የኢትዮ-ሶማሌ የፓርቲና የክልል አመራሮች የተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም ውሳኔ አሳለፉ

(አብዱረዛቅ ካፊ)

የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩና የክልሉ ካቢኔ አባላት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርና የኢ.ሶ. ህ.ዴ.ፓ ሊቃመንበር አቶ መሀመድ ረሺድ ኢሳቅን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸው የሚመለሱ ውሳኔ አሳልፏል።

ወሳኔው የተላለፈው ዛሬ ቅዳሜ ኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርና የክልሉ ካቢኔ አባላት ዛሬ  ቅዳሜ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው።

በውሳኔው መሰረት፤ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የሶማሌ ወገኖች በራሱ በክልሉ መንግስት ወደ ቄያቸው የማስመለስ ሥራ ከወዲሁ እንደሚጀመር እና ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ኦሮሞ ወንድሞች በተለይ በጅግጅጋና በሌሎች አከባቢዎች በተለያዩ ንግድ ሥራዎች ተሰማርቶ የነበሩ የኦሮሞ ወንድሞች ወደ ክልሉ የሚመለሱበት ስራ እንደሚሰራ  አስታውቋል።

ኦሮሞ ወገኖቹ ወደ ክልሉ በሚመጡበት ጊዜ ደማቅ የወንድማማችነት አቀባበል እንደሚደረግላቸው ክልሉ አስታውቋል።
ይህ ደግሞ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በአገራቸው በፈለጉት አከባቢ  ለመኖር እኩል ህገመስግስታዊ መብት ስላላቸው ነው ብሏል የክልሉ መንግስት።

መጨረሻም የክልሉ ህዝብ፣ የክልሉ መሪ ድርጅት ኢ.ሶ. ህ.ዴ.ፓ እና የክልሉ መንግስት፤ ከክልሉ የተፈናቀሉ  ኦሮሞ ወንድሞች በተለይ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ ኦሮሞ ወገኖች  ወደ ቀዬያቸው እንድመለሱ ጥሪ አቀርቧል።

********

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago