣስታየት ወጣ ያለና ከዚህ በፊት ያልተለመደ ነበር፡፡ ለምሳሌ ኣንድ ባለ ሰልጣን እየደጋገመ “የኣማራ ህዝብ ራሱ በራሱ ታግሎ ብእህዴን/ብኣዴን ፈጠረ” እያለ ብቁጣ መንፈስ ሲናገር ሌላ ትርጉም የሚያስዝ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ ከዚህ ንግግር ኣካያ የትግራይ ህዝብ በእግር መትከሉ ወቅት ለኢህዴን ያደረገው ድጋፍ፣ ህወሓት ለብኣዴን የሰጠው የጦር መሳርያ ድጋፍ፣ በውጭ ግንኝነቱ ለነበረው መደጋገፍ፤ በኋላ በደርግ ውድቀት ማግስት ጥረት ለማቋቋም ከትእምት የተሰጠው ብድር … ወዘተ ቦታ ያላቸው ኣይመስሉም፡፡

ሌላ ጥያቄ የጫረ ክስተት ኣንዳንድ ከፍተኛ የሃገራችን ባለስልጣናት በተሌቭዝን መስኮት የሰጡት ኣስታየት ነው፡፡ እነዚህ በለስልጣናት ሲናገሩ “እኔ ና ድርጅቴ የኢህዴን/ብኣዴን የትግል ውጤት ነን” ብለው ያስቀምጣሉ፡፡ ይህ ከሆነ እሰየው፡፡ ሰለ ኢህዴን/ብኣዴን ቀደምት ኣባላት የትግል ፅናት መገለጫቸውም የሚገባ ነው ባይ ነኝ፡፡ ሆኖም ግን አደነዚህ የመሳሰሉ ከተመሳሳይ ኣፍ የወጡ ንግግሮች ከዚህ በፊት በህወሓት ምሰረታ በዓል ከተነገሩት ኣንፃር ተቃርኖ የሚታይባቸው ይመስላሉ፡፡ ከዚህ ተነስተን በተመሳሳይ ሰዎች ከኣንድ ኣመት በፊት ለህወሓትና ለትግራይ ህዝብ የቀረበው ምስጋና ያማይገባው ነበር ማለት ነውን? ብለን እንድንጥየቅን ኣስገዶናል፡፡

እነዚህ ና ሌሎች ትዝብቶች ሰሞኑን ከ35ኛው የብኣዴን ምሰረታ በዓል ጋር ተያይዘው እየተነሰኑ ማነጋገርያ ኣርስት ሆነው ይገኛሉ፡፡

እኔ እንደ ግለሰው እነዚህ ትዝብቶች ካነሱት ና ከተከራከሩት ኣንዱ ነኝ፡፡ ምናልባት እነዚህ ትዝብቶች ላይ ኣስታየት በመስጠቴ ብዙ ሰዎች ላይመቻቸው ይችላል ኣልያም ጠቃሚ ኣርእስት ኣድርገው ላይ ወስዱት ይችላሉ፡፡ በኔ እይታ ግን እጅግ ትላልቅ ኣጀንዳዎች ናቸው፡፡ ለምን ለሚለው ምክንያቶቼን ላስቀምጥ፤

1. ብኣዴን ለምን በዚሁ ወቅት ከኢህኣዴግ ትግል ተነጥሎ የግለ-ድርጅት የታሪክ ባለቤትነት ጥያቄ ኣነሳ የሚል ጥያቄ ነው፡፡ በርግጥ ከተለያዩ ኣካላት እንደሰማነው ለዚህ የተለየ መነሻ የሆኑት ነጥቦች የኣማራ ዴሞክራስያዊ ብሄርተኝንት ለማስተዋወቅ፣ ለመጪው ትውልድ የኢዴን ታሪክ ለመንገር ና በብኣዴን መሪነት የተሰሩ የልማት ስራዎች ኣግልቶ ለማውጣት የሚሉ ናቸው፡፡ ታድያ ዴሞክራሰያዊ ብሄርተኝነት ለሌች ስራና ታሪክ እውቅና ኣትስጥ ይላል እንዴ? የሌሎች ታሪክ የራስህ ኣሰመስለህ ኣቅርብ ይላል እንዴ? የሌሎች የጀግንነት ውሎ እየወሰዱ ዴሞክራስዊ ብሄርተኛ ነኝ ማለቱስ ከትምክህተኝነት በምን ይለያል?

2. የትግራይ ህዝብ የትግል መንስኤ ከነበሩት ምክንያቶች ኣንዱ ከምንሊክ በኋላ የተፈጠረቸው ኢትዮጵያ የነበረው የታሪክ ኣፃፃፍ ነው፡፡ ይሄ ኣግላይ ጠቅላይ የታሪክ ኣፃፃፍ በመሰረቱ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረ-ሰቦች በግል የሰሩት ታሪክ የሚጨፈልቅ፣ ከነሱ ነጥሎ ለሌሎች የሚሰጥ፣ ባለታሪኮችን ኣግልሎ በታሪክ ጎዳና ላልነበሩ የሚሰጥ … ወዘተ ነበረ፡፡ በዚህ የታሪክ ኣፃፃፍ ኩፉኛ የተሰቃየም የትግራይ ህዝብ ነበረ፡፡ የ3000 ዘመናት ታሪክ ያላት ሃገር እየተባለ ሲዘመር የትግራይ ህዝብና መሪዎቹ በግምባር ቀድምትነት የሰርዋቸው ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ነጥቦች ኣይነሱም፡፡ ለምሳሌ የጉንደት፣ ጉራዕ፣ ኩፊት፣ ዶግዓሊ … ጦርነቶች ከታሪክ ማህድር ተገለው ቆይተዋል ቢባል ማጋነን ኣይደለም፡፡ ታድያ የታሪክ ግዞዋችንና ኣፃፃፋችን እርስ በራሳችን እንድንናቆር ምክንያት ከነበረ፤ ከዚህ መማር ትተን የታሪክ ጨረታ በሚመስል መልኩ ዘጋቢ ፊልሞች መስራት ለምን ኣስፈለገ?

3. ክርክሩ እየጦፈ በሄደ ቁጥር ኣንዳድ ወገኖች የኢትዮጵያ ታሪክ ስለሆነ ኣንዱ ወሰደ ኣንዱ ተወሰደ ማለቱ ምናመጣው? ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ይሄ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጉዞና ውጤቱ የሆነው ፌደራሊዝም በኣግባቡ ኣለመረዳት ይመስለኛል፡፡ በኛ ፌደራሊዝም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች የተለያየ ማንነት ያላቸው ናቸው ብለን ካበቃን በኋላ፤ የተለየያ ታሪክ እንዳላቸው መቀበልም ግድ ይለናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝበች ታሪካዊ ኣመጣጣቸውና ጉዘዋቸው የሚመስል የግል ታሪክ ኣላቸው፡፡ በጋራ የሱሩት የጋራ ታሪክም ኣላቸው፡፡ ሰለዚህ የግል ታሪክ በግል መዝገብ የጋራ ታሪክ በጋራ ታሪክ መዝገብ ማስቀመጡ ተገቢና ለሃገራችን ኣንድነት ጠቃሚ ነው ብየ ኣምናሎሁ፡፡ በዚህ ሂደት የራሴ ሚለውን ብኣዴን የመራው የኣማራ ህዝብ የትግል ታሪክ ኣግልቶ ማውጣት ከፈለገ፤ የራሱን ይወስዳል እንጂ የሌሎች የራሱን ኣስመስሎ መቀራመት የለበትም፡፡

በስተመጨረሻ ታሪካችን የሚገባውን ቦታ ኣላገኘም ኣልያም ያለኣግብ እየተወሰደ ነው ስንል ለትምክህና ለሽላ ኣይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብ ከታገለላቸው ኣላማዎች ኣንዱ የማንነቱ ኣንኳር ነጥቦች የሆነውን የራሱ ታሪክ ለማቀብ ና የታሪክ ፍሰቱ የጠበቀ የተለየ ህልውና ለማረገጥ ነበረ፡፡ ሰለዚህ የታሪክ ሽምያ አለ ብለን ስንል የትግራይ ህዝብ በዋናነት በታገለለትና መስዋእት በከፈፈለት ስርዓት ታሪኩ ታቅቦ ተከብሮ እንዲኖር ከመፈለግ ኣንፃር ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ ታሪኩን ና ማንነቱን ለመጠበቅ በካሄደው ትግል የሰራው የግል ታሪክ በግል ከሌሎች ጋር የሰራው ታሪክ በጋራ ሊመዘገብ ሲገባ፤ ኣሁን እንደታየው ክስተት ሚዛዊነት በሌለው ኣካኋን ሲዘግቡት ኣልያም ኣስመስለው ሲወስዱት ማየት እጅጉን ያሳስባል ጥያቄም ያስነሳል፡፡

በተተለይ በተለይ የደርግ ውድቀት እውን እንዲሆን ና የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊ ኣንድነት እንዲረጋገጥ ብሎም የራሱን ማንነትና ታሪክ ታቅቦ ና ተክብሮ እንዲኖር፤ የሌሎች ማንነት እንዲከበር በመሪነት ለተሰዋ ህዝብ፤ በምስጋና ፈንታ እንደዚህ ኣይነቱ ፈተና ሲገጥመው እጅጉን ያማል፡፡ የትግራይ ህዝብ ለከፈለው መስዋእት ቁሳዊ ካሳ መክፈል ባይቻልም፤ የሰራው ታሪክ ሳይሸራረፍ እንዲታቀብና ለዘለኣለም እንዲዘከር በማድረግ ልንክሰው ይገባል፡፡

ኣቅልለን ማየትም የለብን፡፡ ምክንያቱ የ17 ዓመታቱ የትግል ታሪክ ና የተከፈለው መስዋእት እያንዳንዱ የትግራይ በቴሰብ ይመለከታልና፡፡

ሰለዚህ ታሪክ ለባለ ታሪክ! ካለፈው ኣግላይ ጠቅላይ የኢትዮጵያ ታሪክ ኣፃፃፍ ስልት የፈጠረው ሃገራዊ ኣለመግባባት እንማር!

የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊ-ፌደራላዊ-ዴሞክራስያዊ-ኣንድነት ይለምልም!

***********

Mehari Yohanes is a lecturer at Department of Political Science and Strategic Studies of Mekele University. He can be reached at [email protected]

more recommended stories