​10ኛው የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የጋራ ምክክር መድረክ በስኬት ተጠናቅቋል

(አብዱረዛቅ ካፊ)

ላለፉት 5ቀናት ቀናት በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተውና የክልሉ ልማት፣ ሰላምና መልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀው የጋራ መድረክ ዛሬ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡

በካሊ አደራሽ በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት የክልሉ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድና የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሳዊ ፓርት (ኢሶህዴፓ) ሊቀመንበር እና የክልል ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ መሀመድረሼድ ኢሳቅ መብራሪያ ተሰጥተዋል፡፡

በመዝጊያ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ለመድረኩ ተሳታፊ  አገር ሽማግሎች፣ ወጣቶች ፣ ሴቶችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አካላት ለነበራቸው የላቀ ተሳትፉ ከፍ ያለ ምስገና አቀርቧል፡፡

የክልሉ ህዝብና መንግስት የሀገራችንም ሆነ የክልሉን ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈፀም ለሚያደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርቧል፡፡

Photo – Ethio-somali elders consultation

የክልሉ ህዝብ ዋነኛ ጠላት የሆነው ድህነትን ለማጥፋትና በሁሉም ዘርፍ ራስን ለመቻል መንግስት የነደፈው እቅድ ውጤታማ በማድረግ ከህዝቡ ተሳትፎ ውጪ ሊታሰብ የሚቻል ጉዳይ እንዳልሆነ አስምሮበታል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችአገር ሽማግሌዎች የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ለማጠናከር የሚረዱ የጋራ የስምምነት ነጥቦች አቀርቧል፡፡

ከእነዚህ መካከል፤ 1ኛ ከጽንፈኝነት አክራሪነትና ከአሸባሪነት አመለካከት ጋር ለመታገል እንደሚሰሩ 2ኛ የክልሉ ህዝብና መንግስትም ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ለአንድ አፍታ ያህል እንዳማይቆምና የተፈናቃይ ወገኖች ኑሮ ወደ ነበሩበት መደበኛ ኑሮ ለመመለስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ 3ኛ የክልሉ ህዝብ ራሱን እንዲችል የሚያግዝ እና በውሃ፣ በእንስሳት መኖ፣ በጤናና በትምህርት መሰረት ያደረገው የክልሉ እቅድ በቁርጠኝነት እንደሚያሳኩና 4ኛ በሥራ እድል ፈጠራ የሚያተከረውና የሥራ ክቡርነት ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመገንባት ዓለማ ያደረገው ‘ተዓብና ማል’ ኢንተርፕራይዝ የክልሉ ወጣቶች በሰፊው እንዲሳተፉ ግንዛቤ እንደሚሰጡ አረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ኣወዳይ ከተማ ህይወታቸው ላጡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ቤተሰቦች ለማቋቋሚያ የሚውል ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የ500,000 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ ከተፈናቃይ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተረክበዋል፡፡

የመድረኩ ተሳተፊዎች በክልሉ ያለው የሰላም፣  የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ያላቸው ተሳትፎ በማጠናከር ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በሰላም አብሮ መኖር እና የመቻቻል የቆየ እሴቶቻችንን ይበልጥ እንዲጎለብቱ ከምን ጊዜውም በላይ እንደሚጠበቁ እንዲሁም ለህገ- መንግስታችንና ለፈዴራሊዝም ሥርዓታችን ቀጣይነት ዘብ እንደሚቆሙ ቀል ገብቷል::

በመጨረሻም በሥነ ስርዓቱ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያተረፈው ታዋቂው የሙዜቃ ባለሙያና በሶማሊማህበረሰብ ዘንድ ክብር የሚሰጠው አንጋፋው አርቲስት አህመድ አሊ ኢጋል ለመድረኩ ተዳሚዎችሁ አዝናኝ ሙዚቃ በማቅረብ አዝናንተዋል፡፡

******

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago