ሳይንቲስቶች ወደ አገሯ የተመለሰችውን ሉሲ እውነተኝነት አረጋገጡ

ከ5 አመታት ቆይታ ወደ አገሯ ሚያዝያ 23/2005 ዓ/ም የተመለሰችው ሉሲ እውነተኛዋ መሆኗን የዘርፉ ሳይንቲስቶች አረጋገጡ ፡፡

ሉሲ /ድንቅነሽ/ ላለፉት 5 አመታት በአሜሪካ ሂውስተን ፣ ቴክሳስ፣ ሲያትል፣ኒውዮርክና ካሊፎርኒያ ኢትዮጵያን ለመላው ዓለም ስታስተዋውቅ ቆይታ ወደ አገሯ ስትመለስ ተቀይራ /ቅጅዋ/ ተመልሶ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ይነሳ ነበር ፡፡

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሉሲን በቅርበት ሲከታተሏት የነበሩት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ ዶ/ር ዘረሰናይ አለምሰገድ እንዳሉት የሉሲ ቅሪት አካል ዶ/ር ብርሃኔ አስፋው ጨምሮ በሁለት ኢትዮጵያዊያን ሳይንትስቶች እንዲሁም በሁለት አሜሪካዊያን ሳይንትስቶች ማለትም ሉሲን ለመጀመርያ ግዜ በአገኙት በዶ/ር ዶናልድ ጆሃንሰንምና ሉሲ በነበረችበት ሙዚዮም የሚሰሩ /ኩሬተር/ በዶ/ር ዳርክ ቨንቱን ሃዉት እንዲሁም ሉሲ በአገር ውስጥና ዉጪ ኩሬተራ የሆኑት በአቶ አለሙ አድማሱ ከፍተኛ ጥበቃና እንክብካቤ ሲደረግላት መቆየቷን ገልጸዋል፡፡

ሉሲን ከእነዚህ ሰዎች በስተቀር ንክኪ ያልተደረገላት መሆኑንና ገና ስትገኝ ቅሪት አካሎቿ የተሰያሙባቸው ጽሁፎች ሁሉ አብሯት እንዳሉ ዶ/ር ዘረሰናይ አረጋግጠዋል፡፡

ተመራማሪ ዶ/ር ብርሃኔ አስፈው በበኩላቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ሉሲ ትክክለኛዋ ነች ብለዋል፡፡

ሉሲን ለመጀመርያ ግዜ እ.ኤ.አ በ1974 በአገኙት ዶ/ር ዶናልካረል ጆሃንሰንም ሉሲ የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነችው ሉሲ ቅሪት አካልዋ ለማንም እንደማይቀየርና ወደ ሀገሯዋ የተመለሰችው ትክክለኛዋ ሉሲ ስለመሆንዋ አረጋግጠዋል፡፡

ሉሲ በነበረችበት ሙዝየም የሚሰሩ /ኩሬተር/ ዶ/ር ዳርክ ቨንቱን ሃውተም በዉልና ስምምነት መሰረት የወሰዱቱን ትክክለኛዋን ሉሲና 148 ልዩ ልዩ ቅርሶች መልሰው ማስረከባቸውን ገልፀዋል፡፡

ከአምስት አመት ቆይታ ወደ አገሯ ሚያዝያ 23/2005 ዓ/ም የተመለሰችው ሉሲ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገብታለች፡፡

ሉሲ 3 ነጥብ 18 ሚሊዮን እድሜ ያላት ሲሆን አንድ ነጥብ 10 ሜትር ቁመት እንደነበራት ይገመታል፡፡

ሉሲ ወደ አሜሪካ የተላከችው ሀምሌ 29 /1999 ዓ/ም ነበር ፡፡

***********

ምንጭ – ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን via ERTA

Daniel Berhane

more recommended stories