መንግስት:- ”አልሸባብና በኤርትራ የሚታገዙ አሸባሪዎች ለጥቃት እየተዘጋጁ ነው”

አልሸባብ በመባል የሚታወቀው አለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን እና በኤርትራ መንግስት እገዛ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በሃገራችን ውስጥ የተለያዩ ስፍራዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ አስተማማኝ መረጃ ያለው መሆኑን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡

የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሉ መላው ህብረተሰብና የፀጥታ ሃየሎች ሁኔታውን በንቃት በመከታተል ከፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ጋር በትብብር እንዲሰሩም ጥሪውን አስተላለፏል፡፡

በጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሉ የተላለፈው ይኸው መግለጫ ባለፈው ጥቅምት 3ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ ለሽብር ተግባር ሲሰናዱ በራሳቸው ላይ ባደረሱት አደጋ ህይወታቸው የጠፋ ሁለት የሶማሊያዊያን አሸባሪዎች ጉዳይ ላይ ምርመራ ሲያደረግ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

እነዚህ ሁለት አሸባሪዎች በወቀቱ የኢትዮጵያና የናይጀሪያ ብሄራዊ ቡድኖች የሚያደርጉትን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር በሚከታተሉ የስፖርት አፍቃሪዎች ላይ አደጋ ለማድረስ ዓላማ እንደነበራቸው የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን መግለጫው በተጨማሪ አስታውቋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የፀረ ሽብር ግብረሃይሉ የጀመረውን ምርመራ በተጠናከረ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ግብረሃይሉ ገልጿል፡፡

በቅርቡ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞችና አካባቢዎች በሁለት አቅጣጫ የተመራና ተመሳሳይ ዓላማና ቅንጅት ያለው የሽብር ጥቃት ዝግጅት መኖሩን የሚመለከት አስተማማኝ መረጃ ማግኝቱን የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሉ የመረጃ ክፍል ይፋ ባደረገው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሽብር ጥቃት ዝግጅቶቹ ጠንሳሾች አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን እና የኤርትራ መንግስት ያሰማራቸው አሸባሪዎች መሆናቸውን የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሉ በመግለጫው አስታውቆ የአሸባሪዎች አላማም በሽብር ጥቃቶች የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋትን በማናጋት የልማት ግስጋሴዎች ማደናቀፍ መሆኑን ግብር ሃይሉ ገልጿል፡፡

በህብርተሰቡ ላይ አሰቃቂ ጉዳት ሊያስከትል የሚችለውን ይህን እኩይ የሽብር ጥቃት ዝግጅት ተግባራዊ ሳይሆን ለማምከን በሚደረገው ጥረት ላይም መላው ህዝብና የፀጥታ ሀይሎች እንደወትሮው በመተባበር ንቁ ክትትልና ተሳትፎ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡም የፀረ ሽብር ግብር ሀይሉ አበክሮ ጠይቋል፡፡

በመሆኑም ህዝብ በሚዝናናባቸው ስፍራዎች የሚሰሩ ዜጎች ከወትሮው የተለየ አጠራጣሪ ሁኔታዎችና ግለሰቦች በገጠሟቸው ግዜ በአካባቢያቸው ላሉ የፖሊስና የጸጥታ ሀይሎች በፍጥነት እንዲያሳውቁም የጸረ ሽብር ግብረ ሀይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም ሆቴሎቻቸውንና መኖሪያ ቤታቸውን የሚያከራዩ ባለንብረቶችና ባለ ይዞታዎች በተለይ የውጭ ሀገር ዜጎችንና የማያውቋቸውን ኢትዮጵውያንን አድራሻ በአግባቡ መዝግበው በመያዝ መረጃን ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ የህግ ግዴታ እንዳለባቸው መግለጫው በጥብቅ አስጠንቅቋል፡፡

በተመሳሳይ መኪናዎቻቸውን የሚያከራዩ ግለሰቦች ፣ድርጅቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለታክሲዎች የደበኞቻቸውን ማንነት የሚገልጽ ሙሉ መረጃ የመያዝና የማሳወቅ እንዲሁም የሚጭኗቸውን ማናቸውንም ዕቃዎች የማወቅ ግዴታም ያለባቸው መሆኑን የጸረ ሽብር ግብረ ሀይሉ አስታውቋል፡፡ ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥመው ሁኔታውን በአቅራቢያው ላሉ የፖሊስና የፀጥታ ሀይሎች እንዲያሳውቁም አሳስቧል፡፡

በየአካባቢው በሚገኙ የፍተሻ ኬላዎች ላይ የሚሰሩ የፍተሻ ስራተኞች ተግባራቸውን ከወትሮ በተለየ ጥንቃቄ ና አትኩሮት ማከናወን እንዳለባቸውም የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉ አስታውቋል፡፡

——————

Source: ERTA, Nov. 5, 2013, titled “በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶች ሊደርሱ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ቅደመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ”.

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago