የአማራ እና የትግራይ ክልል የወሰን ጥያቄ በተመለከተ (On State Border Change)

(መኮነን ፍስሃ)

የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ህገ-መንግስታዊ ግንኙነት አለቸው፡፡ መፍትሔውም ህገ-መንግስታዊ ስርአቱ ተከትሎ መሆን አለበት፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 48 (1) እንደህ ይደነግጋል: “የክልሎችን ወሰን በሚመለከት ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት ይፈጸማል፡፡ በሚመለከታቸው ክልሎች መስማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የህዝብን አሰፋፈርና ፍላጎት መሰረት መባድረግ ይወስናል፡፡”

የፌደራል ስርአቱን ተከትሎ የሁለቱም አጎራባች ክልሎች የአስተዳደር ወሰን ለ28 አመታት ሲሰራበት የቆየ ብሆንም የይገባኛል ጥያቄ ከአማራ ክልል በመነሳቱ ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን ተከትሎ በወርሀ ጳጉሜ 2009 ዓ/ም በሁለትም ርእሳነ መስተዳደር ማለትም በአማራ ክልል በኩል አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተወከሉበት በትግራይ ክልል በኩል ደግሞ አቶ አባይ ውልዱ በፈረሙት ስምምነት ኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 48 መሰረት እልባት አግኝቶ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡

ከዚህ በኃላ የሚቀርብ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የግዛት ማስፋፋት አለማ እንጂ የአማራ ክልል ህጋዊ የወሰን ጥያቄ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ስምምነቱ ህጋዊና ገዢ ነው፡፡ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤትም በይግባኝ መልክ ሊሄድም አይችልም፡፡ የአማራ ክልል በድጋሜ ጥያቄ እንዲያቀርብ መፍቀድ የድብብቆሽ ጨዋታ እንጂ የህገ-መንግስት ጥያቄ ፍጹም ሊሆን አይችልም፡፡ በባህላዊና በሀይማኖታዊ ተቋማት የሚደረጉ የእርቅ ስርአቶች ከላይ ከተቀመጡት የህግ ማእቀፎች አንጻር ሊቃኙ ይገባል፡፡

የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ መሬትና ተፈጥሮ ሀብት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች የጋራ ሀብት ነው ከሚል አንጻርም መቃኘት አለበት፡፡ ይህ ብቻም አይደለም ማንኛውም ኢትዮጰያዎ በፈለገው አከባቢ ተንቀሳቅሶ የመኖርና የመስራት መብት አለው፡፡

ይህን የማያከብር የአማራ ክልል መንግስትና ሀይል ወይም ቡድን ስለ መሬት አብዝቶ የሚጨነቀው የአሀዳዊነት አባዜ (Centralist Mentality)ና የግዛት አስፋፊነት (Expansionist Mentality) ድምር ውጤት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሊታከም የሚገባው በሽታ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የማንነት ጥያቄና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ፍፀም የተለያየ ህግና ስርአት ያላቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የማንነት ጥያቄ የሚቀርበው በሚመለከተው ብሄር ብረሰብና ህዝብ እንጂ በማንኛውም አካል ወይም በማንኛውም የመንግስት አካል ሊቀርብ አይችልም፡፡ በሁለተም የሚያገናኝ ድልድይ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ የህዝብ ፍላጎት ነው፡፡ እሱም ምርጫው የፖለቲከኞች ሳይሆን በሚመለከተው ህዝብ ፍላጎት ብቻ የሚወሰን ጉዳይ ነው፡፡ የራስህ ህድል በራስህ የመወሰን መብት መሰረቱ የህዝቦች ሉአላዊ ስልጣን እንጂ የሌላ ሀይል ፍላጎት ሊሆም አይችምና፡፡ ከዚህ ውጪ ፖለቲካ ነው፡፡ የፖለቲካ ችግር ደግሞ መፍትሄው ፖለቲካ ነው፡፡ ፖለቲካዊ መፍትሄ ደግሞ የፖለቲከኞች ነው፡፡ የፖለቲካ ጨወታ ህግጋት ደግሞ በህግ ተቀምጧል፤ ተገድቧል፡፡

በስተመጨረሻ:- ማንኛውም አከባቢ ወደዚህ ቢካለል ወይም ወደዛ ቢካለል ህዝቡም፣ ተራርውም፣ ሸንተረሩም፣ ወንዙም ተነስቶ አይሄድም፡፡ መሪዎች የህዝብ መሰረታዊ የልማት፣ የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደር ወዘተ ማረጋገጥ ሲያቅታቸው ህዝቡ እንደ ጊዚያዊ ማስተንፈሻ ይጠቀሙበታል፡፡ በህዝብ መነገድ ይቁም!

*********

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago