ሉሲ ከ5 ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገባች

ሐምሌ 29/1999 ምሽት 1፡30 ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተጓዘችው ሉሲ ዛሬ ሚያዝያ 23/2005 ከረፋዱ 4፡20 ላይ አዲስ አበባ ገብታለች፡፡

ሉሲ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ፣ ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሀንሰንና ሌሎች ግለሰቦች አቀባበል አድርገውላታል፡፡

ከሉሲ ጋር ወደ አሜሪካ ተጉዘው የነበሩ ሌሎች 148 ቅርሶችም ሚያዝያ 22/2005 ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ወደ አሜሪካን የሄደችው ለአምስት ዓመት ቆይታ ሲሆን አሜሪካን በነበረችበት ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ነዋሪዎችና ጎብኝዎች ተመልክተዋታል፡፡

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ሉሲ በህዝብ ለህዝብና የመንግስታት ግንኙነት ላይ አምባሳደር ሆና ማገልገሏ ተገልጿል፡፡ ከጎብኝዎችም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችም በቅርስ አያያዝና ጥናት፣ በቅርስ አውደ ርዕይ ዝግጅትና መሰል ዘርፎች ከአሜሪካዊያን ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ችለዋል፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው ሉሲ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 6/2005 ድረስ ለህዝብ እይታ ትቀርባለች፡፡ ከዚያም ለበለጠ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር አመቺ በሆነ ቦታ እንድታርፍ ይደረጋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አቶ አሚን አብዱልቃድር ሉሲ ወደ አሜሪካ ከመጓዟ በፊት ሲቲ ስካን የተነሳች በመሆኗና በርክክቡ ወቅትም ለመጀመሪያ ጊዜ በቁፋሮ ያገኟትን የስነ ቅርስ ባለሙያዎች ጨምሮ ሌሎች አለማቀፍ ባለሙያዎች የተገኙ ስለሆነ በማንነቷ ላይ ምንም አይነት ጥርጣሬ የለንም ብለዋል፡፡

Source: ERTA – May 1, 2013. Originally titled “ሉሲ እና 148 ቅርሶች አዲስ አበባ ገቡ“.

9.14540.489673
Daniel Berhane

Daniel Berhane

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago