Audio| ዳንኤል ብርሃነ፣ አርጋው አሽኔ፣ መስፍን ነጋሽና ጽዮን ግርማ በVOA ላይ ያደረጉት ውይይት

በዚህ ወር የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ VOA የአማርኛ ፕሮግራም አራት የሚዲያ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ያደረጉትን ውይይት አድርገው ነበር፡፡

በሁለት ክፍል የተሰራጨው ውይይት ተሳታፊዎች፡- ጽዮን ግርማ፣ አርጋው አሽኔ፣ ዳንኤል ብርሃነ እናመስፍን ነጋሽ ነበሩ፡፡

የፕሮግራሙ ርዕሰ-ጉዳይ (በVOA ድረ-ገጽ ላይ የሠፈረው) ጽሑፍ እንደሚከተለው ሲሆን፡-

ነጻና ሚዛናዊ ምርጫ ለማካሄድ የሁሉንም ተወዳዳሪዎች ፕሮግራም ለሕዝብ የሚያደርስ በነጻነት የሚዘግብ መገናኛ ብዙኃን ወሳኝነት የዲሞክራሲ ባሕልና መሠረትም ነው።

በርካታ ጋዜጠኞች እስር ላይ በሚገኙባትና ያንኑ ያህል ቁጥራቸው የበዛ አገር ጥለው በተሰደዱባት ኢትዮጵያ በነጻነት መዘገብ የሚችሉ ጋዜጠኞች መኖር እያነጋገረ ነው።

ለጋዜጠኞች መብት ከቆሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ Freedom House በቅርቡ ስለ አገሮች የነጻ ፕሬስ ይዞታ ባወጣው ዓመታዊ ሪፓርቱ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ቀጥሎ ጋዜጠኞች የታሰሩባት አገር መሆንዋን ዘግቧል። በጸረ ሽብር ሕጉና በወንጀለኛ መቅጫ የተከሰሱ ቢያንስ አስራ ሰባት ጋዜጠኞች በእስራ ላይ እንደሚገኙ ሌሎች በርካቶች እንደተሰደዱ በሪፖርቱ ዘርዝሯል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለ ስልጣናት በተደጋጋሚ “ጋዜጠኛ ሰለሆነ የሚታሰር ማንም የለም። በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ብቻ ናቸው የታሰሩት፤” ይላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰለመጪዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ለመዘገብ የሚያስችል ነጻ የመገናኛ ብዙኃን ሕዋ አለ? ከአድማጮች ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን መልስ ጨምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ ጋዜጠኞች ተጋብዘው ይወያያሉ።

ውይይቱ በVOA የተላለፈው በታህሳስ 4 (Dec. 13) እና ታህሳስ 11(Dec. 20) ሲሆን፤ ሁለቱን ክፍሎች አንድ ላይ በማድረግ ከታች ባለው የድምጽ ፋይል አቅርበናቸዋል፡፡

– – – – –

*********

Daniel Berhane

Daniel Berhane

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago