ግቤ ሶስት 82 በመቶ – ገናሌ ዳዋ ሶስት 48 በመቶ – ህዳሴ ግድብ 32 በመቶ ተጠናቅቀዋል

(የማነ ገብረስላሴ)

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ ።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል የውጭ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም በማስመልከት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የግቤ ሶስት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የገናሌ ዳዋ የሃይል ማመንጫ ግድቦችና የአዳማ ሁለት የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ናቸው።

የግቤ ሶስት የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍታው108 ሜትር መድረሱን ገልጸው፤ በግድቡ በግራና ቀኝ በኩል የኮንክሪት ሙሌት ስራዎች በአብዛኛው መከናወናቸውንም ተናግረዋል። የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የሃይድሮ መካኒካል ስራዎች እየተፋጠኑ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዩኒቶች የጀኔሬተርና ተርባይን ክፍሎች የተከላና የገጠማ ስራ ተጀምሯል። በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ወሮችም የፕሮጀክቱ ሁለት ዩኒቶች የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ ርብርብ እየተደረገ ነው።

ፕሮጀክቱ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት በሚጀምርበት ወቅት ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ለማስተላለፍ ከግቤ-ወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ ተገንብተው ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የገለጹት።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ ግንባታ 24 ሰዓት እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት ሃላፊው፤ የግንባታው 32 በመቶ መጠናቀቁንም ጠቁመዋል። ከግድቡ ግንባታ ጎን ለጎን የሃይል ማከፋፈያ ግንባታዎችም እየተፋጠኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

አቶ ምስክር እንዳሉት፤ የገናሌ ዳዋ ሶስት ፕሮጀክት የውሃ ማስተንፈሻ ቁፋሮ ግንባታም ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።ፕሮጀክቱ 48 ነጥብ 7 ሜጋዋት የሚያመነጩ ሶስት ዩኒቶች ያሉት ሲሆን፤ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር 254 ሜጋዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።

ለፕሮጀክቱ የተያዘው ወጪ 451 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም 60 በመቶው በቻይና መንግስት ብድር ቀሪው 40 በመቶ ደግሞ በኢፌዴሪ መንግስት የሚሸፈን መሆኑንም ነው የጠቆሙት።

እንደ ሃላፊው ገለጻ፤ ፕሮጀክቱ ለአገልግሎት ሲበቃ የመነጨውን ሃይል የሚያስተላልፉ ገናሌ -ወላይታ ሶዶ በ300 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት የቅየሳ ስራ አየተገባደደ ነው።

153 ሜጋዋት የሚያመነጨውን የአዳማ ሁለት የነፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸሙ 40 በመቶ መድረሱንም ተናግረዋል።

የግቤ ሶስት የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 1870 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው ታውቋል።ይህም በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለውን የሃይል አቅርቦት በ94 በመቶ ለማሳደግ ያስችላል።ፕሮጀክቱ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዩሮ ወጪ እየተደረገበት ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 40 በመቶ እስከሚደርስ ድረስም ወጪው የተሸፈነው በመንግስት መሆኑ ተገልጿል። ቀጥሎ ላለው የግንባታ ሂደት የቻይና የኢንዱስትሪ የንግድ ባንክ 470 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ሰጥቷል።

የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ ዕድሎችን መፍጠራቸውም ተመልክቷል።

*******

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን – የካቲት 20፣ 2014 –  ‹‹የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ ቀጥሏል››

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago