‹አንድነት› ፓርቲ- ‘ሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት’ ንቅናቄ አወጀ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ዛሬ ሰኔ 13/2005 በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቀው ለ3 ወራት የሚዘልቅ “ሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የተሰኘ ሕዝባዊ ንቅናቄ አውጇል።

ሕዝባዊ ንቅናቄው የአዳራሽ ስብሰባ፣ የተቃውሞ ሰልፍ እና የፀረሽብር ሕጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ ፊርማ (ፒቲሽን) ይሰበሰባል። በዚህም በአዲስ አበባ 6 እና በክልል ደግሞ ለመጀመሪያ ዙር ዐሥር ስብሰባዎች ይካሄዳሉ።

የንቅናቄው ዓላማ የፀረሽብር ሕጉ እንዲሰረዝ፣ የዜጎች መፈናቀል እና የመሬት መቀራመት እንዲቆም፣ የሥራ አጥነትና የኑሮ ውድነት እንዲቀረፍ እና የንግዱ ማኅበረሰብ ውስጥ ፍትሐዊ ውድድር እንዲሰፍን መሆኑ በመግለጫው ተጠቁሟል።

የፓርቲው ተወካዮች “ሌላ ፓርቲ ሲያደርግ አይታችሁ ነው ወይ?” በሚል ለቀረበው ጥያቄ ሲመልሱ “ከሌላ መማር ለአንድነት ይጠቅመዋል እንጂ አይጎዳውም ሆኖም ስር እስክንሰድ ጊዜ ወስደን ነው እንጂ ዓመታዊ ዕቅዳችን ላይ ነበር። ፓርቲያችን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ እንጂ በግብታዊነት አይሠራም” ብለዋል። የፀረ ሽብሩን ሕግ እንዲሰረዝ ስለሚያስፈልግበት ምክንያት ሲናገሩ ደግሞ የፀረ ሽብር ሕጉ ከአሸባሪዎች ይልቅ ዜጎችን ለማጥቃት የተዘጋጀ ነው በማለት ንቅናቄው ለሕዝብ ጥቅም መሆኑን “አሁን እየጠየቅን ያለነው ስለአንዱዓለም ወይም ስለአንድነት አይደለም። ስለኢትዮጵያውያን ነው” በሚል ገልጸውታል።

“ፀረ ሽብር ሕጉ እንዲሻር ነው ወይስ እንዲሻሻል የምትጠይቁት?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ተወካዮቹ “አንድ አዋጅ ሕገ መንግሥቱን አንዴ ከጣሰ ይሰረዛል። ይህ አዋጅ ግን እስከ15 ጊዜ ሕገ መንግሥቱን ስለሚጥስ መሰረዝ አለበት” ብለው መልሰዋል። “ኢትዮጵያ የውጭ ሽብር ስጋት ቢኖርባትም አዋጁ ዜጎችን ለማፈን የወጣ ነው። ማሰብም ሳይቀር ይከለክላል” ብለውታል።

“የሰልፍ ፈቃድ ብትከለከሉስ?” ለሚለው ጥያቄ ደግሞ “ሕግ ማሳወቅ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይጠይቀንም። ትግላችን ሰላማዊ ነው፣ አይቆምም” ብለዋል።

*********

Source: Fenote – June 20, 2013, titled “አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሕዝባዊ ንቅናቄ በይፋ ጀመረ”.

9.14540.489673
Daniel Berhane

Daniel Berhane

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago